ከእውነት አልባነት ጋር የሚካሔድ ሙግት

(‘ሐሳቦች መዘዝ አላቸው’ በሚል ርእስ በኤማሁስ መጽሔት ቅጽ 1 ፣ ቁጥር 1 በወጣው ጽሑፍ ላይ የተጻፈ አስተያየት)

በመሐሪ ዘመልአክ (PhD)

ከዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት የእጓለ ገብረ ዮሐንስ ‘የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ’ ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበብኹ በኋላ ጸሐፊውን ከዚያ በፊት አለማወቄ ገርሞኝ እንደነበር አስታውሳለኹ ። ማን ናቸው ? እንዴት እስከዛሬ ድረስ ስለእርሳቸው ሳልሰማ ቀረኹ ? ለምን ? ይኼ በ1956 ዓ.ም. የታተመ የሬድዮ ንግግር ከኾነ መጽሐፍ ለመጻፍ ብለው ተነሥተው ቢጽፉ ኖሮ ምን ሊጽፉ ነበረ ? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎች ጭንቅላቴ ውስጥ ተመላልሰዋል ።[1] በኋላ ፈላስፋው ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተማሪና መምህር እንደነበሩ ስሰማ በመጽሐፉ ውስጥ ያየሁት የሐሳብ ጥልቀት በዘመኑ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልሒቃን ዘንድ የነበረው ተዋሥኦ ሊደርስ ይንጠራራበት የነበረውን ልክ የጠቆመኝ መሰለኝ ።

ከዚያ በኋላ ያ የተዋሥኦ ልሕቀት የት ገባ ? እንዴት ድርቅና የተጫነው ተዋሥኦ ዋጠው ? እንዴት ኦርቶዶክሳዊነትን ከአመክንዮ የተፋታ እና አመክንዮን የሚፈራ ጭፍን እምነት የሚያስመስሉ የፎክሎር ሰባኪዎች ተፈለፈሉብን ?  የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህን ለመኾን የሚጠየቀው መስፈርት ስለምን ድፍረት የለበሰ አላዋቂነት መሰለ ? በሚዲያ ላይ ሲናገሩ በአላዋቂነታቸው አንገታችንን የማያስደፉን ካህናት ስለምን ቁጥራቸው አልበረክት አለን ? ኦርቶዶክሳዊነት ችግርን እና ጭንቀትን ለማረሳሳት የተጠመቀ ዕፀ-ዝንጋዔ (‘opium of the masses’) እስኪመስል ድረስ በኦርቶዶክሳዊነት ስም የገነነው ተዋሥኦ ለምን አላዋቂነት ተጫነው ? ቤተ ክርስቲያን ሲባል ከስሜታዊ ሙጥኝታ (sentimental attachment) ባለፈ ለሰው ልጅ ህልውናዊ ጥያቄ የተሰጠ ከሞት ፍርኃት በላይ ኾኖ የመኖር የሕይወት አማራጭ እንደኾነ የሚያሳይ ተዋሥኦ ራቀን ? የእጓለ ገብረ ዮሐንስን እምነትና አመክንዮ የተሰናሰሉበትን ኦርቶዶክሳዊ ተዋሥኦ አስቀጥለን ቢኾን ኖሮ እነዚኽ ከላይ የጠቃቀስኋቸው ሕመሞቻችን ይደርሱብን ነበረ ? እነዚኽን ጥያቄዎች የማነሣው በዚኽ ጽሑፍ መልስ ለመስጠት ሳይሆን ባለፉት 75 ዓመታት ኦርቶዶክሳዊው ተዋሥኦ የደረሰበትን ድቀት እንድናስተውለው ጥቂት ታዋቂ ቁስሎቻችንን ነካክቼ ሕመሙን ለማስታወስ እና የኤማሁስ መጽሔት ላይ የሚተጉት ለጋ እጆች ሊገምዱት የሚታትሩትን የተዋሥኦ ገመድ ከእጓለ ገብረ ዮሐንስ ተዋሥኦ ጋር ሰባ ዓመታት ወደ ኋላ ኼጄ የታሪክ ድራቸውን አንድ ላይ ልቋጥር ፈልጌ ነው ።

ይኽ ድር የተገመደው አሚን (faith) እና አመክንዮ (reason) ከሚባሉ ኹለት ክሮች ነው ። ከአመክንዮ የተፋታ እምነት ወደ ጥንቆላነት (superstition) ይወርዳል ። ከእምነት የተፋታ አመክንዮ ደግሞ መንፈሳዊው (spiritual)ን በስሜት (emotion)፣ ሰብአዊውን (human) በቁሳዊው (material) አጣፍቶ ሰውን ለቀቢጸ ተስፋ (nihilism) መንጋጋ ያስረክባል ። እስካሁን ከሰማኋቸው ፖድካስቶቻቸው በመነሣት የኤማሁሳውያን ሕልም በእምነት የበለፀገ አመክንዮ እና በአመክንዮ የጠራ እምነት ላይ የተሠራ የኦርቶዶክሳዊነት ተዋሥኦ መገንባት ይመስለኛል ። ሙግቶቻቸው ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ (Christocentric) ፣ ጥንታውያኑን አበውን ያገናዘቡ ፣ ከሐዋርያዊ ክርስትና ፍንክች ላለማለት የቆረጡ ናቸው ።

የኤርምያስ ክንዴ ‘ሐሳቦች መዘዝ አላቸው’ የሚል መጣጥፍ ይኽን ከምናይባቸው ጽሑፎች አንዱ ነው ። ኤርምያስ የነገረ ጾታን (የጾተኝነትን) ተዋሥኦ በማኅበራዊ ሚዲያ ከሚታየው አላዋቂነት ፣ ተንጨርጫሪነትና ተንጰርጳሪነት ከሚመሩት ጫጫታ አውጥቶ ነገሩን ከሥሩ አጥርቶ ለማሳየት ይሞክራል ። ድኅረ ዘመናዊነት ፣ ጾተኝነት (gender ideology) እና ከሰው-ባሻገሬነት (transhumanism) የቆሙባቸው ፍልስፍናዊ መሠረቶች በውስጣቸው ያለውን ኢተጠየቃዊነትና ተፋልሶ በማሳየት ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ቀናይቱን ህልውናዊ አማራጭ እንደሚያቀርብ ይጠቁማል ። የኤርምያስ መጣጥፍ ኹለት መሠረታዊ የሙግት ነጥቦች ነገረ ሰብእ (anthropology) እና ነገረ ዕውቀት (epistemology) ኾነው ታይተውኛል ።

ከነገረ ዕውቀት አኳያ ሲፈተሹ ፥ በጥቅሉ የድኅረ ዘመናዊነት አስተሳሰቦች በተለይም ደግሞ የጾተኝነት ርእዮተ ዓለም (gender ideology) “የማውቀው የሚሰማኝን ነው ፤ ስለዚኽም እውነት ማለት እኔ የተሰማኝ ነገር ነው ።” የሚል መሠረት ላይ ይቆማሉ ። ኤርምያስ ሌሎች ይኽን አስተሳሰብ የሞገቱ ዕውቅ ክርስቲያን ጸሐፊዎችን ተተግኖ ይኽንን የድኅረ ዘመናዊነት ዓምድ ስሕተት ይጠቁማል ። ይኽ የድኅረ ዘመናዊነት መንገድ ማኅበረሰባዊ ሥልጣኔ ሳይኾን እውነትን በማኅበር ተሰብስቦ የመካድና ማለቂያ ወደሌለው ውዥንብር የመገሥገሥ እብደት ነው ። የአስተያየት አገዛዝን የማስፈን ፣ ወይም የአንጻራዊነትን አምባገነንነት የማንገሥ ጉዞ (Dictatorship of relativism) ነው ።[2] ኤርምያስ በዚህ መንገድ የሚደረግ ጉዞ የሰውን ልጅ በእውነት አልባነት በረኀ ውስጥ ወደመሞት እንደሚያደርሰው ያስጠነቅቃል ።

ኹለተኛው ነጥብ ነገረ ሰብእን የሚመለከት ነው ። ኤርምያስ የጾተኝነት ርእዮተ ዓለም ለሰው ልጅ የሚሰጠው ብያኔ የሰውን ልጅ ማንነትና ክብር የማይገልጥ ስሑት ብያኔ እንደኾነ ይጠቁማል ። ጾተኝነት የሰው ብያኔውን የቀዳው ከእነ ኒቼና ሳርት ፀረ እግዚአብሔር ህልውናዊነት (atheist existentialism) ነው ። በዚያ የሐሳብ ፈለግ ደግሞ ሰው ራሱን የመፍጠር ፍዳ የተጣለበት ትርጉም አልባ ነገር ነው ። እነርሱ እንደሚሉት መነሻው አጋጣሚ መድረሻው ደግሞ ምንምነት ስለኾነ በዚኽ ወይም በዚያ መንገድ መኖሩ የሚያመጣው ምንም ዓይነት የሞራል ዕሴት የለም ፤ እንዲያውም እግዚአብሔር እና ሞራል የሚባሉ ሐሳቦች ሰው ፍላጎቶቹን እየተከተለ ራሱን እንዳሻው አድርጎ እንዳይፈጥር ዕንቅፋት ይኾኑበታል ፤ ስለዚኽ እነዚኽን ጠላቶቹን አሽቀንጥሮ ጥሎ በኢሞራላዊነት ፍላጎቶቹን ብቻ እየተከተለ ያሻውን ማድረግ አለበት ፤ ያሻውን ደጋግሞ በማድረግም ያሻውን መኾን ይችላል ።

ይኽ ፀረ እግዚአብሔር ህልውናዊነት ከውጪ ሲያዩት ሰውን የሚያከብር ፥ ለሰው ልጅ ቅድሚያ የሚሰጥ ይመስላል ። ነገር ግን ፥ ውስጡ ሲታይ እጅግ አደገኛና የሰውን ልጅ ራሱ በትርጉም አልባነት ራሱን እንዲጠላ የሚያደርግና ምናልባትም የሰውን ልጅ ሕይወት ከመናቅና ከመጥላት የመጣ አስተሳሰብ ይመስላል ፤ ዣን ፖል ሳርት “Hell is other people”[3] (ሲዖል ማለት ሌሎች ሰዎች ናቸው) እንዲል ። ጾተኝነትን ‘አሜን’ ብሎ የሚቀበል ሰው ይኽን ‘የሰው ልጅ ሕይወት ትርጉም አልባ ነው’ የሚለውን ነገረ ሰብእ ቢያውቀውም ባያውቀውም ‘አሜን’ ብሎ ይቀበለዋል ፤ የጾተኝነት ርእዮተ ዓለም የቆመበት መሠረቱ ነውና ።

ኤርምያስ ይኽን የጾተኝነትን ርእዮተ ዓለም መሠረት ለማፍረስ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ለሰው ልጅ የሚሰጠውን ብያኔ በማንጸሪያነት ያቀርባል ። የሰው ልጅ ለትርጉም አልባ ፍጻሜ ራሱን የመፍጠር ዕዳ የተሸከመ ነገር አይደለም ። በክርስቶስ ሙላት ክርስቶስን መስሎ ፥ ከእግዚአብሔር ጋር ፣ በእግዚአብሔር ውስጥ ፣ ለእግዚአብሔር ክብር በመኖር ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ አምላክ እንዲኾን የተፈጠረ የእግዚአብሔር መልክ ነው ፤ “ከሰዎች መካከል አማልክት ይኾኑ ዘንድ ለሚያምኑብኽ ቅን ኅሊናን የፈጠርኽ”[4] እንዲል ። ይኽ ብያኔ ሴት ወይም ወንድ ፣ ግሪካዊ ወይም አሜሪካዊ ፣ ሀብታም ወይም ድኃ ፣ ወዘተርፈ መኾንን ለሰው ልጅ መበየኛነት አይወስድም ። ከሰውነት የማሳነስ ወይም የማተለቅ ሚናም አይሰጣቸውም ። ክርስቲያናዊው ብያኔ የሰው ልጅ በምንም ኹኔታ ውስጥ ይኹን ፥ የትም ይኑር ፥ ሰው መኾን አለመኾኑን ፥ እንደሰው እየኖረ መኾን አለመኾኑን የሚለካው በክርስቶስ ኑሮ ልክ ነው ። ሰው የመኾን ልኩና ግቡ የእግዚአብሔር ልጅነት ስለኾነ እንደሰው መኖራችን የሚለካው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ኑሮ መጠን ነው ። ከእርሱ ያነሰ ልክና ሚዛን ለሰው ልጅ አይመጥነውም ። የሰው ልጅነት ማለት የእግዚአብሔር ልጅ መኾን የሚችል ፍጡር ነው ። የተፈጠረበት ዓላማ ፣ የሚኖረው ኑሮ ትርጉሙ ፣ ልኩ ፣ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ኦርቶዶክሳዊው የህልውና አማራጭ ይኽ ነው ።

የኤርምያስ ሙግት አሌክሳንደር ፑሽኪን እና የሞስኮ ጳጳስ የነበሩት ፊላሬት በግጥም ያደረጉትን ምልልስ ያስታውሰናል ። አንድ ቀን ፑሽኪን ጨለምተኝነት ጎበኘውና እንዲኽ ብሎ ገጠመ፦

Useless gift, accidental gift,

Life, why were you given me?

Why are you given by fate’s secret will

As punishment or as reward?

Who sent you down to me?

Death’s enigma or life’s mocking breath?

I do not know you — what use are you?

Or why do I suffer and die?

ግጥሙም የብዙዎችን በባዶነት ጩኸት የሚሰቃይ ሐዘንተኛ ልብ ነካው መሰል ብዙዎች ወደዱት ። በዚኽ ጊዜ ሊቀ ጳጳሱ ፊላሬት እንዲኽ ሲሉ በይፋ ለፑሽኪን መልስ ሰጡ፦

Not in vain and not by chance

Was life’s gift given to you.

Not without the will of Heaven

Did your soul begin to burn.

In yourself — look, and discover:

Both the source of pain and hope.

Believe: from Heaven’s highest realm,

God watches over every soul.

ፑሽኪን ይኽን ግጥም አንብቦ ሐሳቡን በይፋ ቀይሯል። ኤርምያስም ገብቷቸውም ይኹን ሳይገባቸው ጾተኝነትን ሙጥኝ ያሉትን አለቃቃሽ ነፍሶች ሐሳባቸውን ይቀይሩ ዘንድ ይጣራል ፤  የሰው ልኩ ክርስቶስ ነውና ።

፨ ፨ ፨

[1] “ብፁዓን ንጹሐነ ልብ” የሚለውን ሥራቸውንም አንዘነጋም።

[2] “The tyranny of relativism” Benedict XVI, Light of the World: The Pope, The Church and The Signs Of The Times. A Conversation with Peter Seewald (San Francisco: Ignatius Press, 2010), 50-54.

[3] Sartre, Jean-Paul, No Exit: A Play in One Act (United Kingdom: French), 1958.

[4] “ዘፈጠርከ ኅሊናተ ርቱዓተ ለእለ የአምኑ ብከ ከመ እምሰብእ ይኩኑ አማልክተ” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ “መጽሐፈ ኪዳን፣” in መጽሐፈ ቅዳሴ፤ መዝገበ፡ ቅዳሴ፡ ዘደብር፡ ዓባይ (አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ የመጻሕፍት ማተሚያ ድርጅት፣ 1984).

Share...

Facebook
Telegram
WhatsApp
X
Email
Print
5 Comments
  • rainyrace
    rainyrace
    August 14, 2025 at 3:21 pm

    ቃለ ሕይወት ያሰማልን እኔም “ሐሳቦች መዘዝ አላቸው” የሚለውን ካነበብኩ በኋላ የተሰማኝ ይህ ነበር እርሶ በመልካም ቃል ገልጠውታል። የኔን ዘመን ወጣት አለማንበብ ርእዮቶችን ጠለቅ ብሎ አለመፈተሽ ወደ ማይነሳበት ውድቀት እየመራው ነው።

    Reply
  • Yitayal
    Yitayal
    August 14, 2025 at 3:33 pm

    It is nice especially for current generation and it is better to continue

    Reply
  • ዓለማየሁ ነጋ
    ዓለማየሁ ነጋ
    August 14, 2025 at 4:01 pm

    በዶክተሩ ጽሑፉ ከተነሳው ሐሳብ በተጨማሪ በፈረንጅ አፍ የሚታወቁትን ቃላትና ሐረጋት ወደ ሀገርኛ ቋንቋ የተመለሱበት መንገድ ይማርካል።

    Reply
  • ልዑል
    ልዑል
    August 14, 2025 at 4:53 pm

    እግዚአብሔር ይስጥልን

    Reply
  • Anteneh tafese
    Anteneh tafese
    August 14, 2025 at 7:42 pm

    ጥሩ እየታና አስተያየት ነው።

    Reply
Leave a Reply to rainyrace Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

Guest Posts
መሐሪ ዘመልአክ

የአእላፋት ዝማሬ ምልክት ነው ።

መግቢያ በዘመናችን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታየው “የአእላፋት ዝማሬ” የተባለው ክሥተት ሰፊ የሆነ ሕዝባዊና ሊቱርጊያዊ ውይይት አስነስቷል። አንዳንዶች ይህን እንቅስቃሴ እንደ መንፈሳዊ ንቃትና የራቁ ምእመናን ተሳትፎ መመለሻ ሲያቀርቡት፣ ሌሎች ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሊቱርጊያ[1] ጋር የሚጋጭ እና ሥርዓታዊ መነሻዋን የሚያዳክም ክዋኔ እንደሆነ ይገምግሙታል። ወንድማችን በርናባስ ሽፈራው የጻፈው “የአእላፋት ዝማሬ”ን የተመለከተ የኤማሁስ ገጽ ጽሑፍ አንዳንዶችን ሲያበሳጭ፣ ሌሎችን ሲያሳስብ እንደሰነበተ በአረቦን ቴሌግራም ቻነል ላይ ተመልክቻለኹ። 23 ገጾችን የያዘ፣ ንዑሳን አርእስት በግልጽ ያልተሰጡት ረዥም ጽሑፍ ስለኾነ ጊዜ ሰጥቶ ማንበብን፣ ካነበቡም በኋላ ዐበይት መከራከሪያዎቹን ማጥለልን ይጠይቃል። እንዲኽም ኾኖ፣ ቢያንስ መሠረታዊ የኾነ የሊቱርጊያዊ ነገረ መለኮት (liturgical theology) ንባብ ለሌለው ሰው ጽሑፉ ከንቱ ምቀኝነት፣ መራራነት፣ አማራሪነት፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ ሊመስል ይችላል። በዋናነት እየነቀሰ የሚተቸው “የአእላፋት ዝማሬ”ን ልዩ ልዩ መልኮች ይኹን እንጂ፣ መሠረታዊ ጉዳዩ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአኹኑ ጊዜ ያለችበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ (liturgical crisis) መጠቆም ኾኖ አግኝቼዋለኹ። ጉዳዩ እኔንም ሲያሳስበኝ የነበረ ነገር ስለነበረ የበርናባስን ሐሳብ እንዲኽ ልለጥቀው ወደድኹ። የእኔ ጽሑፍ የ“የአእላፋት ዝማሬ”ን እንደ ምልክት በመመልከት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ የምትገኝበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ ይጠቁማል። በተለይም በቋንቋ ባዕድነት፣ በዜማ ውስብስብነትና በሰዓት ምቹ አለመኾን ምክንያት ምእመናን ከ“ሰዓታት ጸሎት” የራቁበትን ኹኔታና ኮንሰርታዊ ዝግጅቶች በተግባር የተኩት የሊቱርጊያ ባዶ (liturgical vacuum) ምን እንደሆነ ለማመልከትና መፍትሔውን ለማሳየት ይጥራል። The Problem of Reactive Ministry እና Institutional Survivalism በርናባስ በጽሑፉ የሚተቸው አንዱ ነገር ይኽ ተልእኮን

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

“የአእላፋት ዝማሬ”

ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ ባለፈው ዓመት በልደት ዋዜማ ተካሔደ ። በአዘጋጆቹ እና በተሳታፊዎቹ ዘንድ ይህ ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው ዙር በላይ ያማረ እና የሠመረ ሆኖ ተቆጥሯል ። በጠቅላላው ከምእመናን በኩል በተሳትፎም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘው ተቀባይነት ሌሎች ሁነቶች ሲሆኑ እንደምናየው በጅምር የሚቀር ሳይሆን እንደ ባህል የመተከል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን ያመላክታል ። እንዲያውም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ብቻ ሳይወሰን ወደ ሌሎች ቦታዎችም እንዲሰፋ የሕዝብ ጥያቄ እና በአዘጋጆቹም በኩል እቅድ መኖሩ ይታወቃል ። ስለዚህ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ልክ እንደ ጥምቀት ሁሉ በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ (የአዘጋጆቹ አቅም በፈቀደው ልክ) የአእላፋት ዝማሬ የልደት በዓል መለያ ሆኖ እንዲካሔድ መጠበቅ እንችላለን ። ይህ ነገር በብዙዎች ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጥቅም የሚሰጥ ሆኖ ይታያል ። በእነርሱ ዐይን ይህ ሁነት ቤተ ክርስቲያን በብዙዎች ዘንድ እንድትታወቅ ያደርጋል ። ብዙዎች በዓሉን አስመልክተው ከሚሔዱባቸው የማይገቡ ዓውዶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ ከማድረጉ ባሻገር ፥ በቤተ ክርስቲያን ሱታፌ ያላቸውንም በሚስብ እና በሚገባቸው መልኩ ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ እንዲያውቋት ያስችላቸዋል ። ስለዚህም የሌሉትን በመጥራት ፥ ያሉትንም በማጽናት ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን እንድትዋጅ የሚያስችላት መሣሪያ ነው ፤ ከእርሷ ዘንድ ወደ ክሕደት እና ወደ ኑፋቄ የፈለሰውን ፥ ወይም በስም ክርስቲያን ሆኖ እና ማዕተብ አስሮ ሳለ በምድራዊ ተድላ ባሕር የሰጠመውን ወጣት ወደ ራሷ የምትስብበት መረብ ነው ። ነገር ግን ከኖረው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና አስተምህሮ አንጻር ከመረመርነው ፥ ይህ ሁነት

Read More »
Emmaus Posts
ኤልያስ ገብረ ሥላሴ

መከራ ፣ እከይ እና ክርስትና

መከራ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ድንገተኛ የሆነ ክስተት አይደለም ። ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ለጥቅማችን የሚፈቀድ የእርምት መንገድ ነው እንጂ ። በየዘመኑ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ሁነቶች እንድትወጠር እና መሠረታዊ ነገሮች ትኩረት እንዳያገኙ የሚቀርብ ፈተና አለ ። ሰበር ዜናዎች ፣ ወቅታዊ አጀንዳዎች ፣ አከራካሪ ጉዳዮች ወዘተ ከመነኩሴ መቁጠሪያ በላይ በሚሽከረከሩበት ዘመን ላይ ነው የምንገኘው ። እነዚህ ሁነቶች ትኩረታችንን ይወስዱትና ሳይታወቀን መሠረታዊ ከሆኑትና ዘለዓለማዊነታችንን ከሚበይኑት ጉዳዮች ወጥተን ምድራዊና እዚሁ ቀሪ በሆኑ ጉዳዮች ተወጥረን እንገኛለን ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁኔታ በቤተክርስቲያንን መምህራን እና “ተጽዕኖ ፈጣሪዎች” ላይ እጅግ በርትቶ የሚታይ መሆኑ እና በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እና መድረኮች ሳይቀር ሰፊውን ሰዓት መያዙ ነው ። የቤተክርስቲያን ተልእኮ ስለ ክርስቶስ ምስክር መሆን ነው ። መሠረታዊ ካልሆኑት ሁነቶች ወጥተን ወደዚህ ዋነኛ ተልእኮአችን እንድንመለስ ተዋሥኦ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ። ይህ በምእመናን ፥ በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲን አገልጋዮች ፥ ዘንድ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ። የሁነቶችን መሠረት መመርመርና ትክክለኛ ባሕርያቸውን መረዳት ያሻል ። ሁነቶቹ ችግሮች የሆኑ እንደሆነ ሥር ነቀል መፍትሔ ማሰብ የሚቻለው ፥ መልካም አጋጣሚዎችም ከሆኑ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ልናውላቸው የምንችለው የሁነቶቹን መሠረት በጥልቀት መረዳት ከቻልን ነው ። በመቀጠልም ተከትለው ሊደረጉ ስለሚገቡ ነገሮች መወያየት ከተቻለ ብቻ ነው ። ካልሆነ አሁን እየሆነ እንዳለው የወቅታዊ አጀንዳዎች አሳዳጅ ብቻ ሆነን ነው የምንቀረው ። በተለይ ዘመናችን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ስለሆነ በዚህ

Read More »
Emmaus Posts
ኤማሁስ

የኤማሁስ መንገድ

መጽሔቷን ለማግኘት ይህን ይጫኑ . . . የዘመናችን ተዋሥኦ በይዘቱም ሆነ በመንገዶቹ በግልብነት በእጅጉ የተጠቃ ነው ። ‘በይዘቱ እንዴት ?’ቢባል ሁነቶች ላይ ያተኮረ እና ወቅታዊነትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ። አንድም አቋም ከመያዝና ጎራ ከፍሎ ከመናቆር ባለፈ የእውነት የመማር እና የማሰላሰል ጉጉት የማይታይበት በመሆኑ ። በዚህ ተዋሥኦ ውስጥ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሣት እና ከሁነቶቹ የሚሻገር እና ሐሳባዊ የሆነ ትንተና ለማካሔድ መሞከር ትኩረት ያስነሣል ፤ ሲብስም አጉል እንደመራቀቅ ይታያል ። የሚካሄድበት ከባቢ እና ዘመን ደግሞ ሌላ ግልብነት ደርቦለታል ። በእኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሀገራት ፣ ከዘመናዊነትና ከቴክኖሎጂ መራቀቅ ጋር ተያይዞ ሕዝባዊ ተዋሥኦ በጠቅላላው ስለቱን እና ርቀቱን እንዲያጣ ሆኗል ። የሚነበብም ሆነ የሚታይ ወይም የሚደመጥ ነገር አጭር መሆን አለበት ። ነገር ግን ጠቃሚና ወሳኝ ርእሶች እንዲህ ባለ መንገድ ሊስተናገዱ አይችሉም ። የሚያጠግብ ፍሬ ከሌለበት የተመልካቹ እና የአንባቢው ብዛት ምን ጥቅም ይኖረዋል ? እንዲህ ባለው ከባቢ ውስጥ ሁነቶችን ከሁነትነታቸው እና ከሚያመጡት ወቅታዊ ውጤት በተሻገረ መልኩ ለመመልከት እንቸገራለን ። ቀድሞውኑም (እይታችን ከመጥበቡ የተነሣ) ጠባብ አድርገን የቀረጽነውን አጀንዳ በምንገልጽበት መንገድ የበለጠ እናጠብበዋለን ። ነገር ግን ሁነቶችን እና ሒደቶችን ከመሠረታቸው መመርመራችን እና የምናቀርባቸው መፍትሔዎችም እንዲሁ የማይናወጥ መሠረት ያላቸው መሆናቸው አስፈላጊ ከሆነ ተዋሥኦውም እንዲሁ የጠለቀ እና የረቀቀ መሆን አለበት ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ጊዜ ወስዶ ማሰብ ፣ ማንበብ ፣ ማጠናቀር ፣ መወያየት ፣ መሟገት እና እንዲህ ካለው ሒደት

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

ክፍል ፭ ፡ ወደ ርስታችን ያልተመለስንበት ኢዮቤልዩ

ሩሲያዊው ደራሲ ፌዮዶር ዶስቶየቭስኪ በ1860ዎቹ አውሮፓን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኝ የታዘበውን በዘገበበት ማስታወሻው የለንደን ድሆች ቅዳሜ ማታን እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያሳልፉ ይነግረናል ። በቅድሚያ ሌሊቱን በሙሉ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ጭምር ደስታ ፈጽሞ በተለየው ፣ ድብርት በተጫነው መንፈስ አኳዃን ሲበሉ እና ሲጠጡ ፣ ከሕይወታቸው መራራነት ለማምለጥ ፣ ራሳቸውን ፍጹም ለማደንዘዝ በሙሉ ጥምብዝ እስኪሉ እንደሚሰክሩ መስማቱን ይዘግባል ። ሳምንቱን ሙሉ ሠርተው የቋጠሯትን ገንዘብ ቅዳሜ ሌሊት እንዲህ ይበትኗታል ። አስከትሎም እንዲህ ባለው አንድ ምሽት እሱ ራሱ በመንደራቸው ውስጥ ሲያልፍ የታዘበውን እና የተሰማውን እንደሚከተለው ይመሰክራል ። “One such night – it was getting on for two o’clock in the morning – I lost my way and for a long time trudged the streets in the midst of a vast crowd of gloomy people, asking my way almost by gestures, because I do not know a word of English. I found my way, but the impression of what I had seen tormented me for three days afterwards. The populace is much the same anywhere, but there all was so vast, so vivid that you almost physically felt things which up till then you had only imagined. In London, you no longer see the populace. Instead, you see a loss of sensibility, systematic, resigned and

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

ብያኔን አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ

ከሁለት ሳምንታት በፊት ‘ከጥያቄዎቹ በላይ አደገኛ የሆኑት መልሶች’ በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ አቅርበን ነበር ። ጽሑፉ በዋናነት ማሳነስ (reductionism) የተባለውን ፅንሰ ሐሳብ የሚያነሣ እና የሚተች ነው ። በዚህ ጽሑፋችን ውስጥ መምህር ያረጋል አበጋዝ በቅርቡ ‘ወደ ላይ አያዳልጣችሁ’ በሚል ርእስ ገዳማዊ ሕይወትን ከዘነበ ወላ ዘለፋ ለመከላከል ጽፎ ያጋራውን ጽሑፍ ተችተናል ። ርእሱን በዚህ ጊዜ ጉዳይ ያደረግነውም በዋናነት በምምህር ያረጋል ጽሑፍ ምክንያት ነው ። በተለይ ጽሑፉ ሰፊ ተነባቢነት እና ተቀባይነት ያገኘ እንደ መሆኑ በውስጡ ያየነውን የማሳነስ ዝንባሌ መተቸቱ ጠቃሚ ይሆናል ብለን አመንን ። ነገር ግን የመምህር ያረጋል ጽሑፍ መነሻ ቢሆነንም በይበልጥ ፅንሰ ሐሳቡ ላይ ለማተኮር ነው የሞከርነው – ዓላማችን ነገሩ ላይ ተዋሥኦ እንዲጀመርና የተሻለ መረዳት እንዲፈጠር ማድረግ ስለሆነ ። መምህር ያረጋልም ጽሑፉን ተመልክቶ ምላሽ ሰጥቶናል ። ምላሽ በመስጠቱ ደስ ብሎናል ። በምላሹ ግን አልተደሰትንም ። አለመደሰታችን እኛ በእርሱ ጽሑፍ ላይ ያቀረብነውን ትችት ባለመቀበሉ አይደለም ። ይልቁንም የተሰጠው ምላሽ ከእኛ ትችት ጋር እምብዛም የተያያዘ ባለመሆኑ እንጂ ። ከነገሩ ጋር የማይገጥሙ ምሳሌዎች ቀርበዋል ። ያቀረብነው ሂስ በተሳሳተ መንገድ ተተርጉሟል ። በጽሑፋችን በስም ጠርተን ያራቅነው እና ያነወርነው ሐሳብ የእኛ አቋም ተደርጎ ተገልጧል ። “ለቤተ ክርስቲያን ከልባችን ከመጨነቅና ከመቅናት” ተነሥተን “ያልተባለውን ለማስመሰል በመድከማችን” ተወቅሰናል ፤ ዕጣችን ሆኖ “ሳንነቅፍ መጻፍ አልቻልንምና” ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች መልስ እና እርማት የሚሹ ሆነው አግኝተናቸዋል ። አንድም ለእኛም ሆነ ለመምህር ያረጋል

Read More »