ብያኔን አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ

ከሁለት ሳምንታት በፊት ‘ከጥያቄዎቹ በላይ አደገኛ የሆኑት መልሶች’ በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ አቅርበን ነበር ። ጽሑፉ በዋናነት ማሳነስ (reductionism) የተባለውን ፅንሰ ሐሳብ የሚያነሣ እና የሚተች ነው ። በዚህ ጽሑፋችን ውስጥ መምህር ያረጋል አበጋዝ በቅርቡ ‘ወደ ላይ አያዳልጣችሁ’ በሚል ርእስ ገዳማዊ ሕይወትን ከዘነበ ወላ ዘለፋ ለመከላከል ጽፎ ያጋራውን ጽሑፍ ተችተናል ። ርእሱን በዚህ ጊዜ ጉዳይ ያደረግነውም በዋናነት በምምህር ያረጋል ጽሑፍ ምክንያት ነው ። በተለይ ጽሑፉ ሰፊ ተነባቢነት እና ተቀባይነት ያገኘ እንደ መሆኑ በውስጡ ያየነውን የማሳነስ ዝንባሌ መተቸቱ ጠቃሚ ይሆናል ብለን አመንን ። ነገር ግን የመምህር ያረጋል ጽሑፍ መነሻ ቢሆነንም በይበልጥ ፅንሰ ሐሳቡ ላይ ለማተኮር ነው የሞከርነው – ዓላማችን ነገሩ ላይ ተዋሥኦ እንዲጀመርና የተሻለ መረዳት እንዲፈጠር ማድረግ ስለሆነ ።

መምህር ያረጋልም ጽሑፉን ተመልክቶ ምላሽ ሰጥቶናል ። ምላሽ በመስጠቱ ደስ ብሎናል ። በምላሹ ግን አልተደሰትንም ። አለመደሰታችን እኛ በእርሱ ጽሑፍ ላይ ያቀረብነውን ትችት ባለመቀበሉ አይደለም ። ይልቁንም የተሰጠው ምላሽ ከእኛ ትችት ጋር እምብዛም የተያያዘ ባለመሆኑ እንጂ ። ከነገሩ ጋር የማይገጥሙ ምሳሌዎች ቀርበዋል ። ያቀረብነው ሂስ በተሳሳተ መንገድ ተተርጉሟል ። በጽሑፋችን በስም ጠርተን ያራቅነው እና ያነወርነው ሐሳብ የእኛ አቋም ተደርጎ ተገልጧል ። “ለቤተ ክርስቲያን ከልባችን ከመጨነቅና ከመቅናት” ተነሥተን “ያልተባለውን ለማስመሰል በመድከማችን” ተወቅሰናል ፤ ዕጣችን ሆኖ “ሳንነቅፍ መጻፍ አልቻልንምና” ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች መልስ እና እርማት የሚሹ ሆነው አግኝተናቸዋል ። አንድም ለእኛም ሆነ ለመምህር ያረጋል ጽሑፍ ከተሰጡት ምላሾች አንዳንድ ጉዳዮችን ማጥራት እንደ ሚያስፈልግ ተረድተናል ። የመምህር ያረጋልን ጽሑፍ ድረ ገጻችን ላይ ከለጠፍነው በኋላ ያስተዋልነው አንድ አስገራሚ ነገር ብዙ ሰዎች የእኛን ትችት ትተው የእሱን መልስ ብቻ ያነበቡ መሆናቸው ነው ። ይህ ስላለንበት ሁኔታ ብዙ የሚናገር ይመስለኛል ። እንዲህ ያሉት ሰዎች ከዚህ ጽሑፍም ሆነ በጠቅላላ ከሚደረገው ተዋሥኦ ምንም ያህል የሚጠቀሙ አይመስለንም ። የሆነ ሆኖ ግን ከልብ መረዳትን ለሚሹት እንጽፋለን ።

በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ ፣ መምህር ያረጋል በጽሑፉ ላይ ያቀረብነውን ትችት በትክክል የተረዳው ይመስላል ። “እንደ ገባኝ ከሆነ፣ ዋናው ትችት፣ ጽሑፉ ገዳማዊ ሕይወት በኢኮኖሚ፣ በታሪክና መሰል ዘርፎች ያደረጋቸው አስተዋጽኦዎች መጠቀሳቸውና በዚህ አንጻር መልስ መሰጠቱ፣ ገዳማዊ ሕይወትንና ክርስትናን ወደ ምድራዊ እሳቤና መለኪያ ዝቅ የሚያደርግ (reductionist) ነው የሚል ነው።”

በትክክልም ትችታችን ይህ ነው ። ነገር ግን መምህር ያረጋል ይህን ትችን አይቀበለውም ፤ ያለአግባብ የተሰነዘረ ነው ባይ ነው ። ይህንም ለማስረዳት ከወንጌል አንድ ፣ ከሐዋርያት ሥራ አንድ እንዲሁም አራቱ ወንጌላውያን የጻፉበትን መንገድ በማነጻጸር ሦስተኛ ምሳሌ ይሠጣል ። ነገር ግን ምሳሌዎቹን የእኛ ትችት የተገባ እንዳልሆነ ሳይሆን መምህር ያረጋል የእኛን ትችት በትክክል እንዳልተረዳው የሚያሳዩ ሆነው ነው ያገኘናቸው ።

በመጀመሪያ የቀረበውን ምሳሌ እንመልከት ።

“ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዱቃውያን ቀርበው ስለ ትንሣኤ ሙታን ጉዳይ ጥያቄ በጠየቁት ጊዜ የመለሰላቸው “ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን፣ እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም” ብሎ ነበር። ማቴ. 22፡31-32 ይህ ጌታችን የጠቀሰው ቃል የሚገኘው በኦሪት ዘጸአት 3፡6 ነው። ጌታችን ስለ ትንሣኤ ሙታን ጉዳይ ላነሡት ጥያቄ ሲመልስላቸው፣ ስለ ትንሣኤ ሙታን በግልጽ ከተናገሩት ከነቢያት መጻሕፍት በመጥቀስ ፋንታ ለምን ከዘጸአት ጠቀሰላቸው? ብንል ምክንያቱ ሰዱቃውያን ከአምስቱ የሙሴ መጻሕፍት በቀር የነቢያትን መጻሕፍት ስለማይቀበሉ ነበር። ስለዚህ ከሚቀበሉት መጽሐፍ ጠቅሶ ስህተታቸውን አስረዳቸው አንጂ ከማይቀበሉት መጻሕፍት ጠቅሶ ላስረዳችሁ አላለም።

“ሆኖም ለሰዱቃውያን ከነቢያት መጻሕፍት አለመጥቀሱ ግን የእነርሱን ስህተት በማጽደቅ ወይም ወደ እነርሱ እሳቤ ዝቅ በማለት (reductionism) ያስወቅሰዋልን? ኧረ በጭራሽ! መድኃኒት የሚሰጠው እንደ ሕመሙ ሁኔታና በሽተኛው በሚያስፈልገው ልክ እንጂ በሐኪሙ እውቀት ልክ አይደለምና! አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ደግሞ “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ” እያለ አስተምሯል። ማቴ. 5፡17”

እንደተረዳሁት ከሆነ መምህር ያረጋል ይህን ምሳሌ ያመጣው እሱ ዘነበ ወላን ከማይቀበለው ነገር (የምንኩስና ምንነትና መሠረታዊ ዓላማ) ይልቅ በሚቀበለው (የገዳማት ኢኮኖሚያዊ ፣ ታሪካዊ ወዘተ “አስተዋጽዖዎች”) በኩል ሔዶ ማስረዳቱ እና ጌታችን ለሰዱቃውያን ከማይቀበሏቸው (የነቢያት) መጻሕፍት ይልቅ ከሚቀበሏቸው (የኦሪት) መጻሕፍት ጠቅሶ ከማስረዳቱ ጋር ተመሳሳይ ነው ብሎ ስላሰበ ነው ። ነገር ግን ይህ ንጽጽር እንዴት ተገቢ ሊሆን ይችላል ? የምንኩስና ዋና ዓላማ እና የገዳማት ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ “አስተዋጽዖዎች” ከነቢያትና ከኦሪት መጻሕፍት ጋር የሚነጻጸሩ ናቸው ? ልክ ኦሪትና ነቢያት በእኛ ዘንድ እኩል ሥልጣን እንዳላቸው ሁሉ የምንኩስናን ዋና ዓላማ እና የተባሉትን ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ “አስተዋጽዖዎች” እኩል አድርገን እንቆጥራቸዋለን ? ነቢያት ዋና ፣ ኦሪት ደግሞ ትርፍ ናቸውን ? መምህር ያረጋል እንዳለው “ምናኔያዊ ሕይወት መሠረቱና ዓላማው ቁሳዊ ሀብት ማከማቸትና በዚህ ዓለም መበልጸግ” እስካልሆነ ድረስ እንዴት ከዚህ መነሻ አንጻር ያቀረባቸውን ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ “አስተዋጽዖዎች” ከኦሪት መጻሕፍት ጋር ያነጻጽራቸዋል ? የኦሪት መጻሕፍት ‘ቢኖሩ መልካም – ቢቀሩም ግን ምንም አይደል’ የምንላቸው ናቸው ?

አንድም ጌታችን ለሰዱቃውያን ከኦሪት መጻሕፍት ጠቅሶ ቢመልስ ኦሪትን በተመለከተ ከሰዱቃውያን ጋር ስምምነት ስለነበረው ነው ። መቼም ጌታችን ለሰዱቃውያን ኦሪትን እንደጠቀሰው – ሙስሊሞች (አለመቻሉ ጠፍቶኝ አይደለም – ለነገሩ እንጂ) ሔደው ቢጠይቁት ከኦሪት እንደጠቀሰው  ከቁርዓን ጠቅሶ ያስረዳቸው ነበር አንልም ። ነጥቡ ግልጽ ይመስለኛል – የጋራ መነሻ ያስፈልጋል ።  ታዲያ መምህር ያረጋል (እና ክርስቲያኖች በጠቅላላው) የተነሣውን ጉዳይ በተመለከተ ከዘነበ ወላ ጋር የምንጋራው መነሻ ምንድነው ?

ዘነበ ወላ ‘በእስልምና ምንኩስና አለመኖሩ ሥራ እንደሚከበር ያሳያል’ ሲል ‘መነኮሳት ሥራ ፈት ናቸው’ እያለ ነው ። መምህር ያረጋል ደግሞ በበኩሉ መነኮሳት ሥራ ፈት አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው የገዳማትን ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ “አስተዋጽዖዎች” የዘረዘረው ። ይህን ሲያደርግ በሥራ ምንነት ከዘነበ ወላ ጋር እየተስማማ ነው ። ስህተቱም እዚህ ጋ ነው ። ምክንያቱም ዘነበ ወላ ‘ሥራ’ ሲል እና እኛ ‘ሥራ’ ስንል ተመሳሳይ ነገር እያልን አይደለምና ።

‘Loaded question’ የሚባል የአመክንዮ ግድፈት አለ ። ጥያቄው በውስጡ ስሑት የሆነን መነሻ ርቱዕ እንደሆነ አድርጎ ይዞ ይመጣል ። ስለዚህም ወደ ኋላ ሔዶ ይህ መነሻ ካልታረመ በስተቀር እንዲህ ላለው ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ያን መነሻ ተቀብሎ መነሣቱ ይሆናል ። አንድ ሰው መጥቶ “ማጨስ ተውህ እንዴ ?” ብሎ ቢጠይቃችሁ – ማጨሳችሁን የታወቀ ሐቅ አድርጎ እየጀመረ ነው ። ስለዚህ እንዳመቻቸላችሁ ‘አዎ’ ወይም ‘አይደለም’ ብላችሁ ልትመልሱለት አትችሉም ? አንድ እርምጃ ወደኋላ ተራምዳችሁ “የት ሳጨስ አየኸኝ ?” ማለት ሊኖርባችሁ ነው ። ዘነበ ወላም ‘በእስልምና ምንኩስና የለም ፤ ይልቁንም ሠራተኞችን ያከብራል’ ሲል መነኮሳት ተቀምጠው ይውላሉ እያለ አይደለም ፤ ይልቁንም ‘ሀብት በሚያመጣ ድርጊት ላይ አልተሰማሩም ፤ የተጠመዱባቸው ተግባራት ፍሬ ቢስ ናቸው’ እያለን ነው ። ለእርሱ ሥራ ማለት ገንዘብና ሀብት የሚገኝበት ነገር ነው ፤ ይህ ነው “ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ አስተዋጽዖ” ማለት ። ስለዚህም ጾም ፣ ጸሎት ፣ ማኅሌት ፣ ቅዳሴ ወዘተርፈ ሥራ አይደሉም ፥ ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ “አስተዋጽዖ” የላቸውም ። ለዚህ ልንሠጥ የሚገባን መልስ የዘነበን የሥራ ብያኔ ውድቅ የሚያደርግ እና ክርክሩን ወደዚህ ስሑት መነሻው የሚወስድ አይደለምን ? ‘አይ ፣ መነኮሳት እኮ አንተ ሥራ ብለህ የምትቆጥረውንም ነገር ይሠራሉ’ ብለን ከተከላከልንማ – የዘነበ ወላን ስሑት ብያኔ እየተቀበልን ነው የሚሆነው ። በመምህር ያረጋል መልስም የሆነው ይኸው ነው ።

ነገሩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ አንድ ምሳሌ ላምጣ ። ለምሳሌ አንድ ታክሲ አይቶ የማያውቅ ሰው ታክሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢያይና ረዳቱ ሲጠራ ፣ ሲወርድ ፣ ሲወጣ ፣ በር ሲከፍት ፣ ሲዘጋ ፣ ብሎም ሒሳብ ሲሰበስብ አይቶ ፥ ሹፌሩ በተቃራኒው ጋቢና ምቹ ወንበር ላይ ተቀምጦ ረዳቱን ሲያዝና ሲዝናና የሚውል ቢመስለውና ሹፌሩን እንደ ሥራ ፈት ፣ ረዳቱን እንደ ባተሌ ቢቆጥረው ምን ትመልሱለታላችሁ ። ሹፌሩ ሠራተኛ መሆኑን ለማስረዳት ከረዳቱ ጋር ፉክክር ውስጥ መግባት ወይም ከእርሱ ጋር ምስስሎሽ መፍጠር መፍትሔ ይሆናል ?

መፍትሔው ጠያቂው የያዘውን ስሑት የሥራ ብያኔ ማስጣል ነው ። አለበለዚያ መግባባት ላይ መድረስ የሚቻለው ይህን ስሑት ብያኔ (በማወቅም ይሆን ባለማወቅ) በማጽደቅ ብቻ ነው ። የመምህር ያረጋል ምላሽም ተገቢ አይደለም ብለን የምናስበውም የዘነበ ወላን ስሑት የሥራ ብያኔ ሳያውቀው የሚቀበል በመሆኑ ነው ። ምክንያቱም የመነኮሳቱ የምሥጢርና የምስጋና ተግባራት እንደ ሥራ እስከ ተቆጠሩ ድረስ ሠራተኛ ለመባል ዘነበ ወላ ሥራ በሚላቸው ተግባራትም እንደሚጠመዱ ለማስረዳት ባልደከምን ነበር ። የተሳሳተውን የሥራ ብያኔ ስናርም ፣ በትክክለኛው ብያኔ መሠረት መነኮሳቱን አገልግሎታቸው ብቻ ትጉህ ሠራተኞች ያደርጋቸዋል ። አንዴ ይህን ካደረግን በኋላ “ግን አንተ በምትለውም ቢሆን” ብሎ ወደ ተሳሳተው ብያኔ ተመልሶ እና እሱን መሠረት አድርጎ መከራከር ለምን ያስፈልጋል ?

ስለዚህ ጌታችን ለሰዱቃውያን ኦሪትን ጠቅሶ ቢመልስላቸው – ኦሪትን እርሱም ስለተቀበላት (ስለሰጣትም) ነው ። እኛ ግን የዘነበ ወላን የሥራ ብያኔ የማንቀበለው በመሆኑ መምህር ያረጋል የሱን የሥራ ብያኔ ተቀብሎ መልስ መስጠቱ ጌታ ካደረገው ነገር ጋር ተመሳሳይ አይደለም ። በመሆኑም ምሳሌው ከነገራችን ጋር የገጠመ ሆኖ አይገኝም ።

ይልቁንም መምህር ያረጋል ምሳሌ አድርጎ የተጠቀመበትን ይህን ታሪክ ጥቂት መስመሮች ከፍ ብለን ብናነበው ለነገራችን የሚጠቅም ነገር እናገኝበታለን ። ሰዱቃውያን በሕይወት ሳለች ሰባት ወንድማማቾችን አግብታ ሁሉም የሞቱባትን ሴት ታሪክ ይተርኩና ይህች ሴት በመንግሥተ ሰማያት የማንኛቸው ሚስት እንደምትሆን ይጠይቁታል ። ይህ ጥያቄያቸው ቅድም loaded question ያልነው ዓይነት ጥያቄ ነው ። በመንግሥተ ሰማያት መጋባት እንዳለ አድርገው በመቁጠር ነው ጥያቄውን ያቀረቡለት ። ጌታችን ግን መነሻቸውን ተቀብሎ አልመለሰም ፤ አረማቸው እንጂ ፥ በመንግሥተ ሰማያት ማግባትና መጋባት የለም ሲል ። ከዚያ በኋላ ነው ዋናውን ሐሳባቸውን – ትንሣኤ ሙታን አለመኖሩን – ኦሪትን ጠቅሶ ውድቅ ያደረገባቸው ። ማግባትና መጋባት የለም ካለ በኋላ ወደኋላ ተመልሶ “ግን ቢኖር ራሱ” ብሎ መልስ አልሰጠም ።

መምህር ያረጋል ፥ እኛም በቀደመው በጽሑፋችን ልብ እንዳልነው ፥ የገዳማዊ ሕይወት ዓላማ ቁሳዊ ብልፅግናን ማስገኘት እንዳልሆነ ጠቅሷል ። እኛም ይህን መጥቀስ ዘንግቷል ብለን አልተቸነውም ። ነገር ግን አንዴ ይህን ካለ – “በተባለው ነገርም ቢሆን” ብሎ ለምን ወደ ኋላ ይመለሳል – “የተባለው ነገር” ስሑት መነሻ ያለው ሆኖ ሳለ ? ጾምና ጸሎት ፣ ቅዳሴና ማኅሌት ወዘተርፈ ሥራ ፈትነት አይደሉም ካልን በኋላ – “ግን እንዲያም እንኳን ቢባል” ብለን መቀጠል ይገባናል ?

መምህር ያረጋል ቀጥሎ ምሳሌ አድርጎ ያቀረበው አራቱ ወንጌላውያን የየራሳቸውን ወንጌል በተለያየ መንገድ መጀመራቸውን እና ትኩረታቸውም በተለያዩ ነገሮች ላይ ማረፉን ነው ። ‘አንዱ የጻፈውን አንዱ መግደፉ ያስተቸዋል ወይ? አንዱ ትኩረት የሰጠውን አንዱ ትኩረት መንፈጉ ያስነቅፈዋል ወይ ?’ የሚል ነው ።

ይህን ምሳሌ ሕጹጽ ነው ለማለት ራሱ እንቸገራለን ። ምክንያቱም ከእኛ ትችት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለምና ። የእኛ ትችት መምህር ያረጋል በጽሑፉ የገዳማዊ ሕይወትን አንዱን ገጽታ አጉልቶ ለሌላው ትኩረት ነፈገ ፥ ወይም የገደፈውና በደንብ ያላብራራው ነገር አለ የሚል አይደለም ። ይልቁንም በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን መባል የሌለበትን ነገር ብሏል የሚል ነው እንጂ የማብራሪያ እጥረት ወይም ለአንድ ወይም ለሌላ ነገር አጽንዖ የመስጠት ጉዳይ አይደለም ። ከላይ እንዳሳየነው መምህር ያረጋል ለገዳማት ኢኮኖሚያዊ ፣ ታሪካዊ ወዘተርፈ “ጠቀሜታዎች” ትኩረት ሰጠ የሚል ቅሬታ አይደለም ያቀረብነው ፤ ይልቁንም በመምህር ያረጋል መልስ ውስጥ እነዚህ ነገሮች በመዘርዘራቸው ፣ በዘነበ ወላ ነቀፋ ውስጥ የተቀበረው ‘የምሥጢራትና የምስጋና አገልግሎቶች ዋጋ ቢስ ናቸው’ የሚል ስሑት መነሻ ቅቡልነት እንዲያገኝ ሆኗል የሚል ነው ።

የመምህር ያረጋል ሦስተኛ ምሳሌ ከእሱ ይልቅ እኛን የሚደግፈን ይመስለኛል ። ቅዱስ ጳውሎስ ከአቴና ሰዎች ጋር ባደረገው ተዋሥኦ – መምህር ያረጋል እንደጠቀሰው “ለማይታወቅ አምላክ” የሚል ጽሕፈት ያለበት መሠዊያ ማግኘቱን መነሻ አድርጎ ተጠቅሟል ። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ሲያደርግ ከአቴናውያን ጋር የተጋራው መነሻ ምንድነው ? አለማወቃቸውን ። እሱም እርሱ የሚያውቀውን እነርሱ ግን የማያውቁትን ሊሰብካቸው ሔዷልና ። ይህን በማድረጉም እነርሱን ወደ እርሱ መነሻ ስቦ ሊያመጣቸው ጣረ እንጂ ወደ እነሱ መነሻ አልሔደም ። ዚውስ ወይም አፖሎን እንደ መነሻ አለመጠቀሙን ልብ ይሏል ። ይልቁንም ራሳቸው ባመኑት በአለማወቃቸው በኩል ሔዶ የሚያውቋቸው የመሰላቸውን – ዚውስንና አፖሎን ፣ ሌሎቹንም “አማልክቶቻቸውን” ከሕሊናቸው ሊያስወግድ ሞከረ እንጂ ። አሁንም በድጋሚ እንጠይቅ – መነሻ ይሆነን ዘንድ ከዘነበ ወላ ጋር የምንጋራው ነገር ምንድነው ? መምህር ያረጋል እኮ ዘነበ አላውቀውም ባለው ነገር በኩል ሳይሆን እንደ ዚውስ እና አፖሎ ሐሰተኛ አምላክ አድርጎ የተቀበለውን የኢኮኖሚ ብልፅግናን መሠረት አድርጎ ነው ጥያቄውን ለመመለስ የሞከረው ። ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ የተጠቀመውን መንገድ እና እርሱ ለዘነበ መልስ ለመስጠት የሔደበት መንገድ ተመሳሳይ ናቸው ማለት አይቻልም ።

መምህር ያረጋል እነዚህን ምሳሌዎች በማምጣቱ ትችታችንን አልተረዳውም ብለን ለማሰብ ተገድደናል ። ከላይ እንደጠቀስሁት በጠቅላላው ሲገልጠው የተረዳው ቢመስልም ፥ ምሳሌዎቹ ግን ሕጹጽ እና ከእኛ ትችት ጋር ያልተገናኙ ናቸው ። ይልቁንም ጌታም ሆነ ወንጌላውያኑ ወይም ቅዱስ ጳውሎስ ያደረጉት ነገርና እርሱ ለዘነበ ወላ የሰጠው ምላሽ አላቸው ብሎ ያሰበው ምስስሎሽ የላቸውም ። እንደገባኝ ከሆነ በዘነበ ነቀፋ ውስጥ ስሑት መነሻ የተቀበረ መሆኑን እና እሱ የሰጠው ምላሽ ያን ስሑት መነሻ መቀበልን ግድ እንደሚል የተረዳ አልመሰለኝም ። ከምሳሌዎቹ የተከተለው አባባሉም ይህን ግምቴን የሚያጠናክር ነው ።

“ስለሆነም በዘነበ ወላ ላይ የተጻፈችው ትንሽ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ስለ ክርስትና “ሀሁ” ለማስተማር ወይም ስለ ምንኩስና ምንነት ፊደል ለማስቆጠር አይደለም። ሆኖም ምናኔያዊ ሕይወት መሠረቱና ዓላማው ቁሳዊ ሀብት ማከማቸትና በዚህ ዐለም መበልጸግ አለመሆኑ ሳይጠቀስ ግን አልታለፈም። ሆኖም የተነሣውን ጉዳይ ችላ ብሎ ባልተነሣ ጉዳይ ላይ ብዙ መድከም ዒላማውን የሳተ ስለሚሆን (ያልበላውን ማከክ እንደሚባለው)፣ በዚህም ላይ ገዳማት በሚባለው ጉዳይ ላይም ቢሆን የሚያኮራ ተጨባጭ ታሪክ የሌላቸው ስላልሆኑ፣ ይህ መብራራቱ “ከጥያቄዎቹ በላይ አደገኛ የሆኑት መልሶች” ሊያሰኝ ይችላልን?” (አጽንዖ የተጨመረ)

መምህር ያረጋልን ደግመን እንጠይቀው – የክርስትና ዓላማ ቁሳዊ ሀብት ማከማቸትና መበልፀግ እስካልሆነ ድረስ ፥ አንድ ሰው ክርስትናን በቁሳዊ ሐብትና ብልፅግና ለመለካት ያቀረበውን ጥያቄ “አንተ ባልከውም ቢሆን” ብለን ለመመለስ ለምን እንነሣለን – በአጋጣሚ ይህኛውን ሙግት ለማሸነፍ የሚጠቅመን እንኳን ቢሆን ? የተባለው ተጨባጭ ታሪክ ባይኖርስ – ያኔ ደግሞ ይህ መንገድ ስላማያዋጣን በሌላ መንገድ ልንሔድ ነው ? ለምሳሌ የአውሮፓ እና የግብፅ ገዳማት ቀርተው የኢትዮጵያ ገዳማት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ይህ ነው የሚባል “ተጨባጭ አበርክቶ” የላቸውም የሚል ተቺ ቢመጣብን ሂሳችንን ልንውጥ ነው ? ወይስ “አበርክቶዎቹን” ፍለጋ ልንባትል ነው ? ወይስ ‘አይ ገዳማቱ በዚህ አይለኩም እንላለን ?’ ሲፋጅ በማንኪያ . . . ነው ነገሩ ?

አንድም “ያልተነሣውን ነገር ችላ ብሎ” ማለቱ የዘነበ ነቀፋ loaded መሆኑን እንዳልተገነዘበ ያሳያል ። ምክንያቱም ከላይ እንዳልነው ዘነበ ወላ ገዳማት ሥራ መፍቻ ቦታዎች ናቸው ሲል “የሥራን” አስፈላጊነት እየተናገረ ብቻ ሳይሆን የገዳማትን ዋና ዓላማ እና ዐበይት ተግባራትም እየነቀፈ በመሆኑ ነው ። ስለዚህ መምህር ያረጋል የክርስትና (በተለይ ደግሞ የምንኩስና) ዋና ዓላማ “ያልተነሣ” እና እሱን ለማብራራት የሚደረግ ድካም “ዒላማውን የሳተ” ነው በማለቱ የዘነበን ነቀፋ ማዕከላዊ ነጥብ እንደሳተው የሚያሳይ ነው ።

በተጨማሪም መድሎተ ጽድቅ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ምንም ተጽፎ ቢሆን መምህር ያረጋል የዘነበን ስሑት መነሻ የተቀበለ ምላሽ መስጠቱን ትክክል ሊያደርገው ወይም ሊያብራራው አይችልም ። የገዳማዊ ሕይወት ዓላማ ቁሳዊ ብልፅግና አለመሆኑን መግለጹም ከቁሳዊ ብልፅግና አንጻር የገዳማትን “ጠቀሜታ” ከማብራራቱ ጋር የሚጋጭ ነው ። ወይ አንዱ ወይ ሌላው ነው ሊሆን የሚችለው ። እኛ ‘አንዱ ብቻ መሆን አለበት ።’ ባዮች ነን ። ለዚህም ነው የእኛን ትችት የእርሱ መልስ “በበቂ ካልተብራራ” ወይም “እኔ ያልኩት ካልሆነ ወይም በእገሌ መንገድ ካልሆነ” የሚል ብሎ መግለጹ ትክክል ያልሆነው ። እኛ ያልነው ‘መባል የሌለበት ነገር ተብሏል ፣ ይህ ደግሞ አደገኛ ነው ።’ ነው ። አደገኛ ስንልም በአደገኝነቱ ስለምናምን ነው እንጂ ቃሉን በግድየለሽነት እየተጠቀምነው አይደለም ። የዘነበ ስሑት መነሻ ዘነበ ጋር ቢቀር ይሻላል ።  እርሱም ትቶት ወደ ቤተ ክርስቲያን ቢመጣ ደስ ባለን ። ነገር ግን ይህ ስሑት መነሻ ልብ ሳይባል በመምህር ያረጋል መልስ ውስጥ ተቀባይነት ሲያገኝ – በአፍአ የነበረው አደጋ ወደ ውስጥ ገባ ማለትም አይደል ?

ከዚህም ሌላ ፥ መምህር ያረጋል መልሴ reductionist አይደለም ስላለ ብቻ መልሱ reductionist ከመሆን አይመለስም ። እንዴት reductionist እንዳልሆነ ማሳየት ነበረበት ። ነገር ግን ከላይ እንዳሳየነው የተጠቀማቸው ምሳሌዎችም ሆነ የሰጣቸው ማብራሪያዎች ይህ የሚያሳዩ አይደሉም ። የእኛንም ጽሑፍ እየጠቀሰ ሊሞግተው እና ለምን የእኛ መረዳት ወይም ትችት የተሳሳተ እንደሆነ ሊያብራራ አልወደደም ።

ከመምህር ያረጋል ጽሑፍ ውስጥ በእጅጉ ያዘንንበት እና ምናልባት “ጽሑፋችንን ጨርሶ አላነበበውም ይሆን ?” ብለን እንድንጠይቅ ያደረገን ክፍል – እኛ “ቤተ ክርስቲያን ይህ ዓለም የመሥሪያ ቦታዋ” አይደለም ወይም “ክርስትና ዓለሙን ለመዋጀት የሚችል አስተሳሰብ እና አሠራር የለውም እንዳልን ወይም ወደ እነዚህ ድምዳሜዎች ሊመራ የሚችል ነገር እንደጻፍን አድርጎ ወቀሳ ያቀረበበት ክፍል ነው ። ይህን ወቀሳ ያነበበ ፥ የእኛን ጽሑፍ ግን ያልተመለከተ ሰው “ቤተ ክርስቲያን የሰዎች ረሀብና ችግር አይመለከታትም” ብለን የተከራከርን ይመስለዋል ። ይህን ወቀሳ የሚያሳዝን ሆኖ ያገኘነው በጽሑፋችን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለንን ሐሳብ በግልጥ ያስቀመጥን በመሆኑ ነው ።

“እዚህ ጋ አጽንዖት መስጠት ያለብኝ ነገር ቤተ ክርስቲያን ስለ ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ ጉዳዮች አይመለከታትም እያልሁ አለመሆኑን ነው። ማሳነስ (reductionism) ብለን እያነወርን ያለነው ባህልን ፣ ኢኮኖሚን ፣ ፖለቲካን በራሳቸው ግቦች አድርገን ቤተ ክርስቲያንን ለእነዚህ ግቦች የማስገዛትንና ለእነርሱ በምታደርገው “አስተዋጽዖ” መሠረት ለመዳኘት የመሞከርን ስሑት አካሄድ ነው ። እኛ ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች የምንመለከታቸው በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መነጽርነት መሆኑ እና ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ተገዢ መደረግ የሚገባቸው እንደሆኑ ማመናችን መረሳት የለበትም ።”

ይህን ማድረግ ያስፈልገን ነበር ብለን ባናምንም ግን ምናልባት በዚህ መንገድ የሚተረጉመው ሰው ካለ አርቆ ማጠሩ ይበጃል በሚል ነበር ያደረግነው ። ቅሉ አልበጀንም ።

አይጋጭም እንጂ መምህር ያረጋል እሱ ላይ ያቀረብነው ትችት ከዚህ አባባላችን ጋር ይጋጫል ብሎ ካሰበ – መጋጨቱን ጠቅሶ አስረድቶ ሊሞግተን ይችል ነበር ። እርሱ ግን በግላጭ ከገለጥነው አቋማችን በተቃራኒው እንደቆምን አድርጎ ወቀሰን ። ለዚህም ነው ጽሑፉን ጨርሶ ባያነበው ይሆናል ብለን ያሰብነው ። እያወቀ አድርጎታል ብለን ማመን አልፈለግንም ።

ነገር ግን እኛ ላይ ካደረሰው ወቀሳ የበለጠ አሳሳቢ ሆኖ የሚታየን መምህር ያረጋል ለዘነበ ወላ በሰጠው መልስ ላይ የገዳማትን ኢክኖሚያዊ ፣ ታሪካዊ ወዘተርፈ “ጠቀሜታዎች” መዘርዘሩን ዓለምን ከመዋጀት ጋር ያገናኘው መሆኑ ነው ። ከላይ እንዳስረዳነው ፣ የመምህር ያረጋል መልስ ‘ሥራ ማለት ቁሳዊ ብልፅግናን የሚያመጣ ተግባር ነው ።’ ሲል ዓለሙ (ዘነበ) በሰፋላት ቀሚስ ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን አስገብቶ ‘የራሷ ቀሚስ አላት ግን ይህም ቀሚስ እኮ አይሰፋትም ።’ የሚል ነው ። የእኛም ትችት ከዚህ የመነጨ ነው ። እኛማ ቤተ ክርስቲያን ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለዓለሙም ቀሚስ መስፋት አለባት ባዮች ነን ። እሷ ለዓለሙ ወዳዘጋጀችው ዓለሙን ትጠራዋለች እንጂ ለቅጽበትም ቢሆን ዓለሙ ወዳዘጋጀላት አትሔድም ። ለዚህም ነው የሥራን ብያኔ “ቢሆን ራሱ” በሚልም እንኳን ከዘነበ ወላ ልንዋስ ይገባል ብለን የማናምነው ።

መምህር ያረጋል የጠቀሳቸው ነገሮች እውነት መሆናቸውን አልካድንም ፤ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ቤተ ክርስቲያን ከምትሰጣቸው ዋጋ አንጻር እንጂ ዓለሙ ዋጋ ስለሰጣቸው ዋጋ ልንሰጣቸው አይገባም ነው ያልነው ። ለእነዚህ ነገሮች ዓለሙ ከእኛ በተለየ ምክንያት ዋጋ ስለሰጣቸው ሚዛናችን ተመሳሳይ ሊመስለን አይገባም ። ዓለሙ ሚዛናችሁን ባልቀበልም የእነዚህን ነገሮች ልኬት ግን እጋራችኋለሁ ሲለን ፣ የእኛን ሚዛን የተቀበለ ፣ ወይም መሠረት ያለው ስምምነት የኖረን ሊመስለን አይገባም ። ይልቁንም የራሳችንን ሚዛን አጥብቀን መያዝ ይገባናል እንጂ ።

በዚህ መሠረት ስንመዝናቸው ደግሞ መምህር ያረጋል ከጠቀሳቸው ነገሮች አንዳንዶቹ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ዐበይት አካላት ፣ ሌሎቹ ደግሞ ቢኖሩም ባይኖሩም ከተልእኮዋ የማያጎድሉ ሆነው እናገኛቸዋለን ። ለምሳሌ መምህር ያረጋል ቅዱስ ባስልዮስ በዘመኑ ሐኪም ቤት እና የድሆች መርጃ ቤቶችን እንደመሠረተ ገልጧል ። ይህ ተግባር በመሠረቱ ክርስቲያናዊ ስለሆነ መደረግ ያለበት እንጂ በዘነበ ወላ ብያኔ መሠረት “ሥራ” በመሆኑ የምናደርገው አይደለም ። ስለዚህ ዘነበ ወላ ምንም ቢል ወይም ምንም ባይል ቤተ ክርስቲያን የተልእኮዋ አካል ስለሆነ ልታደርገው ይገባታል ። ማለትም እሷ ራሷን የምትመዝንበት ነገር ነው ። ሌሎች መምህር ያረጋል የጠቀሳቸው ነገሮች ግን – ለምሳሌ ዩኒቨሲቲዎች መቋቋማቸው ፣ የወፍጮ ሥራ ፣ ማዕድናትን ማውጣት ወዘተርፈ ግን ጥሩ ነገሮች ቢሆኑም – ትርፍ ናቸው ፤ ቢሆኑም ባይሆኑም ከተልእኮዋ የሚያጎድሉ ነገሮች አይደሉም ። ይህን ላለመሣትና ዓለሙ ሁለቱን ነገሮች ተመሳሳይ አድርጎ ሲመለከታቸው እኛም ወደዚያ ስህተት አብረን እንዳንገባ ሁሉንም ነገሮች ፣ ሁሌም ቢሆን እኛ ልንመዝናቸውና ዋጋ ልንሰጣቸው የሚገባው ከቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አንጻር ብቻ ነው ።

ለምሳሌ አባ ሶፍሮኒ ወደ እንግሊዝ ሀገር ለመግባት ቪዛ ሲከለከሉ ፥ መምህር ያረጋል እንዳደረገው ‘ዋና ዓላማችን እና ሥራችን ይህ ባይሆንም ፣ በዚህም በኩል ግን አበርክቶ የሌለን አይደለንም ።’ ቢሉ ብለን እናስብ ። ለደቂቃም ቢሆን ወደ ከልካዮቻቸው ሚዛን ሔዱ ማለት ነው ፣ በዚህም ብመዘን አልጣልም ብለው ስላሰቡ ። ከዚያም መምህር ያረጋል ያላቸውን የኢኮኖሚ ፣ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ “አበርክቶዎች” ሲዘረዝሩ ከልካዮቻቸው ‘በጥንት ዘመን ገዳማት ይህ አበርክቶ የነበራቸው መሆኑ እውነት ነው ። አሁን ግን የእኛ ቴክኖሎጂ እና ኢኮኖሚ የበለፀገ ስለሆነ የገዳማት እርዳታ እና እገዛ አያስፈልገንም ። እንኳን ዐዲስ ገዳም ልትመሠርቱ ያሉትም አበርክቶአቸውን ጨርሰው ተዘግተዋል ።’ ቢሏቸው ምን ይመልሳሉ ?

ከልካዮቻቸው በዚህ ሳያበቁ ፥ ለቴክኖሎጂና ለኢኮኖሚ (ትርፍ ላልናቸው ነገሮች) ብቻ ሳይሆን (የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አካል ስለሆኑትም ነገሮች) ‘ሕክምና እና ድሆች መርጃም ቢሆን በበቂ መጠን አሉን ፤ የተራቀቁ ፥ ሕክምናን ለሁሉም ሰው በነጻ የሚሰጡ ሆስፒታሎች አሉን ። ድሆችም በመንግሥት በቀጥታ ይደጎማሉ – ስለዚህ በዚህ ረገድም ቢሆን ልታግዙት የምትችሉት ነገር የለም ።’ ቢሏቸውስ ?

ነጥቤ ግልጽ ይመስለኛል ። ምንም እንኳን በተለያየ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን በአጋጣሚ ያስገኘቻቸውና ለሰው ቁሳዊ ሕይወት ጠቃሚ ሆነው የተገኙት ነገሮች ወይም ስለ ሁሉም የሕይወታችን ገጽ ስለሚገዳት ተልእኮዬ ነው ብላ ይዛ የምትሠራቸው ነገሮች በዓለሙም ሚዛን ዋጋ ያላቸው ሆነው ቢገኙ – ሁልጊዜም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እና ክርስቲያኖች እነዚያን ነገሮች የሚመዝኗቸው ከቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አንጻር እንጂ ዓለሙ ከሰጣቸው ዋጋ አንጻር መሆን የለበትም ። ለደቂቃም ቢሆን ። እንደ ዘነበ ወላ ከውጭ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን የእነሱን መለኪያዎች እንድታሟላ ለሚጠይቋት ሰዎች የእነሱን መለኪያ ተጠቅመን ብናሳምናቸው እና ቤተ ክርስቲያንን ማድነቅ ቢጀምሩ ወይም ወደ ቤተ ክርስቲያን ቢመጡ እንኳን የሚመጡት ያኑ ሚዛን ይዘው ነው – እኛም ቃል የገባንላቸው ብዚያ ሚዛን ቢለኳት ራሱ እንደማታሳፍራቸው ነው ። እነዚህን መለኪያዎች በተሻለ መልኩ የሚያሟላ ነገር ሲያገኙ ወደዚያ መንጎዳቸው አይቀሬ ነው ። እንኳን ውጭ ያሉት ፣ ውስጥ ሆነውም ቤተ ክርስቲያንን በዚህ መንገድ የሚያይዋት ብዙ ሰዎች አሉ ። እንዲህ ያለው መልስ እነሱንም በዚህ ስሑት መንገዳቸው ያጸናቸዋል ። ትችት ልናቀርብ ይገባል ብለን ካመንባቸው ዐበይት ምክንያቶች አንዱም ይህ ነው ።

መምህር ያረጋል ጠቅሶ መልስ ሊሰጥበት አልወደደም እንጂ ጌታችን “ምድራዊ እንጀራ ስለበላችሁ ነው የፈለጋችሁኝ” ብሎ የወቀሳቸውን ሰዎች ምሳሌ አድርገን ያመጣናቸው ለዚህ ነው ። እውነት ነው ጌታችን ብዙሃንን መግቧል ፣ ፈውሷልም ። እውነት ነው ሥጋዊ ደህንነታችን ቤተ ክርስቲያንን ይገዳታል ፤ ምን ጥያቄ አለው ? ነገር ግን ከመመገባችን እና ከመፈወሳችን ብቻ የተነሣ እንፈልገው ዘንድ አይሻም ። ራሱን ማዳን የማይችል እስኪመስል ደክሞ እና ከሞት ጫፍ ሆኖ ፣ በመስቀል ላይ ሆኖም ሳለ እንድንጸና ይጠብቅብናል ። እኛም መስቀሉን ተሸክመን እንድንከተለው ነው ያዘዘን ። መምህር ያረጋል ይህ ጠፍቶታል ብለን አይደለም ። ነገር ግን ሰዎች መስቀሉን መሸከም ካልፈለጉ እንጀራ መብላታቸውን መጥሪያ አድርገን መጠቀም እንችላለን ? እንዲህም ብሎ ያምናል ብለን አናምንም ፤ ነገር ግን ለዘነበ ወላ የሰጠው መልስ እንዲህ ያለ ጥሪ ይዟል በውስጡ ።

አባትና እናት የሚፈለጉት ለልጅ ከሚያደርጓቸው እንክብካቤዎች የተነሣ አይደለም ። ግን እናትና አባት በመሆናቸው እንክብካቤ የማድረግ ግዴታ አለባቸው ። ልጁ አድጎ እነዚያን እንክብካቤዎች መፈለግ ሲያቆም እናትና አባትነታቸው ይቀራል ? እንክብካቤው በሚደረግበትም ጊዜ የእንክብካቤ ምንነት በልጆች ፍላጎት መበየን አይችልም ። የልጆች ብያኔ ወላጆች የሚያደርጉትን እንክብካቤ መያዙ አይቀርም ። ግን የሚያጎድለውም ፣ የሚጨምረውም ይኖራል ። የመጀመሪያው ሥራ ብያኔውን ማረም ነው ። ለጊዜውም ቢሆን ብያኔ የመስጠትን ሥልጣን አሳልፈን የመስጠት ወጥመድ ውስጥ መግባትን ልንፈቅድ አንችልም ። ነገር ግን እንደምናየው ከሆነ ራሳችንን በተደጋጋሚ እዚህ ወጥመድ ውስጥ እያገኘነው ነው ።

ደጋግመን ለዚህ ወጥመድ እንድንሸነፍ የሚያደርገን ነገር ምን እንደሆነ መጠየቅ አለብን ። በውስጡ እንድንወድቅ ብቻ ሳይሆን ፥ ከገባን በኋላም በወጥመድ የመያዝ ሳይሆን የድል አድራጊነት ስሜት እንዲሰማን የሚያደርገን ምንድነው ? በመምህር ያረጋል የመጀመሪያ ጽሑፍም ሆነ ለእኛ ጽሑፍ ብዙዎች በሰጡት ምላሽ ውስጥ የዕቅበተ እምነትን ዓላማ በተመለከተ ስሑት መረዳት ያለ ይመስለናል ። ይኸውም ዕቅበተ እምነት በዋናነት የነቃፊዎቻችንን እና የተቺዎቻችንን አፍ የማስዘጋት ሥራ እንደሆነ መታሰቡ ነው ። ስለሆነም ፥ ይህን ዓላማ ለማሳካት የቀለለውና የተመቸው ነገር ሁሉ ጥቅም ላይ ይውላል ።

በዚህ ጉዳያችን ባደረግነው የመምህር ያረጋል ጽሑፍ ውስጥም ሁለት የሚጋጩ መልሶች ጎን ለጎን የምናገኘው በዚህ የተነሣ ይመስለኛል ። ደጋግሜ እንዳልሁት ፥ መምህር ያረጋል የክርስትና ሕይወት ግብና ዓላማ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና አለመሆኑን ከተናገረ በኋላ ፥ ክርስትና ለዚህ ግቡ ላላደረገው ነገር ያደረገውን “አስተዋጽዖ” መዘርዘር አይጠበቅበትም ነበር ። ወዲያውም የዘነበ ወላ ጥያቄ ያነጣጠረው ዐበይት በሆኑት የገዳማዊ ሕይወት ግቦችና ግብሮች ላይ ስለሆነ ያረጋል ጥያቄውን (ከስሑት መነሻው ጋር) ተቀብሎ የገዳማትን ኢኮኖሚያዊ “ጠቀሜታ” ሲዘረዝር የዘነበ ወላን የተሳሳተ ብያኔ በመቀበል መጀመሪያ ያቀረበውን መከላከያ (ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና የገዳማዊ ሕይወት ዓላማ እኛ መለኪያ አለመሆኑን) ወደ መጣረስ ይገባል ። የእሱን መልስ የሚያነቡ ክርስቲያኖችም የዘነበን ስሑት ብያኔ ባለማወቅ ወደ አእምሮአቸው እንዲያስገቡና ቤተ ክርስቲያንን በዚህ ሚዛን መለካት እንዲጀምሩ ፣ ጀምረውም ከሆነ እንዲገፉበት ይሆናሉ ። የመምህር ያረጋል ዋና ትኩረት ግን ዘነበ ወላን አፉን ማስያዝ ስለሆነ ገዳማዊ ሕይወትን ግቡ ባልሆነ ነገር ለክተንም ቢሆን ይህን ማሳካት ከቻልሁ ለምን አላደርገውም በሚል አመክንዮ የተጓዘ ይመስላል ።

እንደሚታወሰው መምህር ያረጋል ለእኛ ጽሑፍ በሰጠው ምላሽ እኛ ያነሣነውን ትችት በተመለከተ መድሎተ ጽድቅ ቅጽ ፫ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጠ መሆኑን ጠቅሶ ነበር ። ቀድሜ እንዳልሁት መድሎተ ጽድቅ ላይ ምንም ብሎ ቢሆን ለዘነበ ወላ የሰጠው መልስ ላይ የሰጠውን ስህተት ሊያብራራው ፣ ሊያሟላው ወይም ሊያስተባብለው አይችልም ብዬ ስላሰብሁ (እና አሁንም ስለማስብ) ይህን መልስ ለመጻፍ መጽሐፉን የመጥቀስ ግዴታ እንዳለብኝ አልተሰማኝም ። ነገር ግን ካለማየቱ ማየቱ የተሻለ ይሆናል ብዬ ስላሰብሁ መጽሐፉን ከፍቼ የተባለውን ምዕራፍ ተመለከትሁት ። እውነትም በንባቤ የተብራራልኝ ወይም የታረቀልኝ ነገር አልነበረም ። ይልቁንም ለዘነበ ወላ በሰጠው ምላሽ ውስጥ ያለውን ውስጣዊ ቅራኔ መድሎተ ጽድቅ ውስጥም እንዳየው ሆንሁ እንጂ ። ዳግመኛም ዕቅበተ እምነትን የተገኘውን እና የቀለለውን መንገድ ተጠቅሞ ተቺዎችን እና ነቃፊዎችን አፍ የማስዘጋት ሥራ አድርጎ ተመልክቶታል የሚለው ግምቴ እንዲጠናከር ሆነ ።

በመጽሐፉ መምህር ያረጋል “ተሃድሶአውያን” ነን ለሚሉ ፕሮቴስታንታውያን ነው ምላሽ የሚሰጠው ። የተባለው ምዕራፍ (ምዕራፍ 7) ደግሞ ፕሮቴስታንታዊነት በአውሮፓ ፣ በአሜሪካ ፣ በደቡብ ኮሪያ ወዘተርፈ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ይመጣ ዘንድ ቁልፍ ሚና መጫወቱን ፣ በተቃራኒው ኦርቶኮክሳዊነት ግን ኢትዮጵያን ከድህነቷ እንድትላቀቅ እንዳላደረጋት በመግለጥ ለቀረበ ነቀፋ መልስ የተሰጠበት ነው ። መምህር ያረጋል ያቀረበው መልስ የመጀመሪያው ክፍል ተገቢና ግሩም ሆኖ ነው ያገኘሁት ። በአጭሩ “የክርስትና ግብ ቁሳዊ ብልፅግና አይደለምና በዚህ መሠረት ለመመዘን መፍቀዳችሁ በራሱ ለክርስትና ታማኝነት እንደሌላችሁ ያሳያል ።” የሚል ነው ። እውነትም እኛ የመምህር ያረጋልን ጽሑፍ ስንተች ያነሣናቸው ነጥቦች እዚህ ጋ በራሱ በመምህር ያረጋል ሰፋ ተደርገው ተብራርተዋል ። ለናሙና ያህል ሁለት ምንባቦች ልጥቀስ ።

“ዋና ዓላማዬ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘውን መንገድ መስበክ ነው ብሎ የሚያምን የአንድ ግለሰብም ይሁን ቡድን የመጀመሪያ ተግባሩ ሊሆን የሚገባው ፣ ያ ስብከቱ ምን ያህል ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር አቅርቧል ወይም አላቀረበም የሚል ሊሆን ይገባል እንጂ ምን ያህል ቁሳዊ ብልጽግናና የኢኮኖሚ ለውጥ አምጥቷል? የሚል እንዴት ሊሆን ይችላል ? ይህማ የፖለቲካ ፕሮግራሞችና የመንግሥታት ደንበኛ ተግባር ነው ። ተሐድሶ ፕሮቴስታንት ያደረገው ነገር ቢኖር ክርስትናን ለቁሳዊ ፍጆታና እርካታ አገልጋይ ማድረግ ወደ ምድራዊ አስተሳሰብ ማውረድ ነው ።” (ገጽ 107-8)

“ዞሀ ቺአ የተባለው (ፕሮቴስታንታዊነት ለኢኮኖሚ ዕደት የተጫወተውን ሚና በተመለከተ ጥናቶችን ያካሔደ ተመራማሪ እና በመጨረሻም ፕሮቴስታንታዊ የሆነ) ሰው ‘ክርስቶስ ኢየሱስን ተቀብሎ የተጠመቀው’ ፣ ክርስትና ለኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚጠቅም ስለተረዳ ከሆነ አንድ ሰው ክርስቶስ ኢየሱስን የሚቀበለውና የሚጠመቀው በዚህ መንገድ መሆን አለበት ? ክርስትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ጠቃሚ መሆኑን ባይረዳ ኖሮ ክርስቲያን ላይሆን ነበር ማለት ነው ? የዚህ አንድምታው ምንድነው ? ክርስቶስ ኢየሱስ ያስተማረን ክርስትና እንዲህ ያለ ነው ? ክርስቲያን የምንሆንበት ምክንያትስ ይህ ነው ?” (ገጽ 110)

እነዚህ የያረጋል መከራከሪያዎች እኛ የእሱን ጽሑፍ ስንተች ካነሣናቸው ነጥቦች ጋር በእጅጉ ይመሳሰላሉ ። ግራ የሚያጋባው እንዴት እነዚህ ነጥቦች እሱ የዘነበ ወላን ነቀፋ ለመመከት ካቀረባቸው መከራከሪያዎች ጋር እንደሚጋጩ አለማየቱ ነው ። ለምሳሌ ዘነበ ወላ (ልክ ዞሃ ቺአ እንደተባለው ሰውዬ) የአስቄጥስ ገዳም አዲስ የስኳር ድንች ዝርያ ማስገኘቱን ሲረዳ ፣ ‘እንዲያ ከሆነማ (ቄደርም ቢሆን) መጠመቅ እፈልጋለሁ’ ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ቢመጣ መምህር ያረጋል ጽሑፉ ግቡን እንደመታ ይቆጥረው ይሆን ? “ተሐድሶአውያን” የኢኮኖሚ እድገትን እንደ አንድ መለኪያ አድርገው መቁጠራቸው “ክርስትናን ለቁሳዊ ፍጆታና እርካታ አገልጋይ ወደ ማድረግ እና ወደ ምድራዊ አስተሳሰብ ማውረድ” ከሆነ እኛ (በየትኛውም አጋጣሚ ቢሆን) ለምን ተመሳሳይ መንገድ ለመከተል እንፈቅዳለን ?

አስገራሚው ነገር መምህር ያረጋል የክርስትና ግብ ቁሳዊ ብልፅግና ማምጣት እንዳልሆነ የሚያስረዳ ሰፊ ሐተታ ካቀረበ በኋላ ፣ ማለትም ምድራዊ ብልፅግና የኦርቶዶክሳዊነትም ሆነ የፕሮቴስታንታዊነት ወይም ሌላ ራሱን “ክርስትና” ብሎ የሚጠራ አስተምህሮ መለኪያ ተደርጎ ሊቆጠር እንደማይገባ ካሳየ በኋላ ፣ ቀጥሎ በሚመጡት ገጾች ‘ፕሮቴስታንታዊነት በተባሉት ቦታዎች የኢኮኖሚ ዕድገትን አላመጣም ፤ ወይም ቢያንስ ማምጣቱ የተረጋገጠ አይደለም ።” የሚል ክርክር ያነሣና ብዙ ገጾችን እዚያ ላይ ያጠፋል ። አንድ ጊዜ የኢኮኖሚ ዕድገት መለኪያ አይሆንም ካልን በኋላ ፕሮቴስታንታዊነት የኢኮኖሚ ዕድገት ቢያመጣ ወይም ባያመጣ ለምን ግድ ይኖረናል ? ክርክሩ ሲሻል ጉንጭ አልፋ ነው ፤ ሲብስ የኢኮኖሚ ዕድገትን መለኪያ ማድረግ ያልፈለግነው ከልባችን ሳይሆን ክርክሩን ለማሸነፍ ያህል ያስመስልብናል ። ለዚህም ነው መምህር ያረጋል ዕቅበተ እምነትን ተቺዎችን እና ነቃፊዎችን አፍ ማስያዣ ፣ ለኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ‘አይችሉንም’ የሚል የአልሸነፍ ባይነት ስሜት መመገቢያ እንጂ የእኛን እውነታ ወደ ሌሎች የማጋባት ተልዕኮአዊ ተግባር አድርጎ እየተረዳው አይደለም ብዬ ለማሰብ የተገደድሁት ። ለምሳሌ ፕሮቴስታንታዊነት በአውሮፓ የኢኮኖሚ ዕድገት አለማምጣቱን ለማረጋገጥ ሲፈልግ መምህር ያረጋል የካቶሊክ ገዳማት እንዴት የኢንዱስትሪ አብዮት ጀማሪ እንደነበሩ ያስረዳናል ።

“(ፕሮቴስታንታዊው የእንግሊዝ ንጉሥ ሄንሪ 8ኛ) ከስግብግብነቱና ለገዳማት ከነበረው ጥላቻ የተነሣ ገዳማቱን ባይመዘብራቸው ኖሮ ገዳማቱ የኢንዱስትሪ አብዮትን ኋላ ከሆነበት ዘመን አስቀድሞ ሊያመጡት ይችሉ እንደነበር የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው ። ከፕሮቴስታንት መነሣት በፊት በገዳማት ፣ በአምራች ግለሰቦችና ቡድኖች ዘንድ የነበሩ ብዙ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችና የቴክኖሎጂ ግኝቶች ነበሩ ። ገዳማት ጠል የሆነው ፕሮቴስታንቲዝም ሲነሳ ግን ብዙ ገዳማት በመዘጋታቸውና ምስቅልቅሎች በመፈጠራቸው በተጀመረው ዕድገት ላይ አሉታዊ ሚና አሳድሯል ።” (ገጽ 142)

ይህን ከኦርቶዶክሳዊነት ጋር ምን ያገናኘዋል ? የሚያገናኘው ነገር ኖሮ አይመስለኝም ። ይልቁንም መምህር ያረጋል ፊቱ ያለው ባለጋራ ፕሮቴስታንታዊ በመሆኑ የእሱን አፍ ማስዘጋትን ግቡ ያደረገ ይመስላል ። ይህን ለማሳካት እስከረዳው ድረስ ደግሞ ፣ የካቶሊካውያን ገዳማትን አምራችነት ወይም የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲን እና የሊቀ መንበር ማኦን ሀገር ወዳድነት ማውሳቱ ችግር ያለበት መስሎ አይታየውም ።

“ሆኖም ግን ይህን የቻይና የኢኮኖሚ ተአምር ጠንክሮ ከመሥራት ፣ ለሀገራቸው አስበው ከልባቸው የሚሠሩ መሪዎች መኖር ፣ እና ይህን ከመሰሉ ተግባራት እንጂ ከሃይማኖታቸው የተገኘ ነው ለማለት አይቻልም ። ቻይናውያን ከዚህ ሁሉ ስኬት የደረሱት በአገር ደረጃ የሚመራው ፓርቲ ኮሚኒስት በሆነበት ፣ ሕዝቡ ደግሞ በኮንፊሺየስ ፍልስፍና እምነት እና ታኦይዝምና ይህን በመሰሉ ሌሎች ባህላዊ እምነቶች ባሉበት ሁኔታ ነበር ።” (ገጽ 158)

ታዲያ ነገ ደግሞ ኮሚዩኒስቶችና ካቶሊካውያን የእኛ እምነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና ስለሚመራ ትክክል ነው ብለው ወደ እኛ ቢመጡ መምህር ያረጋል ምን ይላቸው ይሆን ? ምን እናተርፍ ብለን ይሆን እንዲህ ያለ ወጥመድ ውስጥ ራሳችንን መክተታችን ? ሊገኝ የሚችለው ትርፍ አንድ ብቻ ነው (ትርፍ ከተባለ) – በፊታችን ያለውን ተቃዋሚ አፍ ማስዘጋት ።[1] መምህር ያረጋል ለዘነበ ወላ የሰጠውን ምላሽ የደመደመው እንደሚከተለው ነበር ።

“ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!”

ይህ አባባሉም ሆነ የጽሑፉ ጠቅላላ መንፈስ በጠቅላላው ተዋሥኦ ለማድረግ የመፈለግ ሳይሆን “አትድረሱብን ፣ አንደርስባችሁም ።” የሚል ቃና ያለው ነው ። ቀሲስ አባተ ይህን የእኔን ጽሑፍ በቀደመው መልሳቸው እንዳነሡት ለምን እንዲህ ዓይነት ስሜት ውስጥ ሊገባ እንደሚችል እንረዳለን ፤ በሀገሩ የማንኖር ሰዎች አይደለንም ። ነገር ግን ይህ ስሜት አሸንፎን ዕቅበተ እምነታችንን እንዲቃኘው ልንፈቅድለት አንችልም ። ምክንያቱም እንዳየነው ከራሳችን መነሻዎች እና መርሖች ጋር የመጣረስ ቅርቃር ውስጥ ስለሚያስገባን ነው ። አንድም እንዲህ ባለ አቀራረብ የምናሰፍነው ዝምታ እንጂ የምንረታው ክርክር ፣ የምንፈጥረውም ስምምነት የለም ። ከዝምታ ካለፈ አፍአዊ የሆነ መደናነቅን ብናተርፍ ነው ። ወይም እንደ ዞሃ ቺአ ያሉ “ምእመናንን” ብናፈራ ነው ።

የዚህን ችግር ባለቤትነት ለመምህር ያረጋል እየሰጠነው እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል ። ነገር ግን ችግሩን እሱም ላይ አስተውለነዋል ፣ ያሳስበንማል ። እንደ እውነቱ ከሆነ ይህን ጉዳይ  የመምህር ያረጋልን ጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ስናነበው ልብ ብለነው እና አሳስቦን ነበር ። ከጽሑፉ reductionist አካሔድ ጎን ለጎን ልንተቸውም ፈልገን ነበረ ። ነገር ግን ጽሑፉ ከሐሳብ ይልቅ መምህር ያረጋል ላይ ያተኮረ እንዳይመስል ፥ ‘በዚህ ጽሑፍ አንዱ ጉዳይ ላይ ማተኮር ይሻላል ፤ ይህኛውን ጉዳይ ደግሞ በሌላ አጋጣሚ በሌላ ጽሑፍ እናነሳዋለን ።’ የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰን ነበር ። አሁንም ይህን ጉዳይ በምልዓት ለመተቸትና ለመተነተን ባንነሣም ግን የጽሑፉ reductionist የመሆን ዝንባሌ ግን ከዚሁ ጉዳይ የመነጨ መሆኑን በማስተዋላችን ነው ነገሩን ልናነሣው የተገደድነው ። እንዲህ በእግረ መንገድ ባናነሣው መልካም ነበር ። ሆኖም ግን የችግሩ ምንነት ፣ የሚያመጣው ችግር እና በቅድሚያ ከተነሣንበት ጉዳይ ጋር ያለው ትስስር ግልጽ ነው ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። ወደፊት ደግሞ ይህን ጉዳይ ራሱን የቻለ ርእስ አድርገን ሰፋ ባሉ ጽሑፎችና ውይይቶች የምንመለስበት ይሆናል ።

ጽሑፌን ከማብቃቴ በፊት አንድ ነገር ልበል ። እኛ መምህር ያረጋልን መተቸታችን በአሱም ሆነ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል ። ብዙ ሰው በእኛ ትችት ያልተስማማው በዋናነት እርስ በእርሳችን ልንለያይ አይገባም ከሚል መነሻ ነው ። በሐሳብ ከመለያየታችን በላይ ልዩነቱ አደባባይ መውጣቱ ደስ አላሰኘም ። አንድም እርስ በእርሳችን ከምንተቻች ትኩረታችንን ከውጪ የሚተቹን ሰዎች ላይ ማድረግ ያለብን መሆኑን ብዙዎች አሳስበውናል ። ነገር ግን ሊያሳስበን የሚገባው ልዩነት ያለን መሆኑ መታወቁ ነው ወይስ ልዩነት ያለን መሆኑ በራሱ ? ልዩነታችንን ሸፋፍነነው ሁላችንም በየራሳችን መንገድ ብንሔድ አንድነታችን ይጸናል ? የሚያሻማ አይመስለኝም ።

[1] መምህር ያረጋል እነዚህን ነጥቦች ያነሣው በዕቅበተ ዕምነት ዓውድ ሳይሆን የኢኮኖሚ ዕድገት ከየት ይመጣል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ብቻ ካለ ጉጉት ቢሆን አንድ ነገር ነበር ። “ተሐድሶአውያኑ” ቀጣፊዎች መሆናቸውን (ሁሌም እንዲያ ናቸውና) ለማሳየት ቢሆን ደግሞ ወደዚህ ሁሉ ዝርዝር መግባት ባላሻውም ነበር ። እያውቁ የሚቀጥፏቸውን ጥቂት ሐቆች መጠቆም ይበቃው ነበር ። በዚህ ጉዳይ እንኳን በቅድሚያ ያቀረበው ክርክር – “ተሐድሶአውያኑ” መጽሐፍ ቅዱሳውያን ነን እያሉ ክርስትናን በኢኮኖሚ ዕድገት ለመለካት መነሣታቸው በራሱ ክርስትናን አለመረዳታቸውንም ሆነ ተአማኒ አለመሆናቸውን ለማስረዳት በቂ ነበር ።

Share...

Facebook
Telegram
WhatsApp
X
Email
Print
14 Comments
  • Temesgen Tessema
    Temesgen Tessema
    October 6, 2024 at 7:26 am

    ቃል ሕይወትን ያሰማልን።
    Insightful !

    Reply
    • Behailu Bekele
      Behailu Bekele
      October 6, 2024 at 10:46 am

      ምስክርነት!

      ዛሬ ሦስት አጋንንት ኡኡኡኡ ብለው ወጡልኝ አንደኛው Reductionistነቴ ፤ ሁለተኛው ጭፍን ተላዌ መምህርነቴ ፤ ሦስተኛዋ ደግሞ ስሁት ዕቅበተ እምነት አረዳዴ ናቸው።

      ደግሞ ሌላም አሳድጌ አሳድጌማ አለቅም ሚሉኝ ርዕዮተ አለማት ስላሉ እባካችሁ አጥምቁኝ በጽሁፍክሙ!

      ቃል ገባለው አንድ ንጉስ ዳዊት ደግምላቹዋለው!

      Reply
  • ዮናስ
    ዮናስ
    October 6, 2024 at 10:32 am

    ቃል ሕይወትን ያሰማልን!
    ጥልቅ ምልከታ በውስጡ ብዙ ቁምነገሮች ያሉት::

    Reply
    • Des
      Des
      October 6, 2024 at 5:29 pm

      መነጋገርን መወያየትን የመሰለ መልካም ነገር የለም። ውድ ወንድሜ የገዳማት ኑሮ ላይ ጥናት አድርገዋል ወይንም አንበዋል? ገዳማት ውስጥ እንዴት ይኖራል? ማህበረ ስላሴ በረሃ ውስጥ ፣ ዳጋ፣ ዋልድባ …ያሉት አበው በስራ እጅግ የሚተጉት ለምን ይሆን? ከዘነባ ወላ ይልቅ የእኛ የሆኑትን ትላልቅ የምናኔ ገዳማት የኑሮ ዘይቤን ምን ያህል በዝርዝር በተጠና መልክ እናውቀዋለን?

      Reply
  • Habtamu
    Habtamu
    October 7, 2024 at 12:17 pm

    ምርጥዬና በሳል ጽሑፍ!
    እግዚአብሔር ብዕራችሁን ያለምልምላችሁ::

    ከስሜታዊነት የወጣ ኦሮቶዶክሳዊ ዕቅበተ እምነት መልካም ነው::የምንወዳቸው መምህራችን(ያረጋል አበጋዝ) ትንሽ ስሜታዊ ባይኾኑ ጥሩ ነበር:: ግን እንደሚመስለኝ መምህራችን ሃይማኖታችን ላይ የሚሰነዘሩ የምንፍቅና:የድንቁርና እና ከፍ ያሉ የጽርፈት(የስድብ) ጽሑፎችን ስላነበቡ ብስጭት ውስጥ ሳይከታቸው አይቀርም:ለዛም ይመስለኛል ጊዜ ሳይወስዱ ና በጥልቀት ሳያስቡ መልስ የጻፉበት::
    ኤማሁሶችም እስካሁን የጻፋችሁት በተዘዋዋሪ መንገድ ለዘነበ ወላና መሰሎቹ መልስ መኾን ቢችልም:ወጥ የኾነ የዘነበ ወላ ትችት ላይ ያተኮረ ጽሑፍ ብትጽፉልን ጥሩ Ground እንይዛለን የሚል ትሑት ሀሳብ አለዉ::

    Reply
    • Binuyam Welde
      Binuyam Welde
      October 8, 2024 at 7:16 pm

      ቃለ ህይወት ያሰማልን

      Reply
      • አንተነህ ዳኜ
        አንተነህ ዳኜ
        October 9, 2024 at 8:08 pm

        በፅንሰ ሃሳቡ ዙሪያ ከሁለቱም ወገን የተሰነዘሩትን ነጥቦች ወስጃለሁ፤ ብዙም ተምሬበታለሁና ሳላመሰግን አላልፍም።

        ነገር ግን ጉዳዩ thematic centered መሆኑን እየተወ personal ወደመሆን ማደጉን ተከትሎ ከውይይቱ ልንማር በሚገባን ፍሬ ሀሳብ distraction መፍጠሩን ስላስተዋልኩ ይህን ለመፃፍ ተነሳሳሁ።

        የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ቤት አይሰራም።
        መተቻቸት ተገቢ ሆኖ ሳለ፤ እንደየቦታው አግባብነቱ ሊታሰብበት ይገባል። አንዳንዴ ይህን መሰሉ ስህተት ከምዕመኑ ይልቅ በመምህራን እንዳይብስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
        በቤተክርስቲያናችን ታሪክ ብናይ ጳውሎስም ለጴጥሮስ ወቀሳ አዘል ምላሽን ሲሰጥ ተመልክተናል፤ ግን በትህትናና በቅንነት ነበር።
        ጴጥሮስ የማልኮስን ጆሮ እንደቆረጠ፤ በቅንነት ለክርስቶስ ተቆርቁሮ ያደረገው ቢሆንም ግሳፄው መልሶ ለተግሳፅ አድርሶታል። እኛስ ሰይፍ መያዛችንን፥ እውቀታችንን ያለአግባብ በመጠቀም ጆሮ መቁረጣችን እግዚአብሔርን ለማስደሰት ይሆነናል?
        እንደው ለማለት ያህል የገቡ ከሚመስሉት የእርስ በእርስ ውይይቱ መሀል ከተጠቀሱ አንዳንድ ሀረጎች በዘለለ genuine appreciation እንዲሁም ትህትና በሁለታችሁም ወገን አላስተዋልኩም። ፅሁፎቻችሁ ትህትናን የሚያስተምሩን አልሆኑም።
        በኤማሁሶች በኩል በቤተክርስቲያናችን መምህራን ውስጥ በዘመናችን የሚስተዋለውን አልሰበር ባይነት አጋጣሚውን አገኘን ብላችሁ በሚመስል ሁኔታ ለክስተቱ በማይመይመጥን የተጋነነ አካሄድ መቃወማችሁ፤ መምህራችን በኩልም ትህትናና እርጋታን ማስተማር ያልቻለ ምላሽ መሰጠቱ አንባቢ ምዕመናንን እያወዛወዘ ያለ መሆኑን ልብ ይሏል።
        ታላቅ ናቸው መምህራን ናቸው ብሎ ዝም ተብሎ ባይታለፍም፥ ሰይፍ አለኝ ተብሎም ጆሮ መቁረጥ አይገባም ብዬ አስባለሁ።
        እውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንፃል ይላልና እባካችሁ እርምጃዎቻችሁን በፍቅር አድርጉት አባታዊ፣ ወንድማዊ ምክሬ ነው።

        በፍቅር ማውራት የምንችልበት መድረክ ከተፈጠረ ሀሳቦችን thematically እያነሳን እየጣልን ብዙ ልናወራ እንችላለን።

        Reply
        • ቀሲስ አባተ አሰፋ
          ቀሲስ አባተ አሰፋ
          October 10, 2024 at 11:51 am

          ለአስተያየቱ ታላቅ አክብሮት አለን። የግለሰቦች ፉክክር ተደርጎ መወሰዱን ግን አልወደድነውም። በጭራሽ አይደለምና!

          Reply
  • Mebratu T.
    Mebratu T.
    October 8, 2024 at 5:15 am

    ረብ የለሹን ሙግት በጥሞና ተመለከትሁት፡፡ ኤማሁሶች ሌላ ሌላውን የአጻጻፍና የእሳቤ (ጽንሰ ሀሳብ) ግድፈትን ትቼ ሁኔታችሁን (መንገዳችሁን ሳያየው) ‹‹ፍየል ከመድረሷ፣ ቅጠል መበጠሷ›› ሆነብኝ፡፡

    ‹‹አሳንሶት››ን፣ የምታሳንሱ አሳናሾች እንዳትሆኑም ሰጋሁ፡፡ እቡይነትም እየተፈታተናችሁ መሰለኝ፡፡

    ስለዚህ፣ ሩቅ መጓዝና ማሰብ ከፈለጋችሁ፣ እየተፈታተናችሁ ያለውን እቡይነት ግደፉት፡፡ በተረፈ የዋሕ ቅናነታችሁን ድንቅ ነው፣ ግን ደሞ በጥበብና በብስለት አድርጉት፡፡

    Reply
    • mulegeda
      mulegeda
      October 8, 2024 at 6:39 am

      ወንድም ዓለም ምኑ ነው ረብ የለሽ ያልካው ሙግቶቹን እንብበህ ሳታስተውላቸው ነው እዚህ የደረስከው መለስ ብለህ እያስተዋልክ አንብበው በተረፈ ኤማአውሶች እየሞገቱ ያሉት በማስረጃ ነው ከቸልክ በማስረጃ ሞግታቸው ከስሜታዊነት ቲፎዚ ውጣ 🙏

      Reply
  • Yosef Fiseha
    Yosef Fiseha
    October 8, 2024 at 4:18 pm

    መልካም፡፡ በነገራችን ላይ የመድሎተ ጽድቅ ቅጽ 3 መጽሐፍ በዋናነት ለጸጋ አብ በቀለ ተሐድሶ ቅጽ 1 መጽሐፍ የተሰጠ የመልስ መጽሐፍ ነው፡፡ ፕሮቴስታንት ለብልጽግና የሚሆን እምነት ነው ስላለና ጸሐፊው ያቀረበው ዳታ ሐሰት መሆኑን ምንጭ ጠቅሶ ዓለም አቀፍ ሆኔታውን በይኖ መልስ የሰጠበት ነው፡፡ ስለዚህ ያረጋል አበጋዝ (ዲ/ን) በኢኮኖሚካል ጉዳይ መልስ የሰጠውን ዐውዱን ብናየው ጥሩ ነው፡፡ መልስ የሰጠበትን ማለቴ ነው፡፡ እናም መድሎተ ጽድቅን ስትጠቅሱ የመጽሐፉን አላማና ዐውዱን ያስተዋላችሁት አይመስለኝም፡፡ ለምትፈልጉት አላማ ከመድሎተ ጽድቅ ቅጽ 3 መጽሐፍ ሐሳብ ብቻ የቆነጠራችሁለት መስሎኛል፡፡ ተሐድሶ ቅጽ 1 መጽሐፍን ብንመለከተው የበለጠ የተሰጠበትን የመልስ አላማ የምንረዳው ይመስለኛል፡፡

    Reply
    • Yonatan Begashaw
      Yonatan Begashaw
      October 9, 2024 at 7:00 pm

      በመጀመሪያ እየተነሱ ያሉት ክርክሮች በራሳቸው የጋራ የሚመስል እንጂ በትክክል የጋራ የሆነ መሰረት ያላቸው አይመስልም። ዓለማዊ አመለካከት፣ መንፈሳዊ ፅንሰ ሃሳብ እና ጭፍን እምነት ላይ መሰረት ያደረጉ ክርክሮች ናቸው እየተነሱ ያለት። በዚህ መሰረት ክርክሩ እርባና ቢስ ነው የሚሆነው። በ ዘነበ ወላ በኩል የቀረበው ሃሳብ መንፈሳዊ ህይወትን በ ዓለማዊ መመዘኛ የሚለካ መሆኑ በራሱ ያቀረበውን ሙግት ውድቅ ያደርገዋል። እናንተ የሰነዘራችሁት ትችት ላይ መምህሩ ያቀረቡት ሃሳብ ደግሞ ትችቱን ከመረዳት ይልቅ መልስ መስጠት ላይ ያተኮረ መሆኑ ላመኑበት ሃሳብ በጭፍን መከላከል ላይ መጠመዳቸውን ያሳብቃል። በዚህ መንገድ ደግሞ ክርክሩ የፅሁፍ ሰጣ ገባ እንጂ ፍሬ የሚያፈራ አለመሆኑን ጠቋሚ ነው። የሃሳብ ፍጭቱ ሊፈታ የሚችለው አንድ መሰረታዊ ሃሳብ ላይ ስትቆሙ ብቻ ነው ስለዚህ ክርክሩ ይቆይና የቆማችሁበትን ቦታ አስተውሉት

      Reply
  • Berihun Hailu
    Berihun Hailu
    October 10, 2024 at 9:53 am

    ተባረኩ በጣም ጥሩ እውቀት አገኘሁ

    Reply
    • ema
      ema
      October 16, 2024 at 7:24 pm

      አሁን እሄ ሀሳብ የእኔን ህይወት እንዴት እንደቃኘዉ ብነግራችሁ ችግር አለዉ ያለዉ አይመስለኝም እናላችሁ እምማረዉ ትምህርት ከተመረኩ በኋላ ብዙ ገንዘብ አያስገኝም እሚለዉ ነገር እለት እለት እያሳሰበኝ ለዶርም ልጆች ሁሌ ስለዚህ ነበር እምነግራቸዉ ምናምን አሁን ምን ገባኝ ለካ ክርስትያን ነኝ አላማየ ወደመምሰል ማደግ ነዉ እያንዳንዱን የህይወት ገፅታ ማየት ያለብኝ ከቤተክርስትያን አንፃር ነዉ
      በዚህም ምክንያት በፊት በልምድ እማደርጋቸዉ እና እማላደርጋቸዉ ነገሮችን እያስተካከልኩ ነዉ ለምሳሌ ከነገርኳችሁ ነገር አሁን ለዶርም ልጆች ስለደሞዝ ሳይሆን ስለዘላለማዊ ህይወት ነዉ እማወራ ደግሞ በጴንጤዎች መንገድ ምናምን እንዳይመስላችሁ…. ደግሞ ኤርሚ😊 የቆሰለች ነፍስ እሚል ስነጽሑፍ ግቢ ጉባኤ ላቀርብ ነበር ተዉኩት እና guys በርቱ በጣም የሰዉ ህይወት ይቀይራል

      Reply
Leave a Reply to Yosef Fiseha Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

Guest Posts
መሐሪ ዘመልአክ

የአእላፋት ዝማሬ ምልክት ነው ።

መግቢያ በዘመናችን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታየው “የአእላፋት ዝማሬ” የተባለው ክሥተት ሰፊ የሆነ ሕዝባዊና ሊቱርጊያዊ ውይይት አስነስቷል። አንዳንዶች ይህን እንቅስቃሴ እንደ መንፈሳዊ ንቃትና የራቁ ምእመናን ተሳትፎ መመለሻ ሲያቀርቡት፣ ሌሎች ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሊቱርጊያ[1] ጋር የሚጋጭ እና ሥርዓታዊ መነሻዋን የሚያዳክም ክዋኔ እንደሆነ ይገምግሙታል። ወንድማችን በርናባስ ሽፈራው የጻፈው “የአእላፋት ዝማሬ”ን የተመለከተ የኤማሁስ ገጽ ጽሑፍ አንዳንዶችን ሲያበሳጭ፣ ሌሎችን ሲያሳስብ እንደሰነበተ በአረቦን ቴሌግራም ቻነል ላይ ተመልክቻለኹ። 23 ገጾችን የያዘ፣ ንዑሳን አርእስት በግልጽ ያልተሰጡት ረዥም ጽሑፍ ስለኾነ ጊዜ ሰጥቶ ማንበብን፣ ካነበቡም በኋላ ዐበይት መከራከሪያዎቹን ማጥለልን ይጠይቃል። እንዲኽም ኾኖ፣ ቢያንስ መሠረታዊ የኾነ የሊቱርጊያዊ ነገረ መለኮት (liturgical theology) ንባብ ለሌለው ሰው ጽሑፉ ከንቱ ምቀኝነት፣ መራራነት፣ አማራሪነት፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ ሊመስል ይችላል። በዋናነት እየነቀሰ የሚተቸው “የአእላፋት ዝማሬ”ን ልዩ ልዩ መልኮች ይኹን እንጂ፣ መሠረታዊ ጉዳዩ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአኹኑ ጊዜ ያለችበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ (liturgical crisis) መጠቆም ኾኖ አግኝቼዋለኹ። ጉዳዩ እኔንም ሲያሳስበኝ የነበረ ነገር ስለነበረ የበርናባስን ሐሳብ እንዲኽ ልለጥቀው ወደድኹ። የእኔ ጽሑፍ የ“የአእላፋት ዝማሬ”ን እንደ ምልክት በመመልከት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ የምትገኝበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ ይጠቁማል። በተለይም በቋንቋ ባዕድነት፣ በዜማ ውስብስብነትና በሰዓት ምቹ አለመኾን ምክንያት ምእመናን ከ“ሰዓታት ጸሎት” የራቁበትን ኹኔታና ኮንሰርታዊ ዝግጅቶች በተግባር የተኩት የሊቱርጊያ ባዶ (liturgical vacuum) ምን እንደሆነ ለማመልከትና መፍትሔውን ለማሳየት ይጥራል። The Problem of Reactive Ministry እና Institutional Survivalism በርናባስ በጽሑፉ የሚተቸው አንዱ ነገር ይኽ ተልእኮን

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

“የአእላፋት ዝማሬ”

ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ ባለፈው ዓመት በልደት ዋዜማ ተካሔደ ። በአዘጋጆቹ እና በተሳታፊዎቹ ዘንድ ይህ ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው ዙር በላይ ያማረ እና የሠመረ ሆኖ ተቆጥሯል ። በጠቅላላው ከምእመናን በኩል በተሳትፎም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘው ተቀባይነት ሌሎች ሁነቶች ሲሆኑ እንደምናየው በጅምር የሚቀር ሳይሆን እንደ ባህል የመተከል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን ያመላክታል ። እንዲያውም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ብቻ ሳይወሰን ወደ ሌሎች ቦታዎችም እንዲሰፋ የሕዝብ ጥያቄ እና በአዘጋጆቹም በኩል እቅድ መኖሩ ይታወቃል ። ስለዚህ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ልክ እንደ ጥምቀት ሁሉ በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ (የአዘጋጆቹ አቅም በፈቀደው ልክ) የአእላፋት ዝማሬ የልደት በዓል መለያ ሆኖ እንዲካሔድ መጠበቅ እንችላለን ። ይህ ነገር በብዙዎች ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጥቅም የሚሰጥ ሆኖ ይታያል ። በእነርሱ ዐይን ይህ ሁነት ቤተ ክርስቲያን በብዙዎች ዘንድ እንድትታወቅ ያደርጋል ። ብዙዎች በዓሉን አስመልክተው ከሚሔዱባቸው የማይገቡ ዓውዶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ ከማድረጉ ባሻገር ፥ በቤተ ክርስቲያን ሱታፌ ያላቸውንም በሚስብ እና በሚገባቸው መልኩ ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ እንዲያውቋት ያስችላቸዋል ። ስለዚህም የሌሉትን በመጥራት ፥ ያሉትንም በማጽናት ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን እንድትዋጅ የሚያስችላት መሣሪያ ነው ፤ ከእርሷ ዘንድ ወደ ክሕደት እና ወደ ኑፋቄ የፈለሰውን ፥ ወይም በስም ክርስቲያን ሆኖ እና ማዕተብ አስሮ ሳለ በምድራዊ ተድላ ባሕር የሰጠመውን ወጣት ወደ ራሷ የምትስብበት መረብ ነው ። ነገር ግን ከኖረው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና አስተምህሮ አንጻር ከመረመርነው ፥ ይህ ሁነት

Read More »
Emmaus Posts
ኤልያስ ገብረ ሥላሴ

መከራ ፣ እከይ እና ክርስትና

መከራ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ድንገተኛ የሆነ ክስተት አይደለም ። ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ለጥቅማችን የሚፈቀድ የእርምት መንገድ ነው እንጂ ። በየዘመኑ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ሁነቶች እንድትወጠር እና መሠረታዊ ነገሮች ትኩረት እንዳያገኙ የሚቀርብ ፈተና አለ ። ሰበር ዜናዎች ፣ ወቅታዊ አጀንዳዎች ፣ አከራካሪ ጉዳዮች ወዘተ ከመነኩሴ መቁጠሪያ በላይ በሚሽከረከሩበት ዘመን ላይ ነው የምንገኘው ። እነዚህ ሁነቶች ትኩረታችንን ይወስዱትና ሳይታወቀን መሠረታዊ ከሆኑትና ዘለዓለማዊነታችንን ከሚበይኑት ጉዳዮች ወጥተን ምድራዊና እዚሁ ቀሪ በሆኑ ጉዳዮች ተወጥረን እንገኛለን ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁኔታ በቤተክርስቲያንን መምህራን እና “ተጽዕኖ ፈጣሪዎች” ላይ እጅግ በርትቶ የሚታይ መሆኑ እና በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እና መድረኮች ሳይቀር ሰፊውን ሰዓት መያዙ ነው ። የቤተክርስቲያን ተልእኮ ስለ ክርስቶስ ምስክር መሆን ነው ። መሠረታዊ ካልሆኑት ሁነቶች ወጥተን ወደዚህ ዋነኛ ተልእኮአችን እንድንመለስ ተዋሥኦ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ። ይህ በምእመናን ፥ በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲን አገልጋዮች ፥ ዘንድ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ። የሁነቶችን መሠረት መመርመርና ትክክለኛ ባሕርያቸውን መረዳት ያሻል ። ሁነቶቹ ችግሮች የሆኑ እንደሆነ ሥር ነቀል መፍትሔ ማሰብ የሚቻለው ፥ መልካም አጋጣሚዎችም ከሆኑ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ልናውላቸው የምንችለው የሁነቶቹን መሠረት በጥልቀት መረዳት ከቻልን ነው ። በመቀጠልም ተከትለው ሊደረጉ ስለሚገቡ ነገሮች መወያየት ከተቻለ ብቻ ነው ። ካልሆነ አሁን እየሆነ እንዳለው የወቅታዊ አጀንዳዎች አሳዳጅ ብቻ ሆነን ነው የምንቀረው ። በተለይ ዘመናችን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ስለሆነ በዚህ

Read More »
Emmaus Posts
መሐሪ ዘመልአክ

ከእውነት አልባነት ጋር የሚካሔድ ሙግት

(‘ሐሳቦች መዘዝ አላቸው’ በሚል ርእስ በኤማሁስ መጽሔት ቅጽ 1 ፣ ቁጥር 1 በወጣው ጽሑፍ ላይ የተጻፈ አስተያየት) በመሐሪ ዘመልአክ (PhD) ከዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት የእጓለ ገብረ ዮሐንስ ‘የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ’ ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበብኹ በኋላ ጸሐፊውን ከዚያ በፊት አለማወቄ ገርሞኝ እንደነበር አስታውሳለኹ ። ማን ናቸው ? እንዴት እስከዛሬ ድረስ ስለእርሳቸው ሳልሰማ ቀረኹ ? ለምን ? ይኼ በ1956 ዓ.ም. የታተመ የሬድዮ ንግግር ከኾነ መጽሐፍ ለመጻፍ ብለው ተነሥተው ቢጽፉ ኖሮ ምን ሊጽፉ ነበረ ? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎች ጭንቅላቴ ውስጥ ተመላልሰዋል ።[1] በኋላ ፈላስፋው ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተማሪና መምህር እንደነበሩ ስሰማ በመጽሐፉ ውስጥ ያየሁት የሐሳብ ጥልቀት በዘመኑ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልሒቃን ዘንድ የነበረው ተዋሥኦ ሊደርስ ይንጠራራበት የነበረውን ልክ የጠቆመኝ መሰለኝ ። ከዚያ በኋላ ያ የተዋሥኦ ልሕቀት የት ገባ ? እንዴት ድርቅና የተጫነው ተዋሥኦ ዋጠው ? እንዴት ኦርቶዶክሳዊነትን ከአመክንዮ የተፋታ እና አመክንዮን የሚፈራ ጭፍን እምነት የሚያስመስሉ የፎክሎር ሰባኪዎች ተፈለፈሉብን ?  የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህን ለመኾን የሚጠየቀው መስፈርት ስለምን ድፍረት የለበሰ አላዋቂነት መሰለ ? በሚዲያ ላይ ሲናገሩ በአላዋቂነታቸው አንገታችንን የማያስደፉን ካህናት ስለምን ቁጥራቸው አልበረክት አለን ? ኦርቶዶክሳዊነት ችግርን እና ጭንቀትን ለማረሳሳት የተጠመቀ ዕፀ-ዝንጋዔ (‘opium of the masses’) እስኪመስል ድረስ በኦርቶዶክሳዊነት ስም የገነነው ተዋሥኦ ለምን አላዋቂነት ተጫነው ? ቤተ ክርስቲያን ሲባል ከስሜታዊ ሙጥኝታ (sentimental attachment) ባለፈ ለሰው ልጅ ህልውናዊ ጥያቄ የተሰጠ ከሞት ፍርኃት

Read More »
Emmaus Posts
ኤማሁስ

የኤማሁስ መንገድ

መጽሔቷን ለማግኘት ይህን ይጫኑ . . . የዘመናችን ተዋሥኦ በይዘቱም ሆነ በመንገዶቹ በግልብነት በእጅጉ የተጠቃ ነው ። ‘በይዘቱ እንዴት ?’ቢባል ሁነቶች ላይ ያተኮረ እና ወቅታዊነትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ። አንድም አቋም ከመያዝና ጎራ ከፍሎ ከመናቆር ባለፈ የእውነት የመማር እና የማሰላሰል ጉጉት የማይታይበት በመሆኑ ። በዚህ ተዋሥኦ ውስጥ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሣት እና ከሁነቶቹ የሚሻገር እና ሐሳባዊ የሆነ ትንተና ለማካሔድ መሞከር ትኩረት ያስነሣል ፤ ሲብስም አጉል እንደመራቀቅ ይታያል ። የሚካሄድበት ከባቢ እና ዘመን ደግሞ ሌላ ግልብነት ደርቦለታል ። በእኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሀገራት ፣ ከዘመናዊነትና ከቴክኖሎጂ መራቀቅ ጋር ተያይዞ ሕዝባዊ ተዋሥኦ በጠቅላላው ስለቱን እና ርቀቱን እንዲያጣ ሆኗል ። የሚነበብም ሆነ የሚታይ ወይም የሚደመጥ ነገር አጭር መሆን አለበት ። ነገር ግን ጠቃሚና ወሳኝ ርእሶች እንዲህ ባለ መንገድ ሊስተናገዱ አይችሉም ። የሚያጠግብ ፍሬ ከሌለበት የተመልካቹ እና የአንባቢው ብዛት ምን ጥቅም ይኖረዋል ? እንዲህ ባለው ከባቢ ውስጥ ሁነቶችን ከሁነትነታቸው እና ከሚያመጡት ወቅታዊ ውጤት በተሻገረ መልኩ ለመመልከት እንቸገራለን ። ቀድሞውኑም (እይታችን ከመጥበቡ የተነሣ) ጠባብ አድርገን የቀረጽነውን አጀንዳ በምንገልጽበት መንገድ የበለጠ እናጠብበዋለን ። ነገር ግን ሁነቶችን እና ሒደቶችን ከመሠረታቸው መመርመራችን እና የምናቀርባቸው መፍትሔዎችም እንዲሁ የማይናወጥ መሠረት ያላቸው መሆናቸው አስፈላጊ ከሆነ ተዋሥኦውም እንዲሁ የጠለቀ እና የረቀቀ መሆን አለበት ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ጊዜ ወስዶ ማሰብ ፣ ማንበብ ፣ ማጠናቀር ፣ መወያየት ፣ መሟገት እና እንዲህ ካለው ሒደት

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

ክፍል ፭ ፡ ወደ ርስታችን ያልተመለስንበት ኢዮቤልዩ

ሩሲያዊው ደራሲ ፌዮዶር ዶስቶየቭስኪ በ1860ዎቹ አውሮፓን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኝ የታዘበውን በዘገበበት ማስታወሻው የለንደን ድሆች ቅዳሜ ማታን እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያሳልፉ ይነግረናል ። በቅድሚያ ሌሊቱን በሙሉ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ጭምር ደስታ ፈጽሞ በተለየው ፣ ድብርት በተጫነው መንፈስ አኳዃን ሲበሉ እና ሲጠጡ ፣ ከሕይወታቸው መራራነት ለማምለጥ ፣ ራሳቸውን ፍጹም ለማደንዘዝ በሙሉ ጥምብዝ እስኪሉ እንደሚሰክሩ መስማቱን ይዘግባል ። ሳምንቱን ሙሉ ሠርተው የቋጠሯትን ገንዘብ ቅዳሜ ሌሊት እንዲህ ይበትኗታል ። አስከትሎም እንዲህ ባለው አንድ ምሽት እሱ ራሱ በመንደራቸው ውስጥ ሲያልፍ የታዘበውን እና የተሰማውን እንደሚከተለው ይመሰክራል ። “One such night – it was getting on for two o’clock in the morning – I lost my way and for a long time trudged the streets in the midst of a vast crowd of gloomy people, asking my way almost by gestures, because I do not know a word of English. I found my way, but the impression of what I had seen tormented me for three days afterwards. The populace is much the same anywhere, but there all was so vast, so vivid that you almost physically felt things which up till then you had only imagined. In London, you no longer see the populace. Instead, you see a loss of sensibility, systematic, resigned and

Read More »