“የአእላፋት ዝማሬ”

ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ ባለፈው ዓመት በልደት ዋዜማ ተካሔደ ። በአዘጋጆቹ እና በተሳታፊዎቹ ዘንድ ይህ ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው ዙር በላይ ያማረ እና የሠመረ ሆኖ ተቆጥሯል ። በጠቅላላው ከምእመናን በኩል በተሳትፎም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘው ተቀባይነት ሌሎች ሁነቶች ሲሆኑ እንደምናየው በጅምር የሚቀር ሳይሆን እንደ ባህል የመተከል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን ያመላክታል ። እንዲያውም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ብቻ ሳይወሰን ወደ ሌሎች ቦታዎችም እንዲሰፋ የሕዝብ ጥያቄ እና በአዘጋጆቹም በኩል እቅድ መኖሩ ይታወቃል ። ስለዚህ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ልክ እንደ ጥምቀት ሁሉ በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ (የአዘጋጆቹ አቅም በፈቀደው ልክ) የአእላፋት ዝማሬ የልደት በዓል መለያ ሆኖ እንዲካሔድ መጠበቅ እንችላለን ።
ይህ ነገር በብዙዎች ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጥቅም የሚሰጥ ሆኖ ይታያል ። በእነርሱ ዐይን ይህ ሁነት ቤተ ክርስቲያን በብዙዎች ዘንድ እንድትታወቅ ያደርጋል ። ብዙዎች በዓሉን አስመልክተው ከሚሔዱባቸው የማይገቡ ዓውዶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ ከማድረጉ ባሻገር ፥ በቤተ ክርስቲያን ሱታፌ ያላቸውንም በሚስብ እና በሚገባቸው መልኩ ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ እንዲያውቋት ያስችላቸዋል ። ስለዚህም የሌሉትን በመጥራት ፥ ያሉትንም በማጽናት ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን እንድትዋጅ የሚያስችላት መሣሪያ ነው ፤ ከእርሷ ዘንድ ወደ ክሕደት እና ወደ ኑፋቄ የፈለሰውን ፥ ወይም በስም ክርስቲያን ሆኖ እና ማዕተብ አስሮ ሳለ በምድራዊ ተድላ ባሕር የሰጠመውን ወጣት ወደ ራሷ የምትስብበት መረብ ነው ።
ነገር ግን ከኖረው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና አስተምህሮ አንጻር ከመረመርነው ፥ ይህ ሁነት እና ሁነቱን ያፈራው ባህል ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ አደጋ መሆናቸውን እንመለከታለን ። ተፈጥሮውንና ቅኝቱንም ከክርስትና የተቃረኑ ሆነው እናገኛቸዋለን ። በሚከተለው ጽሑፍ ውስጥ ይህን ተቃርኖ  ለማብራራት ተሞክሯል ።

 

Share...

Facebook
Telegram
WhatsApp
X
Email
Print
15 Comments
  • Nahom
    Nahom
    December 16, 2025 at 6:18 pm

    Mezemurochune betsehufe lakulegne

    Reply
    • Dn Bereket Abraham
      Dn Bereket Abraham
      December 21, 2025 at 11:28 am

      ወንድሜ በርናባስ ሽፈራው፡ በዚህ ልክ የነገሩን አካሄድ በጥልቀት ተረድተህ እምጥንቱ እስከ ተፍጻሜቱ በሚገባ እየሞገትክ በlogical way ሀሳብህን በዚህ መልኩ አዘጋጅተህ ስላቀረብክልን ልባዊ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ።
      ዲ/ን በረከት ከጐንደር ዓቢየ እግዚእ

      Reply
  • genet
    genet
    December 17, 2025 at 4:09 am

    ቤተክርስቲያን የልጆቿ መገደል እና መሰቃየት መሰደድ በአንድነት ተሰብስበን መጮህ ስለምን አልተቻለንም ? ምንም እንዳልተፈጠረ እንዲህ አሸብርቆ መዘመሩ ውስጣችን ምንም ስሜት ሳይኖር ቀርቶ ነው ? ወይስ ሸፋነነው ለማለፍ እየሞከርን ነው ? የሚል ጥያቄዎችንም ያስነሳል ።

    Reply
    • ደበበ ፡ አቡ
      ደበበ ፡ አቡ
      December 29, 2025 at 1:59 pm

      ጥሩ ፡ ምልከታ ፡ ነው። የሚያብሰከስከኝ ፡ ነገር ፡ ነበረ። ለእራሱ ፡ ለዲያቆን ፡ ሄኖክ ፡ ስለኢጃት ፡ ወጣቶች ፡ ወደሰንበት ፡ ትምህርት ፡ ቤት ፡ መመለስ ፡ በተገናኝነበት ፡ አጋጣሚ ፡ ነግሬዋለሁ። ለኹለተኛ ፡ ጊዜ ፡ እንደመጀመሪያው ፡ ለቅጽበት ፡ ስንገናኝም ፡ እንደፓይለት ፡ ፕሮጀክት ፡ ከሦስት ፡ ሰንበት ፡ ትምህርት ፡ ቤት ፡ ጋራ ፡ እንደጀመሩት ፡ ነግሮኛል። ወደሰባት ፡ እንደሚያሳድጉትም። እኔ ፡ በኢጃትም ፡ የሠለጠንኩ ፡ እንደመኾኔ ፡ የችግሩ ፡ ምንጭ ፡ አእላፋት ፡ ሳይኾን ፡ እራሱ ፡ ኢጃት ፡ ይመስለኛል። እስቲ ፡ አሁን ፡ ቪዲዮውን ፡ ከሞላ ፡ ጎደል ፡ ሰምቻለሁ። ቢረዝምም ፡ ጽሑፉንም ፡ ማታ ፡ አንብቤያለሁ። የሚመስለኝን ፡ ብዙ ፡ በማያውቃት ፡ ገጼ ፡ ልመልስበት። ፌስቡክ ፡ በስሜ ፡ ደበበ ፡ ነው።

      Reply
  • miiia
    miiia
    December 17, 2025 at 9:26 am

    በጣም ወሬ የሚወደ ሰው አየሁ እናተ እኛ ምን ሰራን አትሉም ህዝቡ መጠጥ ቤት ልደቱን እያሳለፈ አንድ ቀን ያልተናገራቹህ አሁን እነሱ መተዉ እንዲህ ቢሆን አሪፍ ነው ሲሉ መተቸት እኛ ምን ሰራን ለቤተክርስቲያን ይባላል መጀመሪያ ከመተቸት

    Reply
    • Afomkfs
      Afomkfs
      December 22, 2025 at 6:08 am

      ገንቢ ያልሆነ የልጅ አስተያየት ከመፃፎ በፊት, Please do read the full article!

      Reply
    • Abrhahm
      Abrhahm
      January 4, 2026 at 1:36 pm

      ሸጋ መጣጥፍ ነበር በርታ
      በመጻሕፍት ዙሪያ ግን ያለህን የንባብ
      ልምድህን አካፍለን

      Reply
  • melaku surafel
    melaku surafel
    December 17, 2025 at 11:49 am

    about Aelafat article
    ወንድም በርናባስ ፅሁፉን በሙሉ አንብቤዋለሁ ጥሩ እይታ ነው ፡፡ እንደ ማህቀፍ ያነሳሀው ከቤ/ን ከማህሌትና ቅዳሴ ውጪ ያሉ ሲጀመሩም ( ለምሳሌ የመጀመርያዎቹ ዘማርያን እነ ዘማሪ ኪነ ጥበብ ፡ ይልማ፡ታደለ ፊጣ እና ሌሎችም) መዘመር ሲጀምሩ በወቅቱ ከመናፍቃን አካባቢ የነበረው በ”ዝማሬ” ስም ወይም ዘዴ ምእመናን ከበረታቸው የማፈናቀለ ዘመቻና ምእመናንም በዚህ የመሳባችን ችግር ያመጣው ወይም ዘመን የወለደው ጊዜያዊ መፍትሄ ነበር (እንደኔ መረዳት)፡፡ ነፍሱን ይማረውና አንድ ስሙን የዘነጋሁት ሰባኪ ስለዚህ ጉዳይ የጃንደረባው ሚድያ ላይ ተጠይቆ በዝርዝር የመለሰውን አይቻለሁ፡፡ ከዚያ በሀላ ሲደረግ የቀጠለውም አሁንም የደረስንበት በብዛት ግጥሙ ላይ የማተኮርና ዜማው ወይ የመናፍቃን ወይ የዘፈን እንዳይመስል የመጠንቀቅ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ለይቶለት ከግጥሙ ውጪ ከሙዚቃ ክሊፕ ጋር በአካሄድ በስልት አንድ አይነት ሆናል፡፡ እኛም የዚህ ዘመን ትውልድ እንደመሆናችን ትውልዱን ለመያዝ ይህንኑ ጊዜዊ መፍትሄ ተብሎ በአንዳንድ ቅን ምእመናንና ሰባኪያን የተጀመረውን ችግር አስቀጥለናል፡፡
    1. በቤ/ን የማህሌት፡የቅዳሴ አገልግሎት ከቁዋንቑ ጋር በተያያዘና አእላፋትን በተመለከተ እንደ ስህተት ወይም ሊስተካከል እንደሚገባው አድርገህ ያነሳሀቸው ነጥቦች በሙሉ እምጋራቸው ቢሆንም ስብስቡን በራሱ እንደ ችግርና ሊስተካከል እንደማይችል አድርገህ መደምደምህ ግን አልተቀበልኩትም፡፡ ምክንያቱም በቅን መንፈስ የተደራጁና የራሳቸውን ጡብ ለማስቀመጥ የተነሱ የሚውተረተሩ ልጆች ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያቱ ምናልባት ከ1950ዎቹ ትውልድ ጋር በገደምዳሜው ያነሳሀው የቤ/ን መዋቅር ላይ ያሉ ሰዎች መፍዘዝ ሳይሆን መሞት ያመጣው ዘመንን ያለመዋጀት ችግር ነው (በአቀራረብ፡በትርጉም ስራ…)፡፡ ድሮ ድሮ ሳያውቁ ይመስለኝ ነበር አሁን በደረስኩበት ድምዳሜ ግን ቤ/ንን ለማፍረስ ሆን ተብሎ በውስጥም በውጭ በቤተክህነቱ መዋቅር የተቀመጡ ሽባ ያደረጉን አካላት አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ዘመኑን የዋጀ አሰራር አካሄድ መዘርጋት ሲገባን በመዋቅርና በአሰራር ቆሞ ቀርና የሞትን ( በአስተምህሮ አላልኮም አደራ) በመሆናችን ምክንያት ተስፋ የቆረጡ ወጣቶች ከቤ/ን መዋቅር ምንም አይነት መፍትሄ ስለማይጠብቁ በራሳቸው መፍትሄ የሚሉትን መተግበር በመጀመራቸው እንዲህ አይነት ጉዳይ ተኮር ማህበራት (Project focused) ተፈጠረዋል ገና ይበራከታሉ፡፡ በዚህም ከተሳካለቸውና ሌላ አላማ ከሌላቸውና አስተያየት የሚቀበሉ ከሆነ በጎ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይሄዳሉ ካልሆነ ደግሞ እንደ አንዳንድ ተቀዋማት እራሳቸው ፈተና መሆን ይጀምራሉ፡፡ እንዲህ አይነት ውዥንብር ሲፈጠር እኮ ፈቃዱን የሰጣቸው የቤ/ን መዋቅር ባይሞት ኖሮ ወጥቶ ከቤ/ን ስርአትና ደንብ አንጻር በዚህ ተረዱት ሰአቱ ቦታው በዚህ መልኩ ይደረግ ማለት ነበረበት ምክንያቱም ቤ/ን የሁላችንም ስለሆነች ማለት ነው፡፡ በእንቁላሉ ጊዜ …ብለን ከሰሙን ገንቢ አስተያየት መስጠትና እራስህ መፍትሄ ብለህ ያስቀመጥከውን” ትክክለኛውን የቤተክርስቲያኒቱ የአምልኮ ውብ ስርአት (-ይህም ቅዳሴና የማህሌቱ ጸሎት)” እንደዋነኛ መሳርያ አድርገው ተጠቅመው በመጪዎቹ አመታት ስለቅዳሴ ስለማህሌት በሚገባው መንገድ አስተምረው ለ አሁኑ” ዝማሬ “ የጎረፈው ህዝብ ወደ ቅዳሴ በየደብሩ እንዲጎርፍ ማድረግ ተገቢነው ፡፡
    2. በአርሲና በተለያዩ አካባቢዎች በእምነታቸው ምክንያት የሚጎዱ ወገኖቻችንን እንድንዘነጋና እንዳናስብ በዚህ ዙርያም የሚደረጉ ጥረቶች እንዳይታዩ መንግስት ለገጽታ ግንባት ሊያውለው እንደሚችልም ሳስብ በጣም አዝናለሁ አዘጋጆቹም ይህን እንዴት እንደሚያዩት ግራግብት ይለኛል፡፡ ለመሆኑ የቤ/ን ወቅታዊና አንገብጋቢው ችግር ለመዝሙር መሰለፍ ወይስ በአላማ እንደንጠፋ የተፈረደብን መሆናችንን ተገንዝበን እራሳችንን ማዘጋጀት ? የሚለውም በብዙ ሰው ዘንድ የአንድ ሰሞን ሀዘን ከመሆን ሊያልፍ አለመቻሉም ያሳስባል፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ መእመናችን ጎራ ከፍሎ የተከራከረውን ያክል በወቅታዊ የአርሲና የቤ/ን ጉዳይ ቢጻፍ እኔን ጨምሮ ይከራከር ይሆን ?
    በተረፈ ጽሁፍህ በጣም እረጅምና (23*2) በርእስ ያልተከፋፈለ መሆኑ ለማንበብ ይከብዳል በአይምሮ ቀንብቦ ለመያዝም ያስቸግራል፡፡ አንዳንድ ጥናት የሚፈልጉ የቍጥር የሚመስሉ መረጃዎች ለምሳሌ የአእላፍ ዝማሬ ተሳታፊዎችን አይነት (ሰንበት ተማሪ፡ ለበአል ጭፈራ ቤት የሚያዘወትርወዘተ) በመሰለን ገልጸሀቸዋል እርግጥም ቆጠራ ካልተካሄደ ከመሰለኝሊዘል አይችልም፡፡ ለወደፊቱ አጠር አጠር አድርገህ በርእስ ከፋፍለህ ቆጥረህ ሰፍረህ ሀሳብህን እንደምታስቀምጠው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
    ለሁሉም የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 4 ላይ ይመስለኛል የኦሪቱ ምሁር የእነ ቅዱስ ጳውሎስ መምህር ስለእነ ቅዱስ ጴጥሮስ በሸንጎ ላይ በሰጠው ምስክርነት አንዳንድ ሰዎች ተነስተው ብዙ ህዝብ አስከትለው እንደነበርና ከእግዚአብሔር ስላልነበሩ እነሱም ተከታዮቻቸውም እንደጠፉ ሐዋርያትንም በተመለከተ ለሾንጎ ፈራጆች “በእርግጥም ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ እንዳትገኙ” ብሎ እንደመከራቸው እኛ እንደምእመን የቤ/ንን ስርአት ከመጠበቅና ከማስጠበቅ አንጻርና የሚጠፉ ነፍሳትን ከመቀነስ አንጻር (በብልጭልጭ ዝማሬ ተመስጠው ከዋናው የአምልኮ ቅዳሴ ሳይደርሱ) “…በፍርሀትና በየዋህነት “ ምላሽና አስተያየት መለገስ ተገቢ ነው፡፡

    Reply
  • Seble Wongel
    Seble Wongel
    December 17, 2025 at 4:39 pm

    I wish there were a public dialogue around this topic. I fear many of the points you raised will fly over our heads and end up fueling mere hostility toward EJAT (SP?). The only reservation I had was your reference to C.S. Lewis … I don’t think I need to explain why. That said, your emphasis on going back to the roots and taking inventory of what we have before adding anything new really resonated with me. Thank you for sharing your insight; it was so compelling that I actually canceled my plan to fly to Ethiopia for the event … seriously!

    Reply
  • Zewdu bekele
    Zewdu bekele
    December 18, 2025 at 1:43 pm

    በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያንና መእመኑ መከራና ስደት ላይ ባሉበት ወቅት ይሄ የመናፍቃን ጉባኤ የመሰለ ከህገ ቤተክርስቲያን ሀዲድ የወጣ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ለተነሱ ቄሳሮችና መናፍቃን የፓለቲክ ሴራ የተመቸ ሌላው አለም የኦርቶዶክስን መከራ አውቆ ለተቃውሞ ሲነሳ አይ መንግስት የመእመናንን ደህንነት እና የቤተ ክርስቲያንን መብት ጠባቂ ነው የሚል መልእክት ለአለም ለማስተላለፍ የፕሮፓጋንዳ ሽፋን የሚሰጥ የአለም ጭፈራ ኮንሰርት ይዘት ያለው ዝግጅት ነው :: ለዚህም ነው ፓለቲካቸውን ለማራሙድ መስቀል አደባባይ ውጡና ዝፈኑ ብለው ይፈቀደችው ከንቲባዋ ::

    በተለይ በውጭ የተጀመረውን ይኦርቶዶክስ ጄኖሳይድ ለአለም ለማሳወቅ እየተሰራ ያለውን ታላቅ ተጋድሎን ተአማኒነት ያሳጣዋል :: ይሄንን መረዳት ያቃተው ኦርቶዶክሳዊ ከአራጆቻችን የሚያገኘውን ድርግና ጉርሻ ህሊናውን የዘጋው በንዋት ራሮት የስከሩ በሀይማኖቱ ስር ለቤተመንግስቱ ታማኝ ባለ ካባ ካድሬዎች ናችው አዘጋጅ ተብለው ብቅ ያሉት ::

    ለምን ወደ ሌላው ሀይማኖት ሄደ ወጣቱ? እንዲህ አይነቱ ከቤተክርስቲያን አስተምሮ ውጭ የሆነ የመናፍቃንና አለማዊ የመሰሉ አምልኮት እያደገ ስለመጣ የኦርቶዶክሳዊነት ጣእሙን የሚያስተምሩት እየከሰሙ ረጅም ጡዋፍ እያስበራ የሚፈጸመውን ግፍና መከራ የቤተክርስቲያንን ውድቀት እንዳይታደግ የምሽቱ አደንዝዥ ስብከት እያስጮሁና ሚሊዬን ስብስበው አለማቸውን የሚቀጩ የቤተመንግስቱ አምላኪ መምህር በሚል ስም የሚቀልዱ እየበበዛ ስለመጣ :: ወጣቱ የሚያየው ጸያፍ ነገሮችን በመሸሽ ሌላ ምኩራብ ለመሞከር እይተገድድ ነጎደ ::
    ዛሬ ጀንደርባ አእላፍ እየተባለ ማታ የምሽት ቤት ዘፋኝ ጠዋት ዘማሪ አርቲስት ተብዬዎችን ፊት አሰልፎ የሚመጣው ዳንኪራ በየቀኑ የሚታረዱት ሰማእታትንና የቤተክርስቲያንን መከራ አለም አውቆ ተቃውሞና በውግዘት ግፍና መከራውን ለማስቆም እንዳይረዳ አራጆቻችን የሚሰሩት የፕሮፓጋንዳ ስራን በትልቁ ለማገዝ የተዘጋጀ ሴራ ፕሮጄክት ነው ::
    ህሊና ያለውን ቤተክርስቲያንና ሰማእቱን ለማሰብን መጭውንም መከራ ለማስቆም ዛሬ ይሄንን አይነት የቄሳሮችን ለማስደሰት የተዘጋጀ ኮንሰርት ማውገዝ ኦርቶዶክሳዊነት ነው :: መታረዳችን ሳይበቃን ሳያንሰን የአራጆቻችንን ምስጋና ለማቅረብ ነጭ ለባሽ ሆኖ መጨፈር ለእህትቤተክርስቲያንና መሪዎችም ከግምት ያወጣል ::

    Reply
  • Abreham
    Abreham
    December 18, 2025 at 3:31 pm

    well done

    Reply
  • Yeabsira Daniel
    Yeabsira Daniel
    December 20, 2025 at 9:23 pm

    በእውነት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ወንድማችን!
    እስካሁን የሚነሱ ትችቶችን ስመለከት ወይ ግለሰብን ወይ ደግሞ ግልፅ ባልሆነ ጉዳይ ነበር። ከቤተ ክርስቲያን ስርዓት አንፃር ግን ፍፁም አልሰማውም። በዚህ ጽሁፍ ምን ያክል ለሥርዓተ አምልኮ መጨነቅ እና ነገራችንን ሁሉ ከዚህ አንፃር መመዘን እንደሚገባን ተምሬያለው። ድንቅ ነው እውነት!

    ጥቂት ጥያቄዎች ላንሳ :-
    1. መዝሙሮች አምልኮ መፈፀሚያ እንደሆኑ ይሰማኛል ፤ በዚህ ጽሁፍ ግን በቤተ ክርስቲያን ያላቸው ክብር ትንሽ እንደሆነ እንዲሰማኝ አድርጎኛል። በደንብ ግልጽ ቢሆን?
    2. የእኛ ቤተ ክርስቲያን ዜማዋን ከቅዱስ ያሬድ እንዳገኘችው ይታወቃል ፤ ያልደረሳቸው አሐት’ስ?
    3. የግዕዝ ቋንቋ ለቤተ ክርስቲያናችን እንደማንኛውም ቋንቋ ነው? ምክንያቱም ግዕዝ እና ግእዝ የሚሉትን ቃላት መምሕራን ሲፈቷቸው እንኳን የተለየ አድርጋ እንደምታየው ነው የተረዳውት?
    4. ከዚህ አጀንዳ ጋር በተያያዘ እንደ መፍትሄ ሃሳብ ለምን የአእላፋት ቅዳሴ ወይ ማኅሌት ቢሆንስ?

    Reply
  • Shimelis
    Shimelis
    December 21, 2025 at 4:43 pm

    ነገር ስለረዘመ የተጻፈውን ጽሑፍ ቅቡልነት ያስገኝለታል ማለት አየደለም። 23 ገጽ እጅግ ረጅም እና አሰለቺ ነው። ከዚህ ከመጠን በላይ የተንዛዛ ጽሑፍ ኹለት ነገሮችን ልክ ሆነው አግኝቻቸዋለኹ። የስፖንሰሮችን በወርቅ ዕጣን ከርቤ ደረጃ ስለመስጠት የሚተቸውን እና ምዕመኑን VIP እና ተራ ብሎ ቦታ ለይቶ ስለማስቀመጥ።
    ከአእላፋት ዝማሬ መርሃ ግብር ጋር የማይገናኙ ልክ ያልሆኑ ኩነቶችን (ለምሣሌ የአዉደ ምኅረት ልመና ወዘተ) ለምሳሌነት ጠቅሶ መተቸትና አእላፋት ዝማሬ ጋር ለማነጻጸር ሞከር ሌላዉ የጽሐፉ ስህተት ነዉ።
    ጸሐፊዉ ራሱን እንደገለጸዉ ብዙ ያነበበ እና ቤተ ክርሰቲያንን “ በደንብ የተረዳ ፣ አባቶች ዘመን ጀምሮ የነበረዉን ስርዓቷንም በሚገባ የሚያዉቅ ” ከሆነ የኢጃትን ምንነት እና ዓላማ የሚሰሩትንም ስራ ቀርቦ ማየት ፣መጠየቅ፣ መመርመር እና ማወቅ ይቻል ነበር። ያኔ ኢጃትን እቋም ይዞ መሞገት፣ መቃወም እና ማዉገዝ ይቻላል። ከሩቅ ቁጭ ብሎ በጥንት መነጽር እየተመለከቱ በዚህ ዘመን የሚከወኑ ኩነቶችን ከመረመሩ አንድም “ትክክል ነዉ” የሚባል ነገር እአይኖርም (የጥነቱ ስርአት ለክ እየደለም እያለኩ አይደለም)። መሬት ላይ የሚታይ ቁምነገር ሳይሰሩ የቤተክረስቲያንን ስርአቷን ስለሚያዉቁ ብቻ ሌሎች የሚሰሩትን ለመተቸት ሩቅ መንገድ መሄድ ብቻዉን ዋጋ አያሰጥም። አንተስ በዚ ሁሉ እውቀትህ የተሰራን ከመተቸት ያለፈ ምን ሰረተሀል? አስብሎ ያስጠይቃልና። ኢጃት የሚሰራቸዉ ዘደርፈ ብዙ ስራዎች ምንም እንከን የለባቸውም እያልኩም አየደለም። ነገር ግን በፈጣሪ እርዳታ ባለፉት 2 እና 3 ዓመታት የሰሩትን ስራ አለማድነቅ እና ለዚህም ፈጣሪን አለማመስገን ግን አላዋቂነት እነጂ ሊቅነት አይደለም።

    Reply
  • ዮናስ ጌታቸው
    ዮናስ ጌታቸው
    December 29, 2025 at 2:06 pm

    ጽሁፍህን ዘግይቼም ቢሆን ዛሬ አንብቤዋለሁ አንዳንድ ነጥቦችህም ነገሩን በሌላ አንግል እንድመለከታቸው አድርገውኛል። የምታነሳቸው ሃሳቦች እና ትችቶች ቤተክርስትያን ተኮር መሆናቸው እና ሙሉ ነገሩ ከሱ ጋር የተያያዘ መሆኑ በጣም ደስ ይላል ያሳሰቡህንም ጉዳዮች በጣም የምጋራቸው ናቸው። ግን ደግሞ ሃሳቦችህ ላይ (እንደኔ አረዳድ እና 21 ገጽ ጽሁፍ ለጻፈ ሰው) የአመክንዮ ችግር አይቼበታለው ይህም የነገሩን ዋና ማእከል ከመገምገም እናም ለሱ የሚያፈርስ ሃሳብ ከማቅረብ ይልቅ የከፋ ሁኔታን አሳይቶ ሌላ ችግር በመጥቀስ ከአእላፋት ዝማሬ ሁኔታ ጋር በመደባለቅ የነሱን ሃሳብ የማኮሰስ ሚዛናዊ ያልሆነ አካሄድ አይቼበታለው።
    እኔ እንዳጋጣሚ ሁለቱንም ያእላፋት ዝማሬ እናም ከዛም ቀጥሎ ማህሌቱንም ቅዳሴውንም ተሳትፍያለው እናም አንተ እንዳልከው ይህ አካሄድ ወይም የአእላፋት ዝማሬ ሚስተካከል ሳይሆን ራሱ እንደ ሚታረም ችግር ነው መታየት ያለበት ብዬ አላምንም። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንዳልኩት ያመክንዮ መዛነፍ ነው። አምክንዮህ ከመዝሙር እና ስብከት አሁናዊ ያለውን ነባራዊ ነገር ከመገምገም እና ከአእላፋት ዝማሬ ጋር ከማገናኘት እንደሚጀምር እኔ ተገንዝብያለው። ይህንንም የአመክንዮ መዛነፍ ያልኩበት ምክንያት የቀረበው ግምገማ ሰለ ዘመናዊ መዝሙር ጥቅምና ጉዳት ከማሳየት ይልቅ አሁን ያሉት መዝሙራት አስከፊ ጎናቸውን ብቻ የሚያሳይ እናም ጥሩዎቹ በጣም አንስተኛ እንደሆኑ የሚደመድም ሆኖ አይቼዋለው እሱንም እየተቃወምኩ ሳይሆን ይህንን ሁሉ ገጽ ላጻፈ ሰው ትንሽ የቁጥር መረጃ መቅረብ ነበረበት ባጠቃላይ መዝሙራት ላይ ይህንን መስራት ቢከብድ ራሱ አካሄዱ ለቤ/ክ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ይብሳል ብሎ እንደደመደመ ሰው ባለፉት ሁለት አመታት ላይ በአእላፋት ላይ የቀረቡትን መዝሙሮች ግጥም እና ዜማ ከዋናው ስርአት የራቀ እና የቢተክርስትያንን ትውፊት የወጣ መሆኑን ማሳየት ነበረበት ግን ይህንን ሳያደርጉ ለመደምደሚያህ የሚሆነውን ዋናውን ግብአት ሲመሰርት ይታያል። ይህም ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ የማስፈን እና የአእላፋት ዝማሬ እርማት ተሰጥቶት የሚቀጥል ሊሆን ይችላል የሚለውን ሌላውን አስተያየት ሊደፈጥጥ የሚችል ነው። እንደኔ ግምት ቢያንስ አንተ ባስቀመጥቀው ሰአት እንኳን 10 ሰአት ፕሮግራሙ ቢጀምር እናም እስከ 11 ሰአት ጸሎት ቢቀጥል ለ 4 ሰዓት ህዝብን ወደ ክርስትያናዊ ህይወት፣ ወደ ንስኃ እና ወደ መቅደስ ህይወት የሚመሩ ‘ዘመናው’ የመዝሙር ግጥም እና ዜማ ቤ/ክ የላትም ማለት ንፉግነት ይመስለኛል።
    ሁለተኛ ላይ ስለ ብዛት፣ ቁጥር እና ቦታ የተናገርከው ነው። እንደ ላይኛውም የነገሩን ዋና ማእከል አለመዳሰሰ ችግርንና ጉድፈትን አውርቶ (እውነት የሆነውን የብዙ ጉባኤዎች ንድፍ እግዚአብሄርንና ከ እርሱ ጋ መኖርን ማዕከል ከማድረግ ወጥቶ ብዛትን ማማከሉን በመዘርዘር) ከዋናው ሃሳብ መሸሽን፣ እናም አንድ አይነት አመለካከት ብቻ እንዲኖር እና የአተያይ ውስንነትን የሚያሳድር ሆኖ አግኝቼዋለው። ይህም የቁጥር ብዛትን እና አንድ ቦታን ማዕከል ያደረገን አገልግሎት ለሰይጣናዊ ሃሳብ እና ስብሰባ መስጠትን ነው። እንደኔ እውቀት እና መረዳት ሰው ሰውኛው ባያግዳቸው እና የተመቻቸ ሁኔታ ቢገኝ ጥምቀትን እና መስቀልን አባቶቻችን ያንድ አገር አደብራት አንድ ላይ ባንድ ቦታ ቢያከብሩ ነበር የትውፊቱ ንድፍ። ይህንንም ልል የቻልኩት ምንም ጥናት ባላረግበትም በዛ ጊዜ የነበረውን ደብር እና የህዝብ ቁጥር በማሰብ ነው። በርግጥ የአንድ ኦርቶዶክሳዊ ጉባኤ ሃሳብ እና ዲዛይን እግዚአብሄርን ማዕከል ያድርግ እንጂ በአንጻር ለትንሽ ሰው ዲዛይን የተደረገ እና ሚደረግ አይደለም፤ ሃሳብህ ይህንን ይላል እያልኩ ሳይሆን ትንሽ ወደዛ የማድላት እናም ነገሩን ገልብጦ ያለማሰበ እና የመደምደም ነገር ይታይበታል። በዘንድሮ ጊዜም በኢትዮጵያ ላይ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ጉባኤን (ከ አስተምህሮም ከ ባህሪም አንጻር) ቀርጾ በአንድ ላይ አድርጎ ህዝቡን ወደመጣበት ደብር በተወሰነ ጊዜ ማድረስ እና ለ ነባሩ እና ዋናው አገልግሎት ለማህሌት አብሶ ደግሞ ለቅዳሴው ሚደርስበትን ሁኔታ ላይ መስራት እና ማመቻቸት ማይቻል ነው ብዬም አላምንም።
    ሌላኛው ሃሳቤ በቤ/ክ የተለመደ እና የታወቀ የሰርክ ጉባኤ አለ ይህም ብዙ ጊዜ ከ 11፡30 እንከ 1፡00 ይሄዳል ግን በኔ እድሜ ልጅ እያለው በ 90 ዎቹ ላይ ባደኩበት ደብር ወልደ ነጎድጓድ ዮሃንስ በባዕላት ሰሞን አብሶ እስከ 3፡00 ድረስ ሚያመሽበት በጣም ብዙ ህዝብም ሚሳተፈበት ጊዜ ነበረ በዛ ጊዜ የነበሩ አገልጋዮችም ጉባኤው እንዳለቀ ወደ ቤተ መቅደስ ሚገቡ ሰዎች ነበሩ። እኔ በግሌ ጉባኤው አሁን ለመኖር ለምሞክረው ኦርቶዶክሳዊ ህይወት ጥቅም እንዳለው አምናለው። ይህንን ያነሳውት በገና ዋዜማ በትልቁ በአላችን በዛ ጊዜ የነበረውን የቀን ጉባኤ ትንሽ ለውጥ ተደርጎለት ተሰባስበን ስንዘምር እንድናመሽ አንድ ሃሳብ ቢቀረጽ የቆየውን ትውፊት ሚያፈርስ እና ሚጋፋ ላይታረም ሚችል እና መደገፍ የሌለበት ሃሳብ፣ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ መንገድ ነው ብሎ ለመደምደም ሚያበቃ ነገር ነው ብዬ ስላላየውት የቀረበውንም ማስረጃ ደካማ እንደሚያደርገው ስለተሰማኝ ነው፣ ባለፈው ጉባኤው በተደረገበትም ቤተክርስትያን ቦሌ መድኃንያለም በማህሌቱ እና በቅዳሴው የነበረው ቁጥር እና የቆረበውም ሰው ብዛት ብዙ ነበር። የማህሌቱን እና የቅዳሴውን ነገር እንዳላደበዘዘው ለማሳየት እንጂ ስለቁጥር ለማውራት አይደለም… በሌላ ቤተ/ክ የነበረውን ነገርም አጥንቶ ማየት እና ማሳወቅ ተገቢ የሆነን ነገርም እያሳዩ
    ሰለ VIP እና ሰለ ስፖንሰር ያነሳኽው ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ምቀበለው ነው።
    በኮሜንት ላይ እንደተጻፈ ሃሳብም ይቺን ልበል ብዬ ነው… እንደ አጠቃላይም እኔ ኢጃት የሚያስባቸው አሳቦች እና ፕሮግራሞች ጊዜውን መዋጀት ሚችሉ የሚከታተላቸውን ሰዎች እና ፕሮግራሙ የተቀረጸላቸውን ሰዎች ማዕከል ያደረገ (ይህ ምዕመንን ያለማወቅ ያለመረዳት የ ኤማሁስም ጭምር የብዙ ማህበሮች ችግር ነው) ሆኖ ነው ማገኛቸው ከብዙ ሌላ ማህበሮችም በተሻለ መልኩ … በገና ሳምንት ሲያደርጉ ያሰቡትን ነገሮች እንዳለ እና በዋነኛነት ደግሞ በገና ዋዜማ ቀኑን ለ ክርስቶስ መመደብ ሲዘምሩ ማምሽት ከዛም ወደማህሌት ሰውን እንዲሄድ ማድረግ እና ወደቅዳሴ እንዲገባ ማድረግ ለሁሉም ክርስትያን (በሃይማኖት ለሚኖረውም በስም ለተባለውም) መሆን የሚችል እና ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ሚችል ከዋናውንም አገልግሎት ጋር አብሮ ሚሄድ ቆንጆ ሃሳብ አድርጌ ነው እኔ ምረዳው… አመሰግናለው

    Reply
  • Hasset
    Hasset
    December 30, 2025 at 6:20 am

    ተባረክ ወንድም
    ሁሉም ነገር ከቤተክርስቲያን እና ከስርዓተ አምልኮ በኩል ካላላፈ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንደሚወስድ በደምብ አሳይተሃል። ሁልጊዜም ነገሮችን ሁሉ በቤተክርስቲያን አይን እስካላየን ድረስ መድረሻችን ስህተት ነው።
    የተቀመጠውም መፍትሔ ትክክለኛ እና ወደ መዳረሻችን የሚያደርሰን ነው። በርቱልን ለቤተክርስቲያን አስፈላጊዎች ናችሁ ብዙ የመስራት አቅምና እውቀት እንዳላችሁ እናምናለን። የቤተክርስቲያን አምላክ ሁሌም ይምራችው።

    Reply
Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

Guest Posts
መሐሪ ዘመልአክ

የአእላፋት ዝማሬ ምልክት ነው ።

መግቢያ በዘመናችን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታየው “የአእላፋት ዝማሬ” የተባለው ክሥተት ሰፊ የሆነ ሕዝባዊና ሊቱርጊያዊ ውይይት አስነስቷል። አንዳንዶች ይህን እንቅስቃሴ እንደ መንፈሳዊ ንቃትና የራቁ ምእመናን ተሳትፎ መመለሻ ሲያቀርቡት፣ ሌሎች ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሊቱርጊያ[1] ጋር የሚጋጭ እና ሥርዓታዊ መነሻዋን የሚያዳክም ክዋኔ እንደሆነ ይገምግሙታል። ወንድማችን በርናባስ ሽፈራው የጻፈው “የአእላፋት ዝማሬ”ን የተመለከተ የኤማሁስ ገጽ ጽሑፍ አንዳንዶችን ሲያበሳጭ፣ ሌሎችን ሲያሳስብ እንደሰነበተ በአረቦን ቴሌግራም ቻነል ላይ ተመልክቻለኹ። 23 ገጾችን የያዘ፣ ንዑሳን አርእስት በግልጽ ያልተሰጡት ረዥም ጽሑፍ ስለኾነ ጊዜ ሰጥቶ ማንበብን፣ ካነበቡም በኋላ ዐበይት መከራከሪያዎቹን ማጥለልን ይጠይቃል። እንዲኽም ኾኖ፣ ቢያንስ መሠረታዊ የኾነ የሊቱርጊያዊ ነገረ መለኮት (liturgical theology) ንባብ ለሌለው ሰው ጽሑፉ ከንቱ ምቀኝነት፣ መራራነት፣ አማራሪነት፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ ሊመስል ይችላል። በዋናነት እየነቀሰ የሚተቸው “የአእላፋት ዝማሬ”ን ልዩ ልዩ መልኮች ይኹን እንጂ፣ መሠረታዊ ጉዳዩ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአኹኑ ጊዜ ያለችበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ (liturgical crisis) መጠቆም ኾኖ አግኝቼዋለኹ። ጉዳዩ እኔንም ሲያሳስበኝ የነበረ ነገር ስለነበረ የበርናባስን ሐሳብ እንዲኽ ልለጥቀው ወደድኹ። የእኔ ጽሑፍ የ“የአእላፋት ዝማሬ”ን እንደ ምልክት በመመልከት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ የምትገኝበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ ይጠቁማል። በተለይም በቋንቋ ባዕድነት፣ በዜማ ውስብስብነትና በሰዓት ምቹ አለመኾን ምክንያት ምእመናን ከ“ሰዓታት ጸሎት” የራቁበትን ኹኔታና ኮንሰርታዊ ዝግጅቶች በተግባር የተኩት የሊቱርጊያ ባዶ (liturgical vacuum) ምን እንደሆነ ለማመልከትና መፍትሔውን ለማሳየት ይጥራል። The Problem of Reactive Ministry እና Institutional Survivalism በርናባስ በጽሑፉ የሚተቸው አንዱ ነገር ይኽ ተልእኮን

Read More »
Emmaus Posts
ኤልያስ ገብረ ሥላሴ

መከራ ፣ እከይ እና ክርስትና

መከራ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ድንገተኛ የሆነ ክስተት አይደለም ። ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ለጥቅማችን የሚፈቀድ የእርምት መንገድ ነው እንጂ ። በየዘመኑ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ሁነቶች እንድትወጠር እና መሠረታዊ ነገሮች ትኩረት እንዳያገኙ የሚቀርብ ፈተና አለ ። ሰበር ዜናዎች ፣ ወቅታዊ አጀንዳዎች ፣ አከራካሪ ጉዳዮች ወዘተ ከመነኩሴ መቁጠሪያ በላይ በሚሽከረከሩበት ዘመን ላይ ነው የምንገኘው ። እነዚህ ሁነቶች ትኩረታችንን ይወስዱትና ሳይታወቀን መሠረታዊ ከሆኑትና ዘለዓለማዊነታችንን ከሚበይኑት ጉዳዮች ወጥተን ምድራዊና እዚሁ ቀሪ በሆኑ ጉዳዮች ተወጥረን እንገኛለን ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁኔታ በቤተክርስቲያንን መምህራን እና “ተጽዕኖ ፈጣሪዎች” ላይ እጅግ በርትቶ የሚታይ መሆኑ እና በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እና መድረኮች ሳይቀር ሰፊውን ሰዓት መያዙ ነው ። የቤተክርስቲያን ተልእኮ ስለ ክርስቶስ ምስክር መሆን ነው ። መሠረታዊ ካልሆኑት ሁነቶች ወጥተን ወደዚህ ዋነኛ ተልእኮአችን እንድንመለስ ተዋሥኦ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ። ይህ በምእመናን ፥ በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲን አገልጋዮች ፥ ዘንድ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ። የሁነቶችን መሠረት መመርመርና ትክክለኛ ባሕርያቸውን መረዳት ያሻል ። ሁነቶቹ ችግሮች የሆኑ እንደሆነ ሥር ነቀል መፍትሔ ማሰብ የሚቻለው ፥ መልካም አጋጣሚዎችም ከሆኑ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ልናውላቸው የምንችለው የሁነቶቹን መሠረት በጥልቀት መረዳት ከቻልን ነው ። በመቀጠልም ተከትለው ሊደረጉ ስለሚገቡ ነገሮች መወያየት ከተቻለ ብቻ ነው ። ካልሆነ አሁን እየሆነ እንዳለው የወቅታዊ አጀንዳዎች አሳዳጅ ብቻ ሆነን ነው የምንቀረው ። በተለይ ዘመናችን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ስለሆነ በዚህ

Read More »
Emmaus Posts
መሐሪ ዘመልአክ

ከእውነት አልባነት ጋር የሚካሔድ ሙግት

(‘ሐሳቦች መዘዝ አላቸው’ በሚል ርእስ በኤማሁስ መጽሔት ቅጽ 1 ፣ ቁጥር 1 በወጣው ጽሑፍ ላይ የተጻፈ አስተያየት) በመሐሪ ዘመልአክ (PhD) ከዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት የእጓለ ገብረ ዮሐንስ ‘የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ’ ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበብኹ በኋላ ጸሐፊውን ከዚያ በፊት አለማወቄ ገርሞኝ እንደነበር አስታውሳለኹ ። ማን ናቸው ? እንዴት እስከዛሬ ድረስ ስለእርሳቸው ሳልሰማ ቀረኹ ? ለምን ? ይኼ በ1956 ዓ.ም. የታተመ የሬድዮ ንግግር ከኾነ መጽሐፍ ለመጻፍ ብለው ተነሥተው ቢጽፉ ኖሮ ምን ሊጽፉ ነበረ ? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎች ጭንቅላቴ ውስጥ ተመላልሰዋል ።[1] በኋላ ፈላስፋው ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተማሪና መምህር እንደነበሩ ስሰማ በመጽሐፉ ውስጥ ያየሁት የሐሳብ ጥልቀት በዘመኑ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልሒቃን ዘንድ የነበረው ተዋሥኦ ሊደርስ ይንጠራራበት የነበረውን ልክ የጠቆመኝ መሰለኝ ። ከዚያ በኋላ ያ የተዋሥኦ ልሕቀት የት ገባ ? እንዴት ድርቅና የተጫነው ተዋሥኦ ዋጠው ? እንዴት ኦርቶዶክሳዊነትን ከአመክንዮ የተፋታ እና አመክንዮን የሚፈራ ጭፍን እምነት የሚያስመስሉ የፎክሎር ሰባኪዎች ተፈለፈሉብን ?  የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህን ለመኾን የሚጠየቀው መስፈርት ስለምን ድፍረት የለበሰ አላዋቂነት መሰለ ? በሚዲያ ላይ ሲናገሩ በአላዋቂነታቸው አንገታችንን የማያስደፉን ካህናት ስለምን ቁጥራቸው አልበረክት አለን ? ኦርቶዶክሳዊነት ችግርን እና ጭንቀትን ለማረሳሳት የተጠመቀ ዕፀ-ዝንጋዔ (‘opium of the masses’) እስኪመስል ድረስ በኦርቶዶክሳዊነት ስም የገነነው ተዋሥኦ ለምን አላዋቂነት ተጫነው ? ቤተ ክርስቲያን ሲባል ከስሜታዊ ሙጥኝታ (sentimental attachment) ባለፈ ለሰው ልጅ ህልውናዊ ጥያቄ የተሰጠ ከሞት ፍርኃት

Read More »
Emmaus Posts
ኤማሁስ

የኤማሁስ መንገድ

መጽሔቷን ለማግኘት ይህን ይጫኑ . . . የዘመናችን ተዋሥኦ በይዘቱም ሆነ በመንገዶቹ በግልብነት በእጅጉ የተጠቃ ነው ። ‘በይዘቱ እንዴት ?’ቢባል ሁነቶች ላይ ያተኮረ እና ወቅታዊነትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ። አንድም አቋም ከመያዝና ጎራ ከፍሎ ከመናቆር ባለፈ የእውነት የመማር እና የማሰላሰል ጉጉት የማይታይበት በመሆኑ ። በዚህ ተዋሥኦ ውስጥ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሣት እና ከሁነቶቹ የሚሻገር እና ሐሳባዊ የሆነ ትንተና ለማካሔድ መሞከር ትኩረት ያስነሣል ፤ ሲብስም አጉል እንደመራቀቅ ይታያል ። የሚካሄድበት ከባቢ እና ዘመን ደግሞ ሌላ ግልብነት ደርቦለታል ። በእኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሀገራት ፣ ከዘመናዊነትና ከቴክኖሎጂ መራቀቅ ጋር ተያይዞ ሕዝባዊ ተዋሥኦ በጠቅላላው ስለቱን እና ርቀቱን እንዲያጣ ሆኗል ። የሚነበብም ሆነ የሚታይ ወይም የሚደመጥ ነገር አጭር መሆን አለበት ። ነገር ግን ጠቃሚና ወሳኝ ርእሶች እንዲህ ባለ መንገድ ሊስተናገዱ አይችሉም ። የሚያጠግብ ፍሬ ከሌለበት የተመልካቹ እና የአንባቢው ብዛት ምን ጥቅም ይኖረዋል ? እንዲህ ባለው ከባቢ ውስጥ ሁነቶችን ከሁነትነታቸው እና ከሚያመጡት ወቅታዊ ውጤት በተሻገረ መልኩ ለመመልከት እንቸገራለን ። ቀድሞውኑም (እይታችን ከመጥበቡ የተነሣ) ጠባብ አድርገን የቀረጽነውን አጀንዳ በምንገልጽበት መንገድ የበለጠ እናጠብበዋለን ። ነገር ግን ሁነቶችን እና ሒደቶችን ከመሠረታቸው መመርመራችን እና የምናቀርባቸው መፍትሔዎችም እንዲሁ የማይናወጥ መሠረት ያላቸው መሆናቸው አስፈላጊ ከሆነ ተዋሥኦውም እንዲሁ የጠለቀ እና የረቀቀ መሆን አለበት ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ጊዜ ወስዶ ማሰብ ፣ ማንበብ ፣ ማጠናቀር ፣ መወያየት ፣ መሟገት እና እንዲህ ካለው ሒደት

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

ክፍል ፭ ፡ ወደ ርስታችን ያልተመለስንበት ኢዮቤልዩ

ሩሲያዊው ደራሲ ፌዮዶር ዶስቶየቭስኪ በ1860ዎቹ አውሮፓን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኝ የታዘበውን በዘገበበት ማስታወሻው የለንደን ድሆች ቅዳሜ ማታን እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያሳልፉ ይነግረናል ። በቅድሚያ ሌሊቱን በሙሉ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ጭምር ደስታ ፈጽሞ በተለየው ፣ ድብርት በተጫነው መንፈስ አኳዃን ሲበሉ እና ሲጠጡ ፣ ከሕይወታቸው መራራነት ለማምለጥ ፣ ራሳቸውን ፍጹም ለማደንዘዝ በሙሉ ጥምብዝ እስኪሉ እንደሚሰክሩ መስማቱን ይዘግባል ። ሳምንቱን ሙሉ ሠርተው የቋጠሯትን ገንዘብ ቅዳሜ ሌሊት እንዲህ ይበትኗታል ። አስከትሎም እንዲህ ባለው አንድ ምሽት እሱ ራሱ በመንደራቸው ውስጥ ሲያልፍ የታዘበውን እና የተሰማውን እንደሚከተለው ይመሰክራል ። “One such night – it was getting on for two o’clock in the morning – I lost my way and for a long time trudged the streets in the midst of a vast crowd of gloomy people, asking my way almost by gestures, because I do not know a word of English. I found my way, but the impression of what I had seen tormented me for three days afterwards. The populace is much the same anywhere, but there all was so vast, so vivid that you almost physically felt things which up till then you had only imagined. In London, you no longer see the populace. Instead, you see a loss of sensibility, systematic, resigned and

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

ብያኔን አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ

ከሁለት ሳምንታት በፊት ‘ከጥያቄዎቹ በላይ አደገኛ የሆኑት መልሶች’ በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ አቅርበን ነበር ። ጽሑፉ በዋናነት ማሳነስ (reductionism) የተባለውን ፅንሰ ሐሳብ የሚያነሣ እና የሚተች ነው ። በዚህ ጽሑፋችን ውስጥ መምህር ያረጋል አበጋዝ በቅርቡ ‘ወደ ላይ አያዳልጣችሁ’ በሚል ርእስ ገዳማዊ ሕይወትን ከዘነበ ወላ ዘለፋ ለመከላከል ጽፎ ያጋራውን ጽሑፍ ተችተናል ። ርእሱን በዚህ ጊዜ ጉዳይ ያደረግነውም በዋናነት በምምህር ያረጋል ጽሑፍ ምክንያት ነው ። በተለይ ጽሑፉ ሰፊ ተነባቢነት እና ተቀባይነት ያገኘ እንደ መሆኑ በውስጡ ያየነውን የማሳነስ ዝንባሌ መተቸቱ ጠቃሚ ይሆናል ብለን አመንን ። ነገር ግን የመምህር ያረጋል ጽሑፍ መነሻ ቢሆነንም በይበልጥ ፅንሰ ሐሳቡ ላይ ለማተኮር ነው የሞከርነው – ዓላማችን ነገሩ ላይ ተዋሥኦ እንዲጀመርና የተሻለ መረዳት እንዲፈጠር ማድረግ ስለሆነ ። መምህር ያረጋልም ጽሑፉን ተመልክቶ ምላሽ ሰጥቶናል ። ምላሽ በመስጠቱ ደስ ብሎናል ። በምላሹ ግን አልተደሰትንም ። አለመደሰታችን እኛ በእርሱ ጽሑፍ ላይ ያቀረብነውን ትችት ባለመቀበሉ አይደለም ። ይልቁንም የተሰጠው ምላሽ ከእኛ ትችት ጋር እምብዛም የተያያዘ ባለመሆኑ እንጂ ። ከነገሩ ጋር የማይገጥሙ ምሳሌዎች ቀርበዋል ። ያቀረብነው ሂስ በተሳሳተ መንገድ ተተርጉሟል ። በጽሑፋችን በስም ጠርተን ያራቅነው እና ያነወርነው ሐሳብ የእኛ አቋም ተደርጎ ተገልጧል ። “ለቤተ ክርስቲያን ከልባችን ከመጨነቅና ከመቅናት” ተነሥተን “ያልተባለውን ለማስመሰል በመድከማችን” ተወቅሰናል ፤ ዕጣችን ሆኖ “ሳንነቅፍ መጻፍ አልቻልንምና” ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች መልስ እና እርማት የሚሹ ሆነው አግኝተናቸዋል ። አንድም ለእኛም ሆነ ለመምህር ያረጋል

Read More »