ክፍል ፭ ፡ ወደ ርስታችን ያልተመለስንበት ኢዮቤልዩ

ሩሲያዊው ደራሲ ፌዮዶር ዶስቶየቭስኪ በ1860ዎቹ አውሮፓን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኝ የታዘበውን በዘገበበት ማስታወሻው የለንደን ድሆች ቅዳሜ ማታን እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያሳልፉ ይነግረናል ። በቅድሚያ ሌሊቱን በሙሉ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ጭምር ደስታ ፈጽሞ በተለየው ፣ ድብርት በተጫነው መንፈስ አኳዃን ሲበሉ እና ሲጠጡ ፣ ከሕይወታቸው መራራነት ለማምለጥ ፣ ራሳቸውን ፍጹም ለማደንዘዝ በሙሉ ጥምብዝ እስኪሉ እንደሚሰክሩ መስማቱን ይዘግባል ። ሳምንቱን ሙሉ ሠርተው የቋጠሯትን ገንዘብ ቅዳሜ ሌሊት እንዲህ ይበትኗታል ። አስከትሎም እንዲህ ባለው አንድ ምሽት እሱ ራሱ በመንደራቸው ውስጥ ሲያልፍ የታዘበውን እና የተሰማውን እንደሚከተለው ይመሰክራል ።

“One such night – it was getting on for two o’clock in the morning – I lost my way and for a long time trudged the streets in the midst of a vast crowd of gloomy people, asking my way almost by gestures, because I do not know a word of English. I found my way, but the impression of what I had seen tormented me for three days afterwards. The populace is much the same anywhere, but there all was so vast, so vivid that you almost physically felt things which up till then you had only imagined. In London, you no longer see the populace. Instead, you see a loss of sensibility, systematic, resigned and encouraged. And you feel, as you look at all those social pariahs, that it will be a long time before the prophecy is fulfilled for them, a long time before they are given palm branches and white robes, and that for a long time yet they will continue to appeal to the Throne of the Almighty, crying: ‘How long, oh Lord?’ And they know it themselves and in the meantime take their revenge on society by producing all kinds of underground Mormons, shakers, tramps . . .”[1]

ይህ የዶስቶየቭስኪ ገለጻ ፌሬድሪክ ኤንግልስ በእንግሊዝ ስላለው የሠራተኛው መደብ ሁናቴ በጻፈው መጽሐፍ ከሰጠው አስተያየት[2] ጋር በእጅጉ ተመሳሳይ ሆኖ እናገኛዋለን – ተመሳሳይ ጥልቀት ባይኖራቸውም ቅሉ ። የዶስቶየቭስኪ ትዝብት ከዚህኛው የኤንግልስ ገለጻ ጋር ብቻ ሳይሆን ባለፈው ክፍል ከጠቀስነው ማርክስ እና ኤንግልስ በማኒፌስቶአቸው በከበርቴው መደብ ላይ ካዘነቡት ወቀሳና ውግዘት ጋር ተመሳሳይ መንፈስ አለው ። የትዝብታቸው መመሳሰል ትኩረታችንን ወደ ሁለት ጉዳዮች ይጠራል ።

በመጀመሪያ የማርክስን እና የኤንግልስን ትዝብት እውነትነት ያረጋግጥልናል ። ዶስቶየቭስኪ በወጣትነቱ ለሶሻሊዝም ቅርብ የነበረ ሰው ነበር ። በኋላ ዘመኑ ግን በሀገሩ ለነበሩ ሶሻሊስቶች ባለጋራ ሆኖ ብቅ አለ ። ይህን የአውሮፓ ጉብኝት ያደረገው ዐበይት ከሚባሉት የሶሻሊስት ጎራ መሪዎች ጋር ብርዕ ይማዘዝ በነበረበት ጊዜ ነው ። በወጣትነቱ ጊዜም ሆነ በዚህኛው ዘመን በሶሻሊዝቶቹ ዘንድ የነበረው ኢአማኒነት ከእርሱ ክርስትና ጋር ሊጣጣምለት አልቻለም ። ስለዚህም ምንም እንኳን ያነሧቸው የነበሩትን ጥያቄዎች ቢጋራቸውም – እነሱ እንደ መፍትሔ ያሚያቀርቧቸውን ሐሳቦችም ሆነ ጠቅላላ ርእዮታቸውን ይቃወም ነበር ። ስለዚህ ዶስቶየቭስኪ እና እነ ማርክስ በርዕዮት ባላንጣዎች ሆነው ሳለ ፣ ይህን ትዝብት መጋራታቸው የነገሩን እውነትነት የሚያረጋግጥልን ይመስለኛል ።

ሁለተኛ ግን ምንም እንኳን ኤንግልስ እና ዶስቶየቭስኪ ይህን ሁኔታ በተመለከተ ተመሳሳይ ትዝብት ቢኖራቸውም ጉዳዩ ላይ ግን ፈጽሞ የተቃረኑ ምልከታዎች ያሏቸው መሆኑ ነው ። ዶስቶየቭስኪ በማስታወሻው ለዚህ አስከፊ ሁኔታ በተለይ ሲተች እና ተጠያቂ ሲያደርግ የምናየው የማኅበረሰቡን ቁስ አካላዊነት ነው ። በተለይ ከበርቴውን ፣ ግን ሌሎቹንም መደቦች ሠራተኛውን እና ገበሬውንም ሳይቀር “ካፒታሊስቶች” እያለ ይጠራቸዋል ። ማርክስ እና ኤንግልስ በተቃራኒው የማኅበረሰቡ ቁስ አካላዊነት ችግር ሆኖ አይታያቸውም ። ይልቁንም እነርሱ ራሳቸው ቁስ አካላውያን ናቸው እንጂ ።

እርግጥ ነው ፥ ቁስ አካላዊነት (Materialism) የሚለው ቃል በሁለት መንገድ ሊተረጎም ይችላል ። የመጀመሪያው ፍልስፍናዊ ቁስ አካላዊነት ሲሆን ይህም እነ ማርክስ የርእዮታቸው መሠረት ያደረጉት ነው ። ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ ቃሉ የሰዎችን ጠባይዕ እና የማኅበረ ሰብእን ባሕል ለመግለጥ ጥቅም ላይ ሲውል የሚይዘው ትርጓሜ ሲሆን “ቁሳዊ ለሆኑ” ነገሮች ቅድሚያ እና ትኩረት መስጠትን – ቁስ ተኮር መሆንን – የሚያሳይ ነው ።

እነዚህ ሁለት ትርጉሞች ሁል ጊዜ ተባብረው አይገኙም ። አንድ ሰው ቁስ አካልነትን ይቀበላል ስንል የግድ ቁስ ተኮር ነው እያልን ላይሆን ይችላል ። ቁስ ተኮር ነው ስንልም የግድ ቁስ አካልነትን ይቀበላል እያልን አይደለም ። ማርክስ ራሱ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው ፤ ምንም እንኳን በቁስ አካልነት ፍልስፍና ባይደራደርም በሕይወቱ ግን ቁስ ተኮር አልነበረም ። የቤተ መጻሕፍት መናኝ ነበር ። በተቃራኒው እርሱ የሚያወግዛቸውና እርሱንም የሚያወግዙት ከበርቴዎች ወይም ቀሳውስትና ጳጳሳት በአብዛኛው ቁስ አካልነትን የሚቃወሙ ቢሆኑም እንኳን ቁስ ተኮር ግን ናቸው – ወይም የእርሱ ውግዘት ቁስ ተኮር ከመሆናቸው ጋር የተያያዘ ነው ።

ይህ ማለት ግን ሁለቱ ትርጉሞች ለየቅል ናቸው ማለትም አይደለም ። በአንድ ስም መጠራታቸውም በአጋጣሚ የሆነ አይደለም ። እነዚህ ሁለት ትርጉሞች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች እንኳን ባይሆኑ በጠነከረ ገመድ የተያያዙ መሆናቸውና አንዱ ባለበት ሌላውም መገኘቱ እንደማይቀር ታሪክም አመክንዮም ይነግሩናል ።

እነ ማርክስ በኖሩበት ዘመን ቁስ አካላዊነት በሁለቱም ትርጉሞቹ በአውሮፓ ውስጥ ገኖ እና ሰፍኖ ነበር ። ከላይ ዶስቶየቭስኪ እና ኤንግልስ የታዘቡት የመከራ ዓለም የኢንዱስትሪ ዐብዮት የተባለው ሁነት ውጤት ነበር ። ይህ አገላለጽ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተደረጉ እና ከእነሱ ቀጥለው ለተደረጉ ሌሎች እርምጃዎች መሠረት ሆነዋል ተብለው የሚታሰቡ የቴክኖሎጂ እመርታዎችን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ነው ። ከእነዚህ እመርታዎች የተነሣ ነገሮችን የማምረት ሒደት ከዚያ በፊት እንደነበረው የሰዎች ጊዜ ፣ ጉልበት እና ጥበብ እንዳይፈልግ ሆነ ። ይልቁንም ከእንፋሎት ፣ ከውሃ ፣ ከድንጋይ ከሰል ወዘተርፈ የሚመነጭ ጉልበትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ብዙ ምርት ማምረት የሚችሉ ማሽኖች እንዲፈለሰሙ እና በእነርሱ አማካይነት የምርት ሒደቱ በቀላሉ እንዲሰፋ እና እንዲዳብር ሆነ ። በእነ ማርክስ አገላለጽ የከበርቴ እና የሠራተኛ “መደቦች” እንዲፈጠሩ ምክንያት የሆነውም ይኸው ዐብዮታዊ ሁነት ነው ።

ነገር ግን ጥቂት የቴክኖሎጂ እመርታዎች ብቻ አልነበሩም ይህ ዐብዮት እንዲካሔድ ምክንያት የሆኑት ። ምክንያቱም እመርታዎቹ መደረጋቸው በራሱ ወደ ምርት አይመራም ። ብዙ ጊዜ ፈጠራዎቹ አንድን ነገር ታሳቢ አድርገው እንጂ በተለያዩ ዘርፍ ላሉት ችግሮች ሁሉ መድኃኒት ለመሆን አይደለም የሚፈጠሩት ። አንድም ከማምረቻ መንገዱ ሌላ የሚመረተው ምርት ጥሬ ዕቃም ለሒደቱ አስፈላጊ ስለሆነ በቂ ጥሬ ዕቃ በሌለበት ቴክኖሎጂው ቢኖርም ስፋት ያለው ምርት ሊመረት አይችልም ። ዳግመኛም እነዚህ ነገሮች ሁሉ ቢሟሉ እንኳን ብቻቸውን ወደ ምርት ዐብዮት ሊመሩ ባልቻሉ ነበር ። ምክንያቱም የማምረት አቅም መኖሩ ብቻውን ለማምረት በቂ ምክንያት አይደለም ። አምራቹ የማምረት ወጪውን ሸፍኖ ትርፍ እንዲያገኝ ምርቱ ፈላጊ ሊኖረው ይገባል ። ለምርት ዐብዮቱ መሳካት አንዱ ምክንያትም የዚህ ፈላጊ ፣ የሸማቹ መገኘት ነበር ። ሰፊ ምርት እንዲመረት ፣ ሰፊ ሸማች መኖር ነበረበት ። ይህ ሸማች በ18ኛው መቶ ምዕት ዓመት ብቅ በአውሮፓ ብቅ አለ ። ምናልባት ከዚያም በፊት ነበረ ይሆናል መኖርስ ፣ ለአካለ መጠን የደረሰው ግን በዚህ ዘመን ነበር ።

“‘There was a consumer revolution in eighteenth century England. More men and women than ever before in human history enjoyed the experience of acquiring material possessions . . . The consumer revolution was the necessary analogue to the industrial revolution, the necessary convulsion on the supply side.’ What in the past had been seen as luxuries now became ‘decencies’ and what had been ‘decencies’ now became necessities. (Work by several scholars) has shown how eighteenth century Britain, and especially eighteenth-century England, was increasingly gripped by a rage for spending which transformed the economy. As Plumb observed, ‘to spend has been the rising chord of Western capitalism’ and ‘aggressive consumption lies at the heart of successful bourgeois society.’ The concept of the classless customer who was always right took hold, as Adam Smith recognized in The Wealth of Nations in 1776: ‘consumption is the sole end and purpose of all production; and the interests of the producer ought to be attended to, only in so far as it may be necessary of promoting that of the consumer. The maxim is . . . perfectly self-evident.”[3]

በዚህ ምንባብ ውስጥ ጸሐፊው የኢንዱስትሪ ዐብዮት ከሌሎች ሀገራት ይልቅ ለምን በእንግሊዝ ተጀመረ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው የሞከረው ። ነገር ግን የኢንዱስትሪ ዐብዮቱ ወደ መላው አውሮፓ በተስፋፋበት መጠን ይህ የቁስ አካላዊነት ባሕልም እንዲሁ የመላው አውሮፓ መገለጫ መሆኑ አልቀረም ። ይህ ዐዲስ የሸማችነት ባሕል ማኅበረሰቡ ውስጥ ቁስ ተኮርነት እንደዳበረ እና የማሀበረስቡ ዐቢይ አንቀሳቃሽ ኃይል መሆኑን የሚያሳይ ነው ። ይህ ቁስ ተኮርነት ነው ለቴክኖሎጂ እመርታዎቹ እና ለምርቱ መስፋፋት ፣ በጠቅላላ ለምርት ዐብዮቱ ገፊ ምክንያት የሆነው ።

ጆሴፍ ቮን ሶነንፌልስ የተባለው በ18ኛው ምዕት ዓመት የኖረ የፖለቲካ ምሁር የሕዝብ ብዛት መጨመር ለምን የአንድ ሃገር ፖለቲካዊ ግብ መሆን እንዳለበት ሲያስረዳ ምክንያት ያደረገው ቁሳዊ ምቾትን እና አካላዊ ደኅንነትን ለማሳደግና ለማስጠበቅ ይረዳል የሚል ነበር ። እነዚህ ሁለት ነገሮች እንደ ሶነንፌልስ ከሆነ “ሁለቱ የማኅበረ ሰብእ ዐበይት ግቦች” ናቸው[4] ። ሶነንፌልስ “የአብርሆታዊው” ዘመን ሰው ነበር ። ስለ ማኅበረ ሰብእ ግብ ያለው አመለካከትም ከዘመነ አብርሆት እሳቤ መነሻዎች የተቀዳ ነበር ።

በኢኮኖሚክስ (ትንሽ አውቃለሁ ስለዚህ ዘርፍ) ‘Maximizing’ የሚባል ነገር አለ ። የተወሳሰበ ነገር አይደለም ። በጠቅላላው ሕይወት ላይ ወይም ደግሞ አንድን ተግባር ስናከናውን ፣ የተወሰኑ ነገሮች ላይ (ብዙዎቹ ነገሮች ላይ ፣ እውነት ለመናገር) ቁጥጥር የለንም – እንደተሰጡን ተሰጥተውናል እንጂ ልንጨምራቸው ወይም ልንቀንሳቸው አንችልም ። የተወሰኑ ነገሮች ላይ ደግሞ ቁጥጥር አለን ። ነገር ግን ልንቆጣጠራቸው የምንችላቸው ነገሮችም ላይ ቢሆን ፍጹም ቁጥጥር የለንም ። አንደኛውን ነገር ለመጨመር ብንፈልግ ሌላኛውን ነገር መቀነስ ይኖርብናል ። ስለዚህ ከእነዚህ ተለዋዋጭ ነገሮች መካከል የምርጫ ቅደም ተከተል ማድረግ ይኖርብናል ማለት ነው ። በቅደም ተከተል ካስቀመጥናቸው በኋላ አንዱን ወይም ሁለቱን መርጠን ‘Maximize’ እናደርጋለን ። ማለትም የመረጥነውን ነገር ለማብዛት ሌሎቹን ነገሮች መሥዋዕት እናደርጋቸዋለን ።

ሶነንፌልስም እያለን ያለው ለእነዚህ ሁለት ግቦች – ቁሳዊ ምቾትና አካላዊ ደኅንነት – ሲባል ሌሎቹ ነገሮች ሁሉ ይሠዋሉ ነው ። ‘Maximze’ የምናደርገው እነዚህን ሁለት ነገሮች ነው ። በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የምርት ዐብዮት መፈጠሩ እና ለዚህ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች መበራከታቸውም በትክክል ይህኑ የሚያረጋግጥልን ነው ። የአውሮፓ ማኅበረሰብእ ያሉትን ስጦታዎች ሁሉ የሰው ጉልበት እና የማሰብ አቅም ፣ መሬት ፣ ንብረት ፣ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ወዘተርፈ ምርትን ለማበራከት ፣ ቁሳዊ ምቾትንም ለማደላደል መሥዋዕት አድርጓቸዋል ። ‘ገንዘብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናል’ እንደተባለ ፥ የአንድ ማኅበረ ሰብእ ልብ በየት እንዳለ ለማወቅ ገንዘቡ በየት እንዳለ ማወቅ በቂ ነው ።

ገንዘቡ የት እንዳለ ባናውቅ ኖሮ ራሱ ግን የዚያ ማኅበረሰብእ ልብ የተሠወረ አልነበረም ፤ በሳይንቲስቶቹ እና በፈላስፋዎቹ የተገለጠ ነበር እንጂ ። እንዲያውም በዘመኑም ሆነ በኋላ የመጡት ምሁራን በዚያ ዘመን በእነዚህ ዘርፎች የተደረገው እርምጃ ከጥንቱ የመፍጠን ያህል ሳይሆን ከጨለማ ወደ ብርሃን የማለፍ ያህል ዐብዮታዊ እንደነበረ ስላሰቡ ዘመኑን “ዘመነ አብርሆት” ብለው ጠሩት ። የዚህን ብርሃን ምንነት አንድ ታሪክ ጸሐፊ እንደሚከተለው ነበር ያጠቃለለው ።

“The basic idea underlying all the tendencies of Enlightenment was the conviction that human understanding is capable, by its own power and without recourse to supernatural assistance, of comprehending the system of the world and that this new way of understanding the world will lead it to a new way of mastering it.”[5]

እኔ ስለዚህ ጉዳይ የማስበውን ልተወው ። ለማርክስ እና ለኤንግልስ ግን ይህ ሐሳብ መሠረታዊ ነበር ። እነሱ ራሳቸው ይህን ነበር ለማሳካት የተነሡት ። በመጨረሻም የሰው ልጅ የዓለምን አሠራር እና አካሔድ መረዳት በመቻሉ ከማመን አልፈው እነሱ ራሳቸው – ማርክስ እና ኤንግልስ – ፍጹም የሆነው መረዳት ላይ “ደረሱ” ።ለፕላስ የተባለ ፈረንሳዊ የሒሳብ ሊቅ እና የቁስ አካላዊነት አቀንቃኝ ያለውን አብነት ብናደርግ – ፍልስፍናዊ ቁስ አካላዊነት ምን ያህል ከእነ ማርክስ አካሔድ ጋር የሠመረ እንደሆነ ለመረዳት ያግዘናል ።

“We ought then to regard the present state of the universe as the effect of its anterior state and as the cause of the one which is to follow. Given for one instant an intelligence which could comprehend all the forces by which nature is animated and the respective situation of the beings who compose it – an intelligence sufficiently vast to submit these data to analysis – it would embrace in the same formula the movements of the greatest bodies of the universe and those of the lightest atom; for it, nothing would be uncertain and the future, as the past would be present to its eyes.”[6]

እንደ ማርክስ አባባል ከሆነ ሐሳቦች ሁሉ የማኅበረሰቡ ቁሳዊ ሁናቴ ውጤቶች ናቸው ፤ ከእነርሱ ሐሳቦች በስተቀር ። (በኋላ ማርክሳዊነት ተብለው የተጠሩት) የእነርሱ ሐሳቦች ግን ከሌሎች ሐሳቦች በተለየ ነባራዊ የሆነውን እውነታ የሚገልጡ ናቸው እንጂ የማኅበረሰቡ ሁኔታ ሲለወጥ የሚለወጡ እና የሚተኩ አይደሉም ። ይልቁንም የቁሳዊውን ሁኔታ የመለዋወጥ ሕጎች የሚያስረዱ ናቸው ። ግልጽ ባልሆነ ምክንያት (ምናልባትም ለፕላስ እንዳለው ወደር በሌለው የማሰብ ክሂላቸው የተነሣ) ማርክስና ኤንግልስ ብቻ ቁሳዊ ሁኔታዎቻቸው ሳይገድቧቸው ፣ ከዘመናቸው ከፍ ብለው የሰውን ልጅ መነሻ እና መድረሻ ለመመልከት “በቅተዋል” ።

የዘመነ አብርሆት ጠቅላላ መንፈስ ፣ ለፕላስ እና ማርክስ በዚህ መጠን ስምሙ መሆናቸው አስገራሚ አይደለም ። ሁሉንም የሚያያይዛቸው አንድ ክር አለ ፤ ይኸውም ቁስ ተኮርነታቸው ነው ። ምንም እንኳን ማርክስ በግል አነዋወሩ ቁስ ተኮር ባይሆንም ፣ የፍልስፍናው ምንጭ ግን የኖረበት ቁስ ተኮር ባሕል ነበረ ። በለፕላስ እና በሌሎችም የተገለጠው እና በማርክስ ተቀባይነት ያገኘው ( ዝርዝሩ ላይ ልዩነቶች ባይጠፉም ቅሉ) ዘመናዊው የቁስ አካልነት ፍልስፍና ልክ እንደ ምርት ዐብዮቱ ሁሉ የአውሮፓ ማኅበረሰብእ ያዳበረው ቁስ ተኮር ባሕል ውጤት ነው ።

ይህ ቁስ ተኮር ባሕል ራሱ ግን ከወዴት መጣ የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችል ይሆናል – መነሣቱም ተገቢ ነው ። እኔ ወደ ፕሮቴስታንታዊው “ተሐድሶ” እና እሱን ወደ አፈራው ካቶሊካዊ የነገረ መለኮት እሳቤ አማትራለሁ ። ነገር ግን ከነገራችን በጣም ርቀን እንዳንሔድ ወደ ዝርዝሩ አልግባ ። ዋናው ነጥብ የእነ ማርክስ ቁስ አካልነት የብራ መብረቅ አለመሆኑ ነው ። ይልቁንም ለረዥም ዘመናት ሲጠመቅ እና ሲፈላ የቆየ ቁስ አካላዊነት (በፍልስፍናውም ሆነ በባሕል ዘርፎች) ዝንባሌ መጎልመስ ነው ።

በዚህ አባባሌ ማርክስ እና ኤንግልስ ከአኔ ጋር እንደሚስማሙ አልጠራጠርም ። ለእነሱ “አብርሆታዊው” እሳቤ ፣ ቁስ አካልነትም ሆነ ቁስ ተኮር ባሕል እና አኗኗር መፈጠራቸው የሰው ልጅ ወደፊት የመራመዱ ማሳያ ናቸው ። መሆን ያለባቸው ነገሮች ናቸው ። ሌላው ቀርቶ በዚያ መጠን የሚያወግዙትን የከበርቴውን መደብ መፈጠር አይጠሉትም ። ወይም ጭቁኑን የሠራተኛ መደብ የፈጠረውን የምርት ዐብዮት አይጠሉትም ። ምክንያቱም ‘አብርሆታውያን’ እንደመሆናቸው የሰው ልጅ ተፈጥሮን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይናፍቃሉና ። እንዲሁም ፣ ለእነርሱ የሰው ልጅ ከክርስትና እና ከሌሎች “ሃይማኖቶች” ቀንበር ነጻ ወጥቶ ወደ አመክንዮ እና ሳይንስ ብርሃን መድረሱ ፣ በዚያም ቁስ አካልነትን መረዳቱ እና መቀበሉ የተፈጥሮአዊ ፣ የዳያሌክቲካዊ ጉዞው አካል ነው ።

“When the ancient world was in its last throes, the ancient religions were overcome by Christianity. When Christian ideas succumbed in the 18th century to rationalist ideas, feudal society fought its death battle with the then revolutionary bourgeoisie. The ideas of religious liberty and freedom of conscience, merely gave expression to the sway of free competition within the domain of knowledge.

“‘Undoubtedly’, it will be said, ‘religious, moral, philosophical and juridical ideas have been modified in the course of historical development. But religion, morality, philosophy, political science, and law, constantly survived this change.’

“‘There are, besides, eternal truths, such as Freedom, Justice, etc. that are common to all states of society. But communism abolishes eternal truths, it abolishes all religion and all morality, instead of constituting them on a new basis; it therefore acts in contradiction to all past historical experience.’

“What does this accusation reduce itself to? The history of all past society has consisted in the development of class antagonisms, antagonisms that assumed different forms at different epochs.

“But whatever form they may have taken, one fact is common to all past ages, viz., the exploitation of one part of society by the other. No wonder, then, that the social consciousness of past ages, despite all the multiplicity and variety it displays, moves within certain common forms, or general ideas, which cannot completely vanish except with the total disappearance of class antagonisms.

“The communist revolution is the most radical rupture with traditional property relations; no wonder that its development involves the most radical rupture with traditional ideas.”[7]

ስለዚህ በጊዜው የሰው ልጅ የቁስ አካልነትን ብርሃን ወደ ማየት ደረሰ ። ይሁን ። ማርክስ እና ኤንግልስም እንዲሁ በዚህ ብርሃን ተመርተው ፣ እዚህ ተራራ ላይ ቆመው የተስፋይቱን ምድር ተመለከቱ ። ለምን ቁስ አካላውያን እንደሆኑ ተረዳን ። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ያልተመለሰ ጥያቄ አለን ። ይህ ሁሉ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ እና አይቀሬ እርምጃ አካል ከሆነ ማርክስ እና ኤንግልስ ከበርቴውን በእጅጉ የሚጠየፉበት እና ለሠራተኛው የሚቆረቆሩበት ምክንያት ምንድነው ? መምጣቱ የማይቀረውን ኮሚዩኒስት ሥርዓተ ማኅበር በመናፈቅ የመጠባበቃቸው ምሥጢር ምንድነው ? ማርክስ እና ኤንግልስ በማኒፌስቶአቸው የታሪክን ምንነት ፣ መነሻውን እና መድረሻውን ቢገልጡልንም ፣ እነርሱ ትህን ሁሉ ለማወቅ እና ፍጻሜውን ለማፋጠን ምን እንደሚያነሣሳቸው ግን አልነገሩንም ። ቶም ሆላንድ የተባለው እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊ ማርክስ ላይ የሚታየውን ይህን ተጣርሶ እንዲህ ይገልጠዋል ።

“Dispassion was a tone that – despite his efforts – (Marx) found impossible to maintain. The revulsion that he so patently felt at the miseries of artisans evicted by their landlords to starve on the streets, of children aged before their years by toiling night and day in factories, of labourers worked to death in distant colonies so that the bourgeoisie might have sugar in their tea, made a mockery of his claims to have outgrown moral judgements. Marx’s interpretation of the world appeared fuelled by certainties that had no obvious source in his model of economics. They rose instead from profounder depths. Again and again, the magma flow of his indignation would force itself through the crust of his scientific-sounding prose. For a self-professed materialist, he was oddly prone to seeing the world as the Church Fathers had once done: as a battleground between cosmic forces of good and evil. Communism was a ‘spectre’: a thing of awful and potent spirit. Just as demons had once haunted Origen, so the workings of capitalism haunted Marx. ‘Capital is dead labour which, vampire-like, lives only by sucking living labour, and lives the more, the more labour it sucks.’ This was not the language of a man emancipated from epiphenomena. The very words used by Marx to construct his model of class struggle – ‘exploitation’, ‘enslavement’, ‘avarice’ – owed less to the chill formulations of economists than to something far older: the claims to divine inspiration of the biblical prophets. If, as he insisted, he offered his followers liberation from Christianity, then it was one that seemed eerily like a recalibration of it.”[8]

የቶም ሆላንድ መጽሐፍ ዋና ዓላማው ምንም እንኳን ከዘመነ አብርሆት ጀምሮ የተቀነቀነው ምዕራባዊው ዓለም በክርስትና የተነሣ ለረዥም ዘመናት ጨለማ ውስጥ የመቆየቱን እና “በኋለኛው ዘመን” በሳይንስ እና በአመክንዮ ነፃ የመውጣቱን እና ብርሃን የማየቱን ትረካ ለመገዳደር ነው ። እንደ ቶም ሆላንድ አባባል ምዕራባዊው ዓለም ክርስትናን ሲክድ ራሱ ከክርስቲያናዊ መርሖችና አስተምህሮዎች በመነሣት ነው ። አንዳንዶቹ የክርስትና መርሖች በእጅጉ ጠልቀው ከመቀበራቸው የተነሣ ከክርስትና የተገኙ ሳይሆኑ በተፈጥሮ የተሰጡ እንደሆኑ ተደርገው ይታሰባሉ ። አንዳንዴ መኖራቸው ጭምር ሳይታወቅ የማኅበረሰቡን አቅጣጫ ግን ይበይናሉ ። ስለዚህ ‘ክርስቲያን መሆናችን ቢያበቃም ግን የክርስትናን ውለታ መርሳት የለብንም ፤ የበላንበትን ወጭት ብንጥለው እንኳን አንስበረው’ የሚል ዓይነት ሐሳብ ነው ። ይህ ሐሳብ አሁን አሁን በተለይ በወግ አጥባቂ ምሁራን እና ፖለቲከኞች አንጻር ተቀባይነቱ እየጨመረ ነው ። አንዳንድ ሰዎች ሥልጣኔውን ለማስቀጠል አስፈላጊ ሆነው ስላገኙት ተጠምቀው “ክርስቲያን” እየሆኑ ጭምር ነው ። ምንም እንኳን በዚህ መንገድ መታሰቡና መገመቱ ለክርስትና ስድብ ቢሆንም ግን ታሪካዊ አስተውሎቱ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ ።[9]

ማርክስን እና ማርክሳውያንን በተመለከተ ይህ “ክርስቲያናዊ” ጠባይዓቸው ባለፈው ክፍል እንዳነሣነው በሁለት ዋና መንገዶች ይገለጣል ። የመጀመሪያው ሞራላዊነታቸው ሲሆን ሌላኛው ዐብዮቱን እና ተከትሎት የሚመጣውን መደብ አልባ ኅብረተሰብእ የማየት ናፍቆት እና እነዚህ ሁለት ነገሮች እንዲሆኑ ዋጋ የመክፈል ፈቃደኝነትና ጉጉት ናቸው ። እነዚህ ሁለት የማርክሳዊነት ጠባይዖች ከማርክሳዊ ቁስ አካላዊነት ጋር ከመጋጨታቸው እና ሊታረቁ ካለመቻላቸው በተጨማሪ በእጅጉ “ክርስቲያናዊ” መሆናቸው አስገራሚ ነው ። በተለይ ማርክሳውያን በጠቅላላው “ለሃይማኖት” በተለይ ደግሞ ለክርስትና ያላቸውን የታወቀ ጥላቻ ከግምት ውስጥ ስናስገባ ።

‘ክርስቲያናዊ’ የሚለውን ቅጽል በሙሉ ልብ መጠቀሙ አስቸጋሪ ነው ። በአንድ በኩል እነዚህ የማርክሳዊነት ገጾች ከክርስትና አስተምህሮ መወሰዳቸው ጥያቄ የለበትም ። በሌላ በኩል ግን ከክርስትና ተነጥለው ሲወሰዱ በክርስትና አስተምህሮ እና ሕይወት ውስጥ ያላቸው ትርጉም ስለሚለያቸው ክርስቲያናዊ ብሎ መጥራቱ ትክክል አይሆንም ። ለዚህ ነው ቃሉን በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ ማስቀመጥን የመረጥሁት ።

ዶስቶየቭስኪ የመጨረሻ መጽሐፉ (The Brothers Karamazov) ውስጥ ሶሻሊዝምን የተመለከተች አንዲት ልባዌ አለችው ።

“For socialism is not merely the labor question, it is before all things the atheistic question, the question of the form taken by the atheism today, the question of the tower of Babel built without God, not to mount to heaven from earth but to set up heaven on earth.”[10]

በዚህች ልባዌ ውስጥ ዶስቶየቭስኪ ቢያንስ ሦስት ቁም ነገሮች ያቀብለናል ። የመጀመሪያው ሶሻሊዝም ከክርስትና ጋር ያለው “ዝምድና” ነው ። በቂ ብለንበታል ይህን – ለጊዜው ። ሁለተኛው ሶሻሊዝም እግዚአብሔርን ከመካድ (Atheism) ጋር ያለው ዝምድና ነው ፤ ዝምድና ብቻ ሳይሆን የሶሻሊዝም ዋና ይዘቱ ኢአማኒነት መሆኑ ነው  ። ሦስተኛው ደግሞ ሶሻሊዝም  “ሰማይን ወደ ምድር ለማውረድ” የሚደረግ ሙከራ መሆኑ ነው – ማለትም ከክርስትና ጋር ባለው ዝምድና እና ከእግዚአብሔርን ከመካድ ጋር ባለው ዝምድና መካከል ያለው ግጭትና ውጥረት ።

በክርስትና ነገረ ሃይማኖት ‘Eschatology’ የሚባል ነገር አለ ። ነገረ ምጽአት ተብሎ ሲተረጎም ሰምቻለሁ ፤ ግን ምናልባት “ተምኔተ መንግሥተ ሰማያት” እና ‘ሱታፌ መንግሥተ ሰማያት’ የሚሉትን ቃላት ዓውድ እየለዩ መጠቀም ሳይሻል አይቀርም ። በኦርቶዶክሳዊው ነገረ ሃይማኖት ይህ አንድ የአስተምህሮ ዘርፍ ሳይሆን ሁሉንም አስተምህሮዎች የሚቃኝ የጠቅላላው አስተምህሮ መንፈስ ነው ሊባል ይችላል ።[11] በአጭሩ ሲብራራ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሳያቋርጡ መሻት ፣ መፈለግ እና መናፈቅ ሊባል ይችላል ። ነገር ግን በመፈለግና በመናፈቅ ብቻ የሚያበቃም አይደለም ። “መንግሥተ ሰማያት በመካከላችሁ ናት” ብሎ ጌታችን እንዳስተማረ ለክርስቲያኖች ምንም እንኳን የመንግሥተ ሰማያት ፍጻሜዋ (መገለጧ) በጌታችን ዳግም ምጽአት ቢሆንም አሁንም በመካከላችን አለችና በእውነት ለፈለጓት ትገኛለች ። ስለዚህም ከመፈለግ አልፎ ከእርሷ መቅመስ ፣ ከእርሷ መሳተፍንም ይመለከታል ።

ታዲያ ማርክሳውያን ሞራላዊነታቸውን ፣ የፍትሕ ጥማታቸውን ሳያስቡት ከክርስትና እንዳገኙት ሁሉ ፥ ለዐብዮቱ እና ለመደብ አልባ ማኅበረ ሰብእ ያላቸውን ጉጉት እና ናፍቆትም በክርስትና ካለው እና ወደ ማኅበረሰቡ በእጅጉ ከሠረገው ተምኔተ መንግሥተ ሰማያት የተወረሰ ሆኖ ይገኛል ። ኮሚዩኒዝም ይህን የክርስትናን መንግሥተ ሰማያትን ፥ የነገሮችን ፍጻሜና ሙላት የመጠባበቅ ፣ የመጠባበቅ ብቻም ሳይሆን አሁን እና እዚሁ የመለማመድ – ማለትም ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት የመመላለስ ልምምድ – ይወርስና ግን ዶስቶየቭስኪ እንደሚለው ከቀድሞ ሥሩ ነቅሎ ሌላ ሥር ላይ ይተክለዋል ፤ ከተገኘበት ዐውድና ማዕከል ነጥሎ ሌላ ዓውድና ማዕከል ይሰጠዋል ። መልኩም እንዲሁ ጨርሶ ሌላ ይሆናል ። አሌግዛንደር ሽሜማን ጥሩ አድርገው እንደገለጹት ፥

“The most ironic and probably the most tragic development of all “Christian” history is the strange mutation of the eschatological world-view from the Church into the secular culture . . . From the medieval sects and “revivals” through the Rainessance, enlightenment, Rationalism, Romanticism, and the social and political utopias of the 19th century, the idea of the Kingdom stood at the center of the secular mind, but a Kingdom, and here lies the tragedy, progressively deprived of its King, more and more identified with “this world” as such.

A secularized eschatology, a faith in the immanent fulfillment by man of his dreams and aspirations, a belief in “history”, “Justice”, “freedom” and other pseudo-absolutes – such was, such still is, the secular faith of the secular man. A faith which miraculously survives and overcomes whatever wave of pessimism and disillusion shakes it at more or less regular intervals.”[12]

ለሽሜማን የምዕራባዊው ዓለም ጉዞ ቀስ በቀስ ከክርስትና መሠረቶች የመፋታት ነገር ግን የክርስትናን ዕሴቶች እያዛባ እና ከመሠረታቸው ነቅሎ እየወሰደ ቀድሞ እንደተሰጡት እግዚአብሔርን ሊያገለግልባቸው ሳይሆን ራሱን ሊያገለግልባቸው ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊደርስባቸው ሳይሆን የራሱን አገዛዝ በምድር ላይ ሊያቆምባቸው የመሞከር ነው ። ማርክሳዊነትም የዚህ አንድ መልክ ነው ።

ጌታችን በምድረ በዳ በተፈተነ ጊዜ የቀረቡለት ፈተናዎች በአንድ ቃል ቢጠቃለሉ – ቁስ አካላዊነት – ሊባሉ የሚችሉ ይመስለኛል ። ሰይጣን ጌታችንን ድንጋዩን ወደ እንጀራ በመለወጥ ረሃቡን እንዲያስታግስ ፣ ወይም ለእርሱ ሰግዶለት የዓለምን መንግሥታት ሁሉ እንዲሰጠው ፣ አሊያም ራሱን ከቤተ መቅደስ ላይ እንዲወረውር እየጋበዘ ሲፈትነው በእግዚአብሔር ፋንታ የሰውነቱን ፍላጎቶች በራሱ ላይ እንዲያነግሣቸው ነበር እየጠየቀው ያለው ። ቁስ አካላዊነት ማለትም ይኸው ነው ። ዳግመኛም ጌታችን ‘ሃብታም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ ይቀላል ።’ ሲልም የቁስ አካላዊነት ዝንባሌ በሰው ላይ ያለውን ኃይል እየገለጠ ነው ።

ለአንድ አፍታ ቅድም ወዳነሣናቸው የቁስ አካላዊነት ሁለት ትርጉሞች እንመለስ ። አንድ ሰው ቁስ አካላዊነትን እንደ ፍልስፍና ሲቀበል ፣ ለቁሳዊ ሁኔታው ቅድሚያ መስጠቱ ይጠበቃል ። ነገር ግን የተገላቢጦሹ እውነት ሆኖ ይገኛል ለማለት በጣም ያስቸግራል ። አንድ ሰው ፍልስፍናው ቁስ አካላዊነትን የሚቃወምና የሚጠየፍ ሆኖም ሳለ ለቁሳዊ ነገሮች ትኩረት እና ቅድሚያ የመስጠት ዕድሉ በጣም ሰፊ ነው ።

ግን ይህ ሁለተኛ ተቃርኖ እንደ መጀመሪያው ተቃርኖ አስገራሚ አይመስለኝም ። በሁሉም ዓይነት ርእዮተ ዓለም – ሌላው ቀርቶ ሥጋ እና ቁስ የክፋትና የጥፋት ምንጭ ተደርገው በሚሳልባቸው ሳይቀር ፣ የሰው ልጅ ሥጋዊ ፣ ቁሳዊ ተፈጥሮ እና ፍላጎት የተስተዋለ እና የታመነ ነው ። እንደ ኤፒከረስ ይህን ፍላጎት በተቻለ መጠን የማርካት ፍልስፍና ያላቸውን ወደ ጎን ትተን ፣ ይህን ፍላጎት ለመግታትና ለመቆጣጠር የሚሹት ላይ ብናተኩር ፥ ይህ ዓይነቱ ትግል ለማሸነፍ በእጅጉ የሚከብድ ፣ ምናልባትም የማይቻል ሆኖ እናገኘዋለን ።ስለዚህ ይህን ፍላጎታቸውን ለመቆጣጠር እየፈለጉና እየሞከሩ ሳይሳካላቸው ስለሚቀር ከሞላ ጎደል ሁሉም ሰዎች ከጥንት ጀምሮ እምነታቸውና ድርጊታቸው እየተጋጨባቸው መኖራቸው ያን ያህል አስገራሚ አይሆንም ።

በክርስትናም ቢሆን ይህ ትግል ከጥንት ጀምሮ ይስተዋላል ። ጌታችን በምድረ በዳ ሰይጣንን ድል መታው ። ፈተናው ግን አላበቃም ። ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ይህኑ ፈተና ስትፈተን አለች ። ይህን ፈተና በመውደቋ ነበር ዶስቶየቭስኪ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የወቀሳት ። በሮምና በግዛቶቿ የሰው ልጅ የጉዞ አቅጣጫ ተቀየረ ።

ይህን ጽሑፍ ስጽፍ የአውሮፓን ታሪክ በተመለከተ የተሻለ ግንዛቤ ለማዳበር በከፊል ያነበብኋቸው ሁለት መጻሕፍት ነበሩ ። አንደኛው ‘The pursuit of Glory’ ይባላል ፤ ሌላኛው ደግሞ ‘The pursuit of Power’ ። የአውሮፓን “አብርሆታዊ” ጉዞ ሲገልጡ ነው ይህን ማለታቸው ። ‘ኃይልን እና ክብርን ፍለጋ’ ። ‘አባታችን ሆይ . . .’ ብለን ስንጸልይ ማብቂያችን ‘መንግሥት ያንተ ናትና ፥ ኃይልም ክብርም’ የሚል ነው ። አውሮፓ ግን ኃይልን እና ክብርን ራሷ ልትፈልጋቸው ሔዳለች ። ‘ዘመነ አብርሆት’ ማለት ሌላ ሳይሆ የዚህ ፍለጋ መታወጅ ነው ።[13]

ማርክስ እና ኤንግልስ ሰው ተፈጥሮ ላይ ይነግሥባታል ፣ የታሪክ ግብም ይህ ነው ከማለታቸው ጋር አልስማማም ። ነገር ግን እንዲህ በማለታቸው የምዕራባዊውን ሥልጣኔ ግብ በትክክል ገልጸውታል ። ዋናው ነገር ቁስ አካል ፣ ዋናው ነገር ምርት ነው በማለታቸውም አልስማማም ። ነገር ግን የምዕራባዊውን ዓለም መነሻ እና የዘመናቸውን እውነታ በትክክል ገልጸውታል ። ይህም በመሆኑ ድኅረ አብርሆት በምናውቀው ምዕራባዊ ሥልጣኔ ሁሉም ነገር ፣ ሁሉም የሕይወት ዘርፍ ይህን የቁስ አካላዊነት መነሻ የተቀበለ ነው ። በወጣትነታቸው ማርክሲስት የኢኮኖሚ ሊቅ የነበሩት እና በኋላ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቄስ እና የነገረ ሃይማኖት ሊቅ የሆኑት ሰርጌይ ቡልጋኮቭ ይህን እውነታ እንዲህ አብራርተውታል ።

“Our time understands, feels, experiences the world as a household, and human power is measured in terms of wealth. In contrast to the voluntary or involuntary asceticism of Franciscan or Buddhist epochs of history, which despise wealth and deny its power over man, our epoch loves wealth—not money, but specifically wealth—and believes in wealth even more than it believes in the individual. This is not merely mammonism, low and selfish (which exists now as it has existed in all times); no—this is economism. Life is, above all, an economic process: such is the axiom of this contemporary economism, expressed in most extreme and even provocative form in economic materialism. This is why economic materialism has such survival power, combined with the appeal of ideological radicalism, its sharpness actually increased by its naivete and immediacy.”[14]

ቡልጋኮቭ ይህን የጻፉት ከሩሲያ “ዐብዮት” በፊት ነበር ። ነገር ግን ይህ እሳቸው ኢኮኖሚዝም (ኢኮኖሚያዊነት) ብለው የጠሩት ሐሳብ – ሕይወት ከምንም በላይ ኢኮኖሚያዊ ሒደት ናት የሚለው እምነት – አሁንም ገዢ ነው ። አሁንም የማይጠየቅ ነው ። እንዲያውም እጅግ ሥር ከመስደዱ የተነሣ – መኖሩ ራሱ አይታወቅም ።

እዚህ ጋ እኛም መልሳችንን እናገኛለን ። ይህን ጽሑፍ ከጀመርሁ ጀምሮ – “ከዐብዮቱ” በኋላ በሚደረጉ ተዋሥኦዎች ውስጥ ዐብዮታዊው ትውልድ አንግቦ የተነሣውን ርእዮት መሠረቶች ያልተመረመሩት እና ያልተጠየቁት ለምንድነው ? እያልሁ ስጠይቅ ቆይቻለሁ ። በጉዳዩ ላይ ዐበይት ከሚባሉት መጻሕፍት መካከል የተወሰኑትን መርጬ ከውስጣቸው እየጠቀስሁ – ይህን ተግባር (መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሣትን) የሚሸሹት ለምንድነው እያልሁ ሳማርር ቆይቻለሁ ። አሁን ግን መልሳችንን አግኝተናል ። ምክንያቱ በማርክሳዊነታቸው የያዙትን የኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነት መሠረት አሁንም ስላልተዉት ነው ። አሁንም ቢሆን እንደያኔው – ዋናው ነገር ኢኮኖሚያዊ ደኅንነት መሆኑን ያምናሉ – የሚጠየቅ ነገርም ሆኖ አይታያቸውም ። ለዚህም ነው  ጥያቄውን የሚሸሹት የሚመስሉት ፤ ግን እውነታው ወዲህ ነው – ጥያቄው በእነሱ ዘንድ ህላዌ የለውም ።

ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነትን የተቀበሉት ከማርክሳዊነት ጋር ከነበረ – በኋላ ማርክሳዊነትን ሲተዉት – እሱንም አብረው መተው አልነበረባቸውም ? ለምንድነው የማርክሳዊነትን “ሳይንሳዊ” ትንተና እና “ጽንፈኝነቱን” (ወይም ሞራላዊ ስሱነቱን እና ምጽአታዊ ሥሪተ አእምሮውን) ሲተዉአቸው – ኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነቱን ግን ይዘውት የቀጠሉት ?

መልሱ ቀላል ነው ። ምክንያቱም ኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነትን – ተማሪዎቹ ከነ ማርክስ አላገኙትም ። ማርክሳዊነትን ከመቀበላቸውም በፊት ይዘውት ነበር ። እነ ማርክስ የማርክሳዊነትን መሠረቶች ከማስቀመጣቸው በፊት ኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነት በመላው ምዕራባዊ ዓለም ሰፍኖ እንደነበረ ሁሉ – ተማሪዎቹም ማርክሳውያን ከመሆናቸው በፊት ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነትን ተቀብላ አቀብላቸዋለች ። ማርክሳዊነትን ለመቀበልም ቅርብ የሆኑት ከዚያ በፊት የነበራቸው የአእምሮ ሥሪት ከማርክሳዊነት መሠረታዊ እሳቤ ጋር ተመሳሳይ ስለነበረ ነው ።

በጽሑፎቻቸው ዐብዮታውያን ጓዶች አፄ ኃይለ ሥላሴን ወቃሽ ናቸው ። ወቀሳቸውም በዋናነት የዘመናዊነትን ጎዳና ቢጀምሩትም በበቂ ደረጃ አልሔዱበትም – ከጊዜው እኩል መራመድ አልቻሉም የሚል ነው ። አንድም ከእሳቸው መምጣት በፊት የነበረውን የተዛባ የምርት ግንኙነት ከማስወገድ ይልቅ በማስቀጠል እና እንዲያውም በማጠናከር ሰፊውን ሕዝብ በዝብዘዋል የሚል ነው ።

ሁለተኛውን ክስ ወደ ፊት በዝርዝር ለመመልከት አስባለሁ ። አሁን ካነሣነው ጥያቄ አንጻር ግን ስንመለከተው በተማሪዎቹ እና በአፄ ኃይለ ሥላሴ መካከል የተፈጠረው ግጭት – መሠረታዊ ስምምነት ያለበት ግጭት ነው ። እንደ እውነቱ ከሆነ – የተማሪዎቹ ጥያቄ መንግሥት ያስተማራቸውን እንዲኖር ፣ እንዲተገብር ነበር ። መንግሥት ራሱ ዋናው ነገር ኢኮኖሚያዊ ደኅንነት እና ብልጽግና እንደሆነ አስተምሯቸዋል ፣ የሰዎችን እኩልነትም እንዲሁ ። ዙሪያቸውን ሲቃኙ ግን ብዙው ሕዝብ በዚህ ረገድ – ዋናውን ጉዳይ – ምርትን –  በተመለከተ በእጅጉ የተጎዳ እንደሆነ ይመለከታሉ ። በሌላ በኩል እነሱን የሚያስተምሯቸው ሰዎች በዚህ ጉዳት ሲቸገሩ እና ሲማረሩ አያዩም ። እንዲያውም የዚህ ጉዳት አድራሽ እና አስቀጣይ ሆነው ይገኛሉ ። ስለዚህ ይህን የመርሕ እና ተግባር ልዩነት ለመድፈን የማርክስ እና የሌኒን መላ በቀረበላቸው ጊዜ – ራስ ወዳድነት ካልሆነ በስተቀር የማይቀበሉበት ምን ምክንያት ይኖራቸዋል ? ስለዚህም ከእነሱ ቀድመው የሩሲያ ወጣቶች እንዳደረጉት ሁሉ ክርስቲያናዊውን የሞራል ስሱነት እና ምጽአታዊ ሥሪተ አእምሮ በትምህርታቸው ካገኙት እና የማኅበረሰቡን ኑሮ ባረሰረሰው ኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነት መሠረት ላይ ይተክሉታል ።

“በመርሕ ደረጃ” ተማሪዎቹ ላይ መፍረድ አይቻልም ። በሔዱበት መንገድ እንዳይሔዱ ምን ይይዛቸው ነበር ? የማርክሳዊነትን ስበት በምን ሊቋቋሙት ይችሉ ነበር ። እኔ ከመጀመሪያውም ለዚህ ዕድል የተተዉ ነበሩ ባይ ነኝ ። እዚህ ጋ ከፕሮፌሰር ባሕሩ ጋር እስማማለሁ ።

“… viewed within the given global and national context, the rise of the Ethiopian student movement had an element of inevitability about it.”[15]

ግን መች ነው ይህ መውጫ የሌለው መንገድ የተተለመው ? መች ነው የትውልዱም ሆነ የሀገሪቱ እጣ ፈንታ የታተመው ? የኢኮኖሚ ቁስ አካላዊነትን መነሻ ለሚቀበሉ ሰዎች – “ከዐብዮቱ” በፊት የነበሩ አንዳንድ ሁነቶችን በመለወጥ ፣ ወይም “ዐብዮቱ” ከፈነዳ በኋላ አንዱ ወይም ሌላው ድርጅት እና ግለሰብ በተለየ መንገድ ተጉዞ ቢሆን ለውጥ ያመጣ ነበር ብሎ ማሰብ ቀላል ነው ። ምክንያቱም በእነዚህ ዘመኖች መነሻችን እና ግባችን – ኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነት – ትክክለኛ ስለነበር ። ለእነሱ የማርክሳዊነት ይዘት (ቁስ አካላዊ ኢኮኖሚያዊነቱ) ትክክል የነበረ ሲሆን – የሔደበት መንገድ ፣ “ጽንፈኝነቱ” (ምጽአታዊ ሥሪተ አእምሮውና የሞራል ስሱነቱ) ግን ጥፋትን አመጣ ።

እኔ ግን ይህን መነሻ የማልቀበል በመሆኑ በዚህ መንገድ መፍትሔ ይመጣ የነበረ መሆኑ አይዋጥልኝም ። ይልቁንም ወደር እና መሰል የሌለው ስሕተት የተሠራው – እጣ ፋንታችንም የታተመው – ይህን ፍልስፍናዊ መነሻ በተቀበልን ጊዜ መሆኑን አምናለሁ ። ‘መች ነው የተቀበልነው ?’ ይባል ይሆናል – ታሪካዊ ምርምር ይሻል – ግን በአንድ ጊዜ የሆነ ነገር እንዳልሆነ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል ። በሌላ አነጋገር “የዘመናዊነት” ታሪክ ብለን የምንጠራው ታሪካችን ማለት ነው ። “ዘመናዊነት” – የኢኮኖሚያዊ ቁስ አካልነት ሌላ ስም ነው ። “ዘመናዊነትንም አትቀበልም ?” ትሉኝ ይሆናል ። እኔም እንደ ማርክስ እና እንደ ኤንግልስ እመልሳለሁ “በዚህ ክስ ጥፋተኝነቴን እቀበላለሁ ።”

“ጽንፈኝነት” (radicalism) እንደ ችግር መታየቱንም አልቀበልም ። ተማሪዎቹን በተመለከተ በብዙዎች የሚቀርበው ቅሬታ እና ወቀሳ “ጽንፈኝነታቸው” ነው ። ይህ ለእኔ ፈጽሞ የሚዋጥልኝ ነገር አይደለም ። እንደኔ መረዳት ግን “ጽንፈኝነት” የሚባል ችግር የለም ። ተማሪዎቹ ጋር ሊኖር የሚችለው ችግር ሦስት ነው ። የሐሳብ ስሑትነት ፣ የመረዳት ውሱንነት ወይም ለሐሳብ እና ለመርሕ አለመታመን ። “ጽንፈኝነትን” እንደ ችግር የሚያነሡ ሰዎች “ጽንፈኝነት” ብለው የሚጠሩት ተማሪዎቹ ለተቀበሉት ርእዮት መታመናቸውን እና የርእዮቱን ግቦች ተከትለው “እስከ ጽንፍ” መሔዳቸውን ከሆነ በዚህ ፍረጃ ፈጽሞ ልስማማ አልችልም ።

እኔ በበኩሌ ተማሪዎቹ ያደረጓቸውን ነገሮች ከርእዮታቸው በመነሣት ለእርሱ በመታመን እስካደረጉት ድረስ የዚያ ርእዮት ሰለባ በመሆናቸው ባዝን እና የርእዮቱን መሠረት ከልብ ባለመጠየቃቸውና ባለ መረዳታቸው ብወቅሳቸውም ፣ “በጽንፈኝነት” ግን አልከሳቸውም። እንዲያውም ለርእዮታቸው በመታመን እስከተጓዙበት ርቀት ድረስ አድናቆቴ ይከተላቸዋል ።

ርእዮቱን የተከተሉ መስሏቸው ከርእዮቱ መነሻዎች ጋር የሚቃረኑ ድርጊቶች ፈጽመው እንደሆነም (ቅራኔው ራሱ ርእዮቱ ውስጥ ያለ እስካልሆነ ድረስ) ለመረዳታቸው ውሱንነት እንወቅሳቸዋለን ። ነገር ግን ይህ የመረዳት ውሱንነት “ጽንፈኝነት” ተብሎ ሊጠራ አይችልም ። እንዲህ ያለውን አለመረዳት “ለዐብዮቱ መጨናገፍ” ምክንያት የሚያደርጉ ሰዎችም አሉ ። ነገር ግን ይህ ውሱንነት በራሱ ምን ያህል ከርእዮቱ ዝንፋት ፣ ምን ያህል ደግሞ ከተማሪዎቹ አለመረዳት የመጣ ነው የሚለው ጥያቄ ላይ እንደ ቆምንበት ቦታ ልዩ ልዩ አቋም ልንወስድ እንችላለን ። ማርክሳዊ የሆነ ሰው የእነሱን መረዳት ሊወቅስ ይችላል ፤ ማርክሳዊነት ስንኩል ርእዮት ስለሆነ ተከታዮቹን ግርምቢጣዊ ወደሆኑ አቋሞችና ድርጊቶች መምራቱ ፣ ጥፋትንም ማስከተሉ አይቀርም የሚል ሰው ደግሞ የተማሪዎቹ ድርጊቶች በአመዛኙ የማርክሳዊነት አመክንዮአዊ ውጤቶች እንደሆኑ ሊያስብ ይችላል ።

ሌላው እና እውነትም “በዐብዮቱ” ታሪክ ውስጥ ጎልቶ ይታያል ብዬ የማስበው ችግር ግን በተማሪዎቹ የትግል ታሪክ ውስጥ ብዙ ነገሮች እንዲህ ካለ ከተረዳ ወይም ካልተረዳ መታመን እንደተደረጉ ሁሉ ፣ ሌሎች ብዙ ከርእዮቱ ጋር ግንኙነት በሌለው ምክንያት የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተፈጸሙ ድርጊቶች መኖራቸው ነው ። ለዚህም ነው እንደ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ እና ሌሎችም ብዙ ጸሐፊዎች ተማሪዎቹ “ያደረጉትን ሁሉ በቅንነት አደረጉት” የሚል ፈጽሞ ከሐቅ ያልተነሣ እና ራሳቸውን እና አባል የነበሩበትን ንቅናቄ ከተጠያቂነት ለማስመለጥ የሚቀርብ መከላከያ የማይዋጥልኝ ፣ የሚያሳዝነኝ ፣ የሚያበሳጨኝም ። ይህ ግን በይደር ይቆየን ።

ይህ ታዲያ ከዋናው – ከብቸኛው ጥያቄ ጋር ያጋፍጠኛል ። ታዲያ ፣ አንተ ትክክለኛው መሠረት ፣ እውነተኛው መንገድ ፣ ርቱዓዊው ርእዮት ነው የምትለው ምንድነው ? አንድም ‘እስካሁን ስትል የቆየኸውን ነገር ሁሉ የትኛውን ርእዮት ይዘህ ፣ የትኛው መሠረት ላይ ቆመህ ነው ስትል የነበረው ?’ ልባልም እችላለሁ ። መልሴ እስካሁን ካነሣኋቸው አንዳንድ ነጥቦች ሊገመት ይችላል ። ብዙ ሰዎችም በቁም ነገር ይህን መልስ መስጠቴን ማመን ሊከብዳቸው እንደሚችል ይገባኛል ። ነገር ግን መልሴ ይኸው ። ክርስትና ።

 

መተላለፊያ

ይህን ጽሑፍ መደምደም አይቻለኝም – ብዙ እንዲህ በአጭሩ ልዘጋቸው የማልችላቸውን ጉዳዮች የከፈትሁበት ነውና ። ብዙ ጉድለቶች እና ድካሞች እንዳሉት አውቃለሁ ። ላነሣ የፈለግኋቸው ሐሳቦች ከዚህ በተሻለ ጥልቀትና ርቀት ሊገለጹ ፣ ባማረም ቋንቋ ሊብራሩ ይገባቸው ነበር ። ነገር ግን ከአቅሜ ውሱንነት ባለፈ ጠቅላላው ሐሳብ በዚህ ጊዜ ዐደባባይ መውጣቱ አስፈላጊ ስለነበረ – በታላቅ መጣበብ ነው ከዚህ የደረሰው ። ምናልባት ከሆነልኝና ጽሑፉም የተገባው ሆኖ ከተገኘ በውስጡ ለተነሣው ሐሳብ ፍትሐዊ ለመሆን የዳበረ እትም ወደፊት ለማዘጋጀት አስባለሁ ።

ከዚያ ባለፈ ግን የዚህ ጽሑፍ ዐቢይ ሐሳብ ከእስካሁኑ የጠለቀ ተዋሥኦ የሚያስፈልገን መሆኑ እንደመሆኑ – ራሴ በጠራሁት ድግስ ልቀር አይቻለኝምና – ከተሳካልኝ – በአጋፋሪነት ጭምር የተዋሥኦው ተካፋይ መሆንን ግዴታዬ አድርጌዋለሁ ።  እስካሁን ያነሣኋቸው ነጥቦች በራሳቸው ብዙ ሐሳቦችን ሊያጭሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ ።

በጽሑፌ መጨረሻ ትክክለኛው መሠረት ፣ እውነተኛው መንገድ ክርስትና ነው እንደማለቴ – ክርስትናን ከዚህ ርእስ ጋር ምን እንደሚያገናኘውና – ከክርስትና አንጻር ነገሩን እንዴት ልንመለከተው እንደምንችል ማብራራት ይጠበቅብኛል ። ይህ ብቻም አይደለም ፤ ሌላም ጥያቄ መመለስ አለበት ። እስከ ዛሬ “ዐብዮቱን” በተመለከተም ሆነ ሌሎች “ሃይማኖታዊ ያልሆኑ” ጉዳዮችን በተመለከተ ከቤተ ክርስቲያን በኩል የሚባል ነገር የለም – ከውጭም ቤተ ክርስቲያንን ይመለከትሻል ብሎ የሚጠይቃት የለም ። እንዲህ ያለው የቤተ ክርስቲያን መገለልና ራሷንም ማግለል ለምን ሆነ ? ተገቢስ ነው ወይ ? ይህንም መነጋገራችን የግድ ነው ።

ዳግመኛም ፥ ምንም እንኳን በዚህ ጽሑፍ እንደ ወተወትሁት በዋናነት መሠረታዊ ጥያቄዎች ላይ ማተኮር አለብን ብዬ ባምንም ፥ ይህ ግን ታሪካዊ ጥያቄዎች ረብሕ የላቸውም ማለት አይደለም ።  በተሳሳተ መንገድ የተነገሩ ታሪኮች መሞገት አለባቸው ። ስለዚህም የተለያዩ መጻሕፍትን በማመሳከር አስፈላጊ የሆኑ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንሞክራለን ።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እነዚህ ሥራዎች ሳይቋረጡ ፥ መዘግየት እንኳን ቢኖር ፥ በዚህ ዓመት ይቀጥላሉ ። ውጤቶቹም በየጊዜው ወደ እናንተ ይደርሳሉ ። ዓይን እና ጆሮ ያገኛሉ – በስምምነት ይታጀባሉ – በሙግትም ይተገተጋሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ።

 

[1] Dostoyevsky F.M. (1985), Winter notes on Summer impressions, Translated by Kyril FitzLyon, Quartet books. pp. 46-8

[2] “Hundreds of thousands of people from all classes and ranks of society crowd by each other [on the streets]…. Meanwhile it occurs to no one that others are worth even a glance. The brutal indifference, the unfeeling isolation of each individual person in his private interest becomes the more repulsive and offensive, the more these individuals are pushed into a tiny space. We know well enough that this isolation of the individual, this narrow-minded self-seeking—is everywhere the fundamental principle of modern society…. From this it follows that the social war—the war of all against all—has been openly declared. As in Stirner, men here regard each other only as useful objects.”

Engels F., Manchester and the Working Class (New York, 1975), 147 (Cited in Frank J. (197_), Dostoyevsky, The Stir of Liberation, Chapter 16, footnote 2)

[3][3] Blanning T. (2008), The Pursuit of Glory; The Five Revolutions that Made Modern Europe 1648-1815, Penguin Books, p. 137-8

[4] Ibid, p. 40

[5] Ibid, p. 489

[6] Miller E.L. (1984), Questions that Matter, An Invitation to Philosophy, McGraw Hills Books, p. 150

[7] Engels F. and Marx K. (1975), p. 73-4

[8] Holland T., (2019), The Making of the Western Mind, Little, Brown, Chapter 18

[9] ቶም ሆላንድ የመጽሐፉን ዋና ሐሳብ በመግቢያው እንዲህ ሲል ነበር ያጠቃለለው ።

“Today, at a time of seismic geopolitical realignment, when our values are proving to be not nearly as universal as some of us had assumed them to be, the need to recognise just how culturally contingent they are is more pressing than ever. To live in a Western country is to live in a society still utterly saturated by Christian concepts and assumptions. This is no less true for Jews or Muslims than it is for Catholics or Protestants. Two thousand years on from the birth of Christ, it does not require a belief that he rose from the dead to be stamped by the formidable – indeed the inescapable – influence of Christianity. Whether it be the conviction that the workings of conscience are the surest determinants of good law, or that Church and state exist as distinct entities, or that polygamy is unacceptable, its trace elements are to be found everywhere in the West. Even to write about it in a Western language is to use words shot through with Christian connotations. ‘Religion’, ‘secular’, ‘atheist’: none of these are neutral. All, though they derive from the classical past, come freighted with the legacy of Christendom. Fail to appreciate this, and the risk is always of anachronism. The West, increasingly empty though the pews may be, remains firmly moored to its Christian past.”

Ibid, preface

[10] Dostoyevsky F.M., The Brothers Karamazov, translated by Constance Garnett, Om Books International, 2024, p. 33

[11] Schmemann A. (1979), Church, World, Mission: Reflection on Orthodoxy in the West, St. Vladimir’s Seminary Press, New York. pp. 28-30

[12] Ibid, p. 63

[13] “With God banished from the physical universe and relegated to primal clock-maker, the way was free for human beings to concentrate on the here and now. Life was no longer o be regarded as a vale of rears though which the faithful had to pass before gaining admission to Heaven, or being set down to Hell; it was promoted be humankind’s prime concern. So the Enlightenment can be said to have been secular, although the German word ‘diesseitig’ is more eloquent, meaning ‘this side of the grave,’ as opposed to ‘jenseitig’ or ‘the far side of the grave’. It can also be said to have been anthropocentric, a quality best expressed by Alexander Pope in his Essay on Man (1733):

Say first of God above or Man below,

What can we reason, but from what we know?

Of Man what see we, but his station here,

From which no reason, or to which refer?

. . .

Know then thyself, presume not God to scan;

The proper study of Mankind is Man.”

Blanning T. (2008), p. 491

[14] Bulgakov S.N. (2000), p. 40

[15] Bahru Zewde (2010), p. 279

Share...

Facebook
Telegram
WhatsApp
X
Email
Print
Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

“የአእላፋት ዝማሬ”

ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ ባለፈው ዓመት በልደት ዋዜማ ተካሔደ ። በአዘጋጆቹ እና በተሳታፊዎቹ ዘንድ ይህ ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው ዙር በላይ ያማረ እና የሠመረ ሆኖ ተቆጥሯል ። በጠቅላላው ከምእመናን በኩል በተሳትፎም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘው ተቀባይነት ሌሎች ሁነቶች ሲሆኑ እንደምናየው በጅምር የሚቀር ሳይሆን እንደ ባህል የመተከል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን ያመላክታል ። እንዲያውም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ብቻ ሳይወሰን ወደ ሌሎች ቦታዎችም እንዲሰፋ የሕዝብ ጥያቄ እና በአዘጋጆቹም በኩል እቅድ መኖሩ ይታወቃል ። ስለዚህ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ልክ እንደ ጥምቀት ሁሉ በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ (የአዘጋጆቹ አቅም በፈቀደው ልክ) የአእላፋት ዝማሬ የልደት በዓል መለያ ሆኖ እንዲካሔድ መጠበቅ እንችላለን ። ይህ ነገር በብዙዎች ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጥቅም የሚሰጥ ሆኖ ይታያል ። በእነርሱ ዐይን ይህ ሁነት ቤተ ክርስቲያን በብዙዎች ዘንድ እንድትታወቅ ያደርጋል ። ብዙዎች በዓሉን አስመልክተው ከሚሔዱባቸው የማይገቡ ዓውዶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ ከማድረጉ ባሻገር ፥ በቤተ ክርስቲያን ሱታፌ ያላቸውንም በሚስብ እና በሚገባቸው መልኩ ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ እንዲያውቋት ያስችላቸዋል ። ስለዚህም የሌሉትን በመጥራት ፥ ያሉትንም በማጽናት ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን እንድትዋጅ የሚያስችላት መሣሪያ ነው ፤ ከእርሷ ዘንድ ወደ ክሕደት እና ወደ ኑፋቄ የፈለሰውን ፥ ወይም በስም ክርስቲያን ሆኖ እና ማዕተብ አስሮ ሳለ በምድራዊ ተድላ ባሕር የሰጠመውን ወጣት ወደ ራሷ የምትስብበት መረብ ነው ። ነገር ግን ከኖረው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና አስተምህሮ አንጻር ከመረመርነው ፥ ይህ ሁነት

Read More »
Emmaus Posts
ኤልያስ ገብረ ሥላሴ

መከራ ፣ እከይ እና ክርስትና

መከራ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ድንገተኛ የሆነ ክስተት አይደለም ። ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ለጥቅማችን የሚፈቀድ የእርምት መንገድ ነው እንጂ ። በየዘመኑ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ሁነቶች እንድትወጠር እና መሠረታዊ ነገሮች ትኩረት እንዳያገኙ የሚቀርብ ፈተና አለ ። ሰበር ዜናዎች ፣ ወቅታዊ አጀንዳዎች ፣ አከራካሪ ጉዳዮች ወዘተ ከመነኩሴ መቁጠሪያ በላይ በሚሽከረከሩበት ዘመን ላይ ነው የምንገኘው ። እነዚህ ሁነቶች ትኩረታችንን ይወስዱትና ሳይታወቀን መሠረታዊ ከሆኑትና ዘለዓለማዊነታችንን ከሚበይኑት ጉዳዮች ወጥተን ምድራዊና እዚሁ ቀሪ በሆኑ ጉዳዮች ተወጥረን እንገኛለን ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁኔታ በቤተክርስቲያንን መምህራን እና “ተጽዕኖ ፈጣሪዎች” ላይ እጅግ በርትቶ የሚታይ መሆኑ እና በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እና መድረኮች ሳይቀር ሰፊውን ሰዓት መያዙ ነው ። የቤተክርስቲያን ተልእኮ ስለ ክርስቶስ ምስክር መሆን ነው ። መሠረታዊ ካልሆኑት ሁነቶች ወጥተን ወደዚህ ዋነኛ ተልእኮአችን እንድንመለስ ተዋሥኦ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ። ይህ በምእመናን ፥ በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲን አገልጋዮች ፥ ዘንድ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ። የሁነቶችን መሠረት መመርመርና ትክክለኛ ባሕርያቸውን መረዳት ያሻል ። ሁነቶቹ ችግሮች የሆኑ እንደሆነ ሥር ነቀል መፍትሔ ማሰብ የሚቻለው ፥ መልካም አጋጣሚዎችም ከሆኑ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ልናውላቸው የምንችለው የሁነቶቹን መሠረት በጥልቀት መረዳት ከቻልን ነው ። በመቀጠልም ተከትለው ሊደረጉ ስለሚገቡ ነገሮች መወያየት ከተቻለ ብቻ ነው ። ካልሆነ አሁን እየሆነ እንዳለው የወቅታዊ አጀንዳዎች አሳዳጅ ብቻ ሆነን ነው የምንቀረው ። በተለይ ዘመናችን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ስለሆነ በዚህ

Read More »
Emmaus Posts
መሐሪ ዘመልአክ

ከእውነት አልባነት ጋር የሚካሔድ ሙግት

(‘ሐሳቦች መዘዝ አላቸው’ በሚል ርእስ በኤማሁስ መጽሔት ቅጽ 1 ፣ ቁጥር 1 በወጣው ጽሑፍ ላይ የተጻፈ አስተያየት) በመሐሪ ዘመልአክ (PhD) ከዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት የእጓለ ገብረ ዮሐንስ ‘የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ’ ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበብኹ በኋላ ጸሐፊውን ከዚያ በፊት አለማወቄ ገርሞኝ እንደነበር አስታውሳለኹ ። ማን ናቸው ? እንዴት እስከዛሬ ድረስ ስለእርሳቸው ሳልሰማ ቀረኹ ? ለምን ? ይኼ በ1956 ዓ.ም. የታተመ የሬድዮ ንግግር ከኾነ መጽሐፍ ለመጻፍ ብለው ተነሥተው ቢጽፉ ኖሮ ምን ሊጽፉ ነበረ ? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎች ጭንቅላቴ ውስጥ ተመላልሰዋል ።[1] በኋላ ፈላስፋው ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተማሪና መምህር እንደነበሩ ስሰማ በመጽሐፉ ውስጥ ያየሁት የሐሳብ ጥልቀት በዘመኑ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልሒቃን ዘንድ የነበረው ተዋሥኦ ሊደርስ ይንጠራራበት የነበረውን ልክ የጠቆመኝ መሰለኝ ። ከዚያ በኋላ ያ የተዋሥኦ ልሕቀት የት ገባ ? እንዴት ድርቅና የተጫነው ተዋሥኦ ዋጠው ? እንዴት ኦርቶዶክሳዊነትን ከአመክንዮ የተፋታ እና አመክንዮን የሚፈራ ጭፍን እምነት የሚያስመስሉ የፎክሎር ሰባኪዎች ተፈለፈሉብን ?  የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህን ለመኾን የሚጠየቀው መስፈርት ስለምን ድፍረት የለበሰ አላዋቂነት መሰለ ? በሚዲያ ላይ ሲናገሩ በአላዋቂነታቸው አንገታችንን የማያስደፉን ካህናት ስለምን ቁጥራቸው አልበረክት አለን ? ኦርቶዶክሳዊነት ችግርን እና ጭንቀትን ለማረሳሳት የተጠመቀ ዕፀ-ዝንጋዔ (‘opium of the masses’) እስኪመስል ድረስ በኦርቶዶክሳዊነት ስም የገነነው ተዋሥኦ ለምን አላዋቂነት ተጫነው ? ቤተ ክርስቲያን ሲባል ከስሜታዊ ሙጥኝታ (sentimental attachment) ባለፈ ለሰው ልጅ ህልውናዊ ጥያቄ የተሰጠ ከሞት ፍርኃት

Read More »
Emmaus Posts
ኤማሁስ

የኤማሁስ መንገድ

መጽሔቷን ለማግኘት ይህን ይጫኑ . . . የዘመናችን ተዋሥኦ በይዘቱም ሆነ በመንገዶቹ በግልብነት በእጅጉ የተጠቃ ነው ። ‘በይዘቱ እንዴት ?’ቢባል ሁነቶች ላይ ያተኮረ እና ወቅታዊነትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ። አንድም አቋም ከመያዝና ጎራ ከፍሎ ከመናቆር ባለፈ የእውነት የመማር እና የማሰላሰል ጉጉት የማይታይበት በመሆኑ ። በዚህ ተዋሥኦ ውስጥ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሣት እና ከሁነቶቹ የሚሻገር እና ሐሳባዊ የሆነ ትንተና ለማካሔድ መሞከር ትኩረት ያስነሣል ፤ ሲብስም አጉል እንደመራቀቅ ይታያል ። የሚካሄድበት ከባቢ እና ዘመን ደግሞ ሌላ ግልብነት ደርቦለታል ። በእኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሀገራት ፣ ከዘመናዊነትና ከቴክኖሎጂ መራቀቅ ጋር ተያይዞ ሕዝባዊ ተዋሥኦ በጠቅላላው ስለቱን እና ርቀቱን እንዲያጣ ሆኗል ። የሚነበብም ሆነ የሚታይ ወይም የሚደመጥ ነገር አጭር መሆን አለበት ። ነገር ግን ጠቃሚና ወሳኝ ርእሶች እንዲህ ባለ መንገድ ሊስተናገዱ አይችሉም ። የሚያጠግብ ፍሬ ከሌለበት የተመልካቹ እና የአንባቢው ብዛት ምን ጥቅም ይኖረዋል ? እንዲህ ባለው ከባቢ ውስጥ ሁነቶችን ከሁነትነታቸው እና ከሚያመጡት ወቅታዊ ውጤት በተሻገረ መልኩ ለመመልከት እንቸገራለን ። ቀድሞውኑም (እይታችን ከመጥበቡ የተነሣ) ጠባብ አድርገን የቀረጽነውን አጀንዳ በምንገልጽበት መንገድ የበለጠ እናጠብበዋለን ። ነገር ግን ሁነቶችን እና ሒደቶችን ከመሠረታቸው መመርመራችን እና የምናቀርባቸው መፍትሔዎችም እንዲሁ የማይናወጥ መሠረት ያላቸው መሆናቸው አስፈላጊ ከሆነ ተዋሥኦውም እንዲሁ የጠለቀ እና የረቀቀ መሆን አለበት ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ጊዜ ወስዶ ማሰብ ፣ ማንበብ ፣ ማጠናቀር ፣ መወያየት ፣ መሟገት እና እንዲህ ካለው ሒደት

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

ብያኔን አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ

ከሁለት ሳምንታት በፊት ‘ከጥያቄዎቹ በላይ አደገኛ የሆኑት መልሶች’ በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ አቅርበን ነበር ። ጽሑፉ በዋናነት ማሳነስ (reductionism) የተባለውን ፅንሰ ሐሳብ የሚያነሣ እና የሚተች ነው ። በዚህ ጽሑፋችን ውስጥ መምህር ያረጋል አበጋዝ በቅርቡ ‘ወደ ላይ አያዳልጣችሁ’ በሚል ርእስ ገዳማዊ ሕይወትን ከዘነበ ወላ ዘለፋ ለመከላከል ጽፎ ያጋራውን ጽሑፍ ተችተናል ። ርእሱን በዚህ ጊዜ ጉዳይ ያደረግነውም በዋናነት በምምህር ያረጋል ጽሑፍ ምክንያት ነው ። በተለይ ጽሑፉ ሰፊ ተነባቢነት እና ተቀባይነት ያገኘ እንደ መሆኑ በውስጡ ያየነውን የማሳነስ ዝንባሌ መተቸቱ ጠቃሚ ይሆናል ብለን አመንን ። ነገር ግን የመምህር ያረጋል ጽሑፍ መነሻ ቢሆነንም በይበልጥ ፅንሰ ሐሳቡ ላይ ለማተኮር ነው የሞከርነው – ዓላማችን ነገሩ ላይ ተዋሥኦ እንዲጀመርና የተሻለ መረዳት እንዲፈጠር ማድረግ ስለሆነ ። መምህር ያረጋልም ጽሑፉን ተመልክቶ ምላሽ ሰጥቶናል ። ምላሽ በመስጠቱ ደስ ብሎናል ። በምላሹ ግን አልተደሰትንም ። አለመደሰታችን እኛ በእርሱ ጽሑፍ ላይ ያቀረብነውን ትችት ባለመቀበሉ አይደለም ። ይልቁንም የተሰጠው ምላሽ ከእኛ ትችት ጋር እምብዛም የተያያዘ ባለመሆኑ እንጂ ። ከነገሩ ጋር የማይገጥሙ ምሳሌዎች ቀርበዋል ። ያቀረብነው ሂስ በተሳሳተ መንገድ ተተርጉሟል ። በጽሑፋችን በስም ጠርተን ያራቅነው እና ያነወርነው ሐሳብ የእኛ አቋም ተደርጎ ተገልጧል ። “ለቤተ ክርስቲያን ከልባችን ከመጨነቅና ከመቅናት” ተነሥተን “ያልተባለውን ለማስመሰል በመድከማችን” ተወቅሰናል ፤ ዕጣችን ሆኖ “ሳንነቅፍ መጻፍ አልቻልንምና” ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች መልስ እና እርማት የሚሹ ሆነው አግኝተናቸዋል ። አንድም ለእኛም ሆነ ለመምህር ያረጋል

Read More »
Emmaus Posts
ቀሲስ አባተ አሰፋ

በፍጹም ለመነቃቀፍ የጠፋ ጊዜ አልነበረም

መምህር ያረጋል ለዘነበ ወላ የሰጠውን መልስ ተከትሎ በኤማሁስ ፕሬስ ጸሐፍት በኩል የቀረበው ትችት አግባብ አለመሆኑን የሚገልጥ አንድ ጽሑፍ አጋርቶናል። ጽሑፉም እዚሁ ገጽ ላይ የወጣ ስለሆነ ብዙ ሰው ያነበበው ይመስለኛል። ያረጋል በዚህ ጽሑፉ ሁለት ነገሮችን ማስተላለፍ የፈለገ ነው የሚመስለኝ። የመጀመሪያው ለዘነበ ወላ የሰጠው መልስ ፈጽሞ በ’reductionism’ የሚከሰስ አለመሆኑን ማሳየት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ጸሐፍቱ እንዲያው እሱን እንንቀፈው ብለው ካልሆነ በስተቀር የጻፉትን የሚያጽፍ ምክንያት ከእርሱ ጽሑፍ ውስጥ የማያገኙ መሆኑን መጠቆም የፈለገ ሆኖ ነው ያገኘሁት። በርግጥ በዚህ ጽሑፍ እኔ ማተኮር የፈለግሁት ሁለተኛው ላይ ቢሆንም፣ ከ“reductionism” ጋር በተያያዘ ስለተነሣው የመጀመሪያው ጉዳይ ግን ትንሽ ነገር ልናገር። ‘reductionism’ (የራሱን የያረጋልን ትርጉም ልጠቀምና – ክርስትናን ወደ ምድራዊ እሳቤና መለኪያ ዝቅ ማድረግ) የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ከልዕልናው አውርዶ ጊዜያዊ ለሆኑ ሌሎች የኑሮ ዘይቤዎች ተገዢ የሚያደረግ  አደገኛ መንገድ ነው። በመሆኑም በነገረ መለኮት ሊቃውንት ደረጃ በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያሉ ውይይቶች መደረግ ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል። በኤማሁስም በኩል፣ ይኼ ርእሰ ጉዳይ ሲነሣ፣ የኤርሚያስ እና የበርናባስ ጽሑፍ የመጀመሪያው አይደለም። ያረጋል ከጻፈው ጽሑፍ ጋር ሳይገናኝ፣ ከአሁን በፊት በሠራናቸው ፖድካስቶች ማሳነስን (reductionism) እንደ አንድ አደገኛ ዝንባሌ ስናነሣ እንደነበር ሲከታተሉን የነበሩ ሰዎች የሚያስታውሱ ይመስለኛል። ነገር ግን ስለነገሩ ምንነትም ሆነ ስላለው አደጋ ገና እንዳልተግባባን እና በዚሁ ጉዳይ ከዚህም በላይ ገፋ አድርገን መነጋገር የሚገባን ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ይኼው የያረጋል መልስ ይመስለኛል። ያረጋል ጽሑፉን ለመከላከል የቅዱሳት መጻሕፍትን አቀራረብ ያነሣበት አግባብ፣ የቀረበበትን

Read More »