በፍጹም ለመነቃቀፍ የጠፋ ጊዜ አልነበረም

መምህር ያረጋል ለዘነበ ወላ የሰጠውን መልስ ተከትሎ በኤማሁስ ፕሬስ ጸሐፍት በኩል የቀረበው ትችት አግባብ አለመሆኑን የሚገልጥ አንድ ጽሑፍ አጋርቶናል። ጽሑፉም እዚሁ ገጽ ላይ የወጣ ስለሆነ ብዙ ሰው ያነበበው ይመስለኛል። ያረጋል በዚህ ጽሑፉ ሁለት ነገሮችን ማስተላለፍ የፈለገ ነው የሚመስለኝ። የመጀመሪያው ለዘነበ ወላ የሰጠው መልስ ፈጽሞ በ’reductionism’ የሚከሰስ አለመሆኑን ማሳየት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ጸሐፍቱ እንዲያው እሱን እንንቀፈው ብለው ካልሆነ በስተቀር የጻፉትን የሚያጽፍ ምክንያት ከእርሱ ጽሑፍ ውስጥ የማያገኙ መሆኑን መጠቆም የፈለገ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

በርግጥ በዚህ ጽሑፍ እኔ ማተኮር የፈለግሁት ሁለተኛው ላይ ቢሆንም፣ ከ“reductionism” ጋር በተያያዘ ስለተነሣው የመጀመሪያው ጉዳይ ግን ትንሽ ነገር ልናገር። ‘reductionism’ (የራሱን የያረጋልን ትርጉም ልጠቀምና – ክርስትናን ወደ ምድራዊ እሳቤና መለኪያ ዝቅ ማድረግ) የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ከልዕልናው አውርዶ ጊዜያዊ ለሆኑ ሌሎች የኑሮ ዘይቤዎች ተገዢ የሚያደረግ  አደገኛ መንገድ ነው። በመሆኑም በነገረ መለኮት ሊቃውንት ደረጃ በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያሉ ውይይቶች መደረግ ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል። በኤማሁስም በኩል፣ ይኼ ርእሰ ጉዳይ ሲነሣ፣ የኤርሚያስ እና የበርናባስ ጽሑፍ የመጀመሪያው አይደለም። ያረጋል ከጻፈው ጽሑፍ ጋር ሳይገናኝ፣ ከአሁን በፊት በሠራናቸው ፖድካስቶች ማሳነስን (reductionism) እንደ አንድ አደገኛ ዝንባሌ ስናነሣ እንደነበር ሲከታተሉን የነበሩ ሰዎች የሚያስታውሱ ይመስለኛል። ነገር ግን ስለነገሩ ምንነትም ሆነ ስላለው አደጋ ገና እንዳልተግባባን እና በዚሁ ጉዳይ ከዚህም በላይ ገፋ አድርገን መነጋገር የሚገባን ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ይኼው የያረጋል መልስ ይመስለኛል። ያረጋል ጽሑፉን ለመከላከል የቅዱሳት መጻሕፍትን አቀራረብ ያነሣበት አግባብ፣ የቀረበበትን ትችት “ስለ አንድ ጉዳይ ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ እንዲገለጥ” ከመፈለግ ጋር ያነጻጻረበት መንገድ፣ ገፋ ሲልም መልስ የሰጠበትን መንገድ “ዐለምን ከመዋጀት” ጋር ያገናኘበት ሂደት፣ እውነቱን ለመናገር፣ አሳብ ለአሳብ እንዳልተገናኘን የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በርእሰ ጉዳዩ ላይ በቂ ጊዜ ወስደን መነጋገር እንዳለብን የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው። ስለዚህ እንደጀመርን ውይይቱን መግፋት እንዳለብን ይሰማኛል። በዚሁ መሠረት አሳቡን የበለጠ ለውይይት ክፍት ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ኤርሚያስ እና በርናባስ በዚሁ ርእሰ ጉዳይ ሁለተኛ ጽሑፋቸውን በዚሁ ገጽ በቅርቡ እንደሚያቀርቡ  እየጠቆምሁ፣ እኔም የማሳነሱን (reductionism) ነገር ለእነርሱ ላቆየዉና ዛሬ ማተኮር ወደፈለግሁበት ሁለተኛው ነገሬ ልግባ።

መምህር ያረጋል በጽሑፉ መጨረሻ አካባቢ፣ የነገሮቹ ሁሉ መነሻ የሆነው የዘነበ ወላ ነቀፌታ ወደ ጎን ተብሎ፣ ፈጽሞ የእሱ አሳብ ወዳልነበረው ርእሰ ጉዳይ ጽሑፉ መወሰዱ ቅር እንዳሰኘው ተናግሯል። በርግጥ ይኼንኑ ስሜት፣ ሲሰጡ በነበሩ ሌሎች አስተያየቶች ውስጥም አስተውለናል። ለማስታወስ ያህል ግን፣ በኤማሁስ በኩል የቀረበው ጽሑፍ ምንም እንኳን ዋና ትኩረት አድርጎት የነበረው ጽንሰ አሳብ ላይ ብዙ ጊዜ የወሰደ ቢሆንም፣ የዘነበን ንግግር ግን ሙሉ ለሙሉ በዝምታ ያለፈ አልነበረም፤ በተናጋሪው ሰው ደረጃ እና ልክ በአጭሩ አሳብ ተሰጥቶበታል። ከዚያ በላይ የዘነበ ንግግር ላይ ሰፊ ትንተና ለማቅረብ የሚያስችል ቁም ነገር ነበር ብለን ግን አናምንም። የዘነበ ዓይነቱ ትችት ስለ ቤተ ክርስቲያን ሩቅ እና ከላይ ከላይ የሆነ ግንዛቤ ካላቸው ሰዎች አንደበት የሚጠፋ አይደለም። ነገሩ ከአንድ ከዘነበ ጋር ብቻ የተያያዘ አለመሆኑን ያረጋልም መጠቆሙም ትክክል ነው። ስለዚህ እኛ የመረጥነው መንገድ ውይይቱን በጽንሰ አሳብ ደረጃ ማድረግን ነበር። በኤማሁስ በኩል የቀረበው ጽሑፍ ፍሬ ነገር  በቀጥታ ቢነገር ፣ ቤተ ክርስቲያን ላይ ለተሰነዘረ የሐሰት ክስ የምንሰጠው መልስ፣ ለክስርትና እምነት መሠረታውያን እውነቶች የተገዛ መሆኑን እና እንደ ዘነበ የተናጋሪውንም ይሁን ሌሎች ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ግንዛቤ እና አመለካከት ላይ ለውጥ ሊያመጣ በሚችል መልኩ እንዲቀርብ የታሰበበት መሆኑን መፈተሽ አለብን የሚል ነው። የያረጋልን ጽሑፍ ከ’reductionism’ አንጻር ማየት የመፈለጉ ምክንያትም የመጣው ከዚሁ መሠረታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነበር። ያረጋል እንደመሰለው፣ እሱ ማንሣት የፈለገውን ነገር ወደ ጎን ብለን፣ ግንኙነት የሌለው ነገር (እሱ እንዳለው ‘ያልበላን ማከክ’) በማንሣት ‘ሌላ reductionist’ እየሆንን ሳይሆን፣ ቢያንስ የያረጋል ጽሑፍ በዚህ በኩል ክፍተት ሊኖርበት አይገባም ነበር ከሚል ወንድማዊ ቅናት የመነጨ መሆኑ ቢታሰብ ደስ ይለኛል።

ይኼን ስንል ግን፣ ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጪም በፈተና ተወጥራ ባለችበት በዚህ ወቅት እንደሚኖር ሰው፣ የዘነበ ዓይነቱ ትችት ሊፈጥረው ከሚችለው ስሜት ነጻ ሆነን አይደለም። ‘ዘመድ ቄስ እየፈታ ያለቅስ’ እንደሚባለው፣ ማዘንንም፣ መፍታትንም በአንድ ላይ እንድናከናውን ግድ ያለ ዘመን ላይ ስለወደቅን፣ በትዕግስት እና በጥንቃቄ የመሥራትን ሕመም ከመሸከም ውጪ አማራጭ የለንም ብለን ስለምናስብ እንጂ። ይኼንን እንድናደርግ የሚያደርገን ደግሞ፣ የቆምንበት የክርስትና እውነት ነው። ስለዚህ ዘነበ ወላ “ዝም በል” የተባለበት መንገድ ትክክል ነው፣ አይደለም? ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገንም ሌላ ነገር ሳይሆን የቆምንበት ይኼው የራሳችን እውነት ነው። እውነቱን ለመናገር፣ ለያረጋል ይኼንን በጽንሰ አሳብ ደረጃ የሚነግሩት ሆኖ አይደለም፤ ነገር ግን እሱ ብቻ ሳይሆን የሁላችንንም ሚዛን የሚያስት  ጫና ውስጥ ነውና እየኖርን ያለነው፣ ኃይላችንም አቅማችንም እውነታችን ላይ እንጂ ሌላ ቦታ ላይ የማይገኝ መሆኑ በስሜት እንዳይዘነጋ ለማሳሰብ ያህል ነው።

በርግጥ እዚህ ላይ ሳይነሣ መታለፍ የሌለበት፣ ከዘነበ ጋር የተያያዘው ሰሞንኛው ነገር ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ ከዕቅበት እምነት ጋር በተያያዘ የምንሠራቸው ሥራዎች፣ በጫናው ምክንያት፣ ብዙ ጊዜ ሚዛናቸውን ይስታሉ። ብዙ ማሳያዎችን ማንሣት ይቻላል፤ ይኼ የእኔ ትዝብት ብቻም አይመስለኝም። ዝርዝሩን አቆይቼ መፍትሔ ወደምለው ስመጣ ግን፣ ዕቅበተ እምነትን መንገድ በሚያቋርጥ ሰው መመሰል የሚቻል ይመስለኛል። መንገድ የሚያቋርጥ ሰው በግራም በቀኝም ያለውን እንቅስቃሴ ዕያየ እንደሚሻገረው ሁሉ፣ ዕቅበተ እምነታችንም ሙሉ በሙሉ ፊቱን በግራ በኩል ወደ መጣው አደጋ አዙሮ ሳይሆን፣ በቀኝ በኩል የሚመክቱለት ወዳጆቹንም ዞር ብሎ ዕያየ ካልተሻገረ መንገዱ መሀል ከቀኝ በኩልም ሊመጣ በሚችል አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ማሰብ ያለበት ይመስለኛል። እኛም ብንሆን፣ ወደ ቀኝ ዞር ብለን ያረጋልን ማየታችን ከዚሁ ከጥንቃቄ አንጻር እንጂ ‘ከትብብር ይልቅ ነቀፌታን የመምረጥ’ ፍላጎት በፍጹም አልነበረም።

በዚሁ ምክንያት፣ ያረጋል የኤርሚያስን እና የበርናባስን ጽሑፍ የነቀፋ እና የፍረጃ አድርጎ መውሰዱ ትክክል አይደለም። እንደ ኤማሁስ፣ የቤተ ክርስቲያንን ችግር መፍታት የምንችለው ጠንካራ እና ደፋር ጥያቄዎችን እያነሣን ለመነጋገር ፈቃዱ እና ተነሣሽነቱ እሰካለ ደረስ ነው የሚል እምነት እንዳለን በተደጋጋሚ እናነሣለን።  በዚሁ መሠረት ለውይይት መቅረብ አለባቸው ብለን የምናስባቸውን ነገሮች ወደ ሕዝቡ ለማቅረብ እንሞክራለን። ለያረጋልም የተሰጠው መልስ በዚሁ አግባብ የቀረበ እና ለተመሳሳይ ዓላማ የተጻፈ ነው። እሱም የጻፈውን ነገር፣ የጻፈውን ያነበቡም ያነበቡትን ነገር መለስ ብለው እንዲያዩ፣ ግራ ቀኙን እንዲመረምሩ በማሰብ ለአንድ ዓላማ የተጻፈ እንጂ በፍጹም ለመነቃቀፍ የቀረበ ጽሑፍ አልነበረም።  ይኼ ደግሞ ምቾት የመንሳት ነገር ቢኖረውም፣ የግድ መለመድ አለበት ብለን ግን እናምናለን። ከዚህ ውጪ ለችግሮቻችን መውጫ አለ ብለን አናስብምና። በዚሁ መልኩ መረዳት  ቢቻል እላለሁ።

Share...

Facebook
Telegram
WhatsApp
X
Email
Print
6 Comments
  • Temesgen Wana
    Temesgen Wana
    October 3, 2024 at 7:13 pm

    እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!

    -ቀጣዩን የተዋሥኦ ክፍል እጠብቃለሁ። ኤማሁስ ቤተሰብ በርቱ!

    Reply
    • አፍቅሮተ አዳም
      አፍቅሮተ አዳም
      October 3, 2024 at 7:57 pm

      ቅንነትን መሠረት ያደረገ ትችት፥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥብቅና እቆማለሁ የሚል ማንም አገልጋይ ሊፈራውም ሆነ ሊሸሸው የማይገባ ነው። በመሆኑም፥ እያንዳንዱ አገልጋይ ራሱን ለእንደዚህ ዓይነት ትችት ዝግጁ ማድረግ አለበት። እንዲህ ዓይነቱ ትችት ባለመለመዱ ብዙ ችግር እንዳጋጠመን አስባለሁ። ይህንኑ አካሄድ መከተሉ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሯችን ነጥሮ አንዲወጣ የራሱ ሚና ይጫወታል ብየ አምናለሁ።
      ውድ የኤማሁስ ቤተ ሰብ በርቱ ቀጥሉበት እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎታቹህ ያስፋ።

      Reply
    • EndashawT
      EndashawT
      October 4, 2024 at 7:01 am

      Great perspective and it’s very thoughtful.
      Stay blessed

      Reply
    • Anonymous
      Anonymous
      October 4, 2024 at 6:37 pm

      Guys watching some of ur videos u guys are very bold. But concerning u and Yaregal , u could have prepared concrete response to that fiction writer. ቤቱን አሮጌ ነዉ አትበለዉ።build a new house near by. ቤቱ ለራሱም ምስክር ለዛም ጉድለት ማሳያ ይሆናል። i sympathize with ur concern but he is an icon , ur battles decreases his influence.

      Reply
  • temesgen
    temesgen
    October 4, 2024 at 4:51 am

    እርግጠኛ መምህራችን ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ እንዲህ ያለውን መልካም ቅናት እንደሚደግፍ።እግዝአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን።ኤማሁስ podcast ደግሞ ንቁ በሆኑ ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ በጣም እየተወደደ ነው በየ telegram group ማየው አስተያየት ይህንን ነው ሚያሳየው በርቱልን

    Reply
    • Kidist
      Kidist
      October 7, 2024 at 12:02 pm

      I am glad this ‘conversation’ happened here. It is good to discuss ideas, opinions and understandings, so each can take note of what is happening. I think its good you have commented on Memhir Yaregal’s post and that he has responded to your criticism. And now you are responding again.
      I believe this is the way to go, criticizing each others ideas and refining the way towards the same goal you are working to achive. (Which i belive is Saving Souls)

      Reply
Leave a Reply to EndashawT Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Posts

Guest Posts
መሐሪ ዘመልአክ

የአእላፋት ዝማሬ ምልክት ነው ።

መግቢያ በዘመናችን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታየው “የአእላፋት ዝማሬ” የተባለው ክሥተት ሰፊ የሆነ ሕዝባዊና ሊቱርጊያዊ ውይይት አስነስቷል። አንዳንዶች ይህን እንቅስቃሴ እንደ መንፈሳዊ ንቃትና የራቁ ምእመናን ተሳትፎ መመለሻ ሲያቀርቡት፣ ሌሎች ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሊቱርጊያ[1] ጋር የሚጋጭ እና ሥርዓታዊ መነሻዋን የሚያዳክም ክዋኔ እንደሆነ ይገምግሙታል። ወንድማችን በርናባስ ሽፈራው የጻፈው “የአእላፋት ዝማሬ”ን የተመለከተ የኤማሁስ ገጽ ጽሑፍ አንዳንዶችን ሲያበሳጭ፣ ሌሎችን ሲያሳስብ እንደሰነበተ በአረቦን ቴሌግራም ቻነል ላይ ተመልክቻለኹ። 23 ገጾችን የያዘ፣ ንዑሳን አርእስት በግልጽ ያልተሰጡት ረዥም ጽሑፍ ስለኾነ ጊዜ ሰጥቶ ማንበብን፣ ካነበቡም በኋላ ዐበይት መከራከሪያዎቹን ማጥለልን ይጠይቃል። እንዲኽም ኾኖ፣ ቢያንስ መሠረታዊ የኾነ የሊቱርጊያዊ ነገረ መለኮት (liturgical theology) ንባብ ለሌለው ሰው ጽሑፉ ከንቱ ምቀኝነት፣ መራራነት፣ አማራሪነት፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ ሊመስል ይችላል። በዋናነት እየነቀሰ የሚተቸው “የአእላፋት ዝማሬ”ን ልዩ ልዩ መልኮች ይኹን እንጂ፣ መሠረታዊ ጉዳዩ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአኹኑ ጊዜ ያለችበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ (liturgical crisis) መጠቆም ኾኖ አግኝቼዋለኹ። ጉዳዩ እኔንም ሲያሳስበኝ የነበረ ነገር ስለነበረ የበርናባስን ሐሳብ እንዲኽ ልለጥቀው ወደድኹ። የእኔ ጽሑፍ የ“የአእላፋት ዝማሬ”ን እንደ ምልክት በመመልከት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ የምትገኝበትን ሊቱርጊያዊ ቀውስ ይጠቁማል። በተለይም በቋንቋ ባዕድነት፣ በዜማ ውስብስብነትና በሰዓት ምቹ አለመኾን ምክንያት ምእመናን ከ“ሰዓታት ጸሎት” የራቁበትን ኹኔታና ኮንሰርታዊ ዝግጅቶች በተግባር የተኩት የሊቱርጊያ ባዶ (liturgical vacuum) ምን እንደሆነ ለማመልከትና መፍትሔውን ለማሳየት ይጥራል። The Problem of Reactive Ministry እና Institutional Survivalism በርናባስ በጽሑፉ የሚተቸው አንዱ ነገር ይኽ ተልእኮን

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

“የአእላፋት ዝማሬ”

ሁለተኛው የአእላፋት ዝማሬ ባለፈው ዓመት በልደት ዋዜማ ተካሔደ ። በአዘጋጆቹ እና በተሳታፊዎቹ ዘንድ ይህ ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው ዙር በላይ ያማረ እና የሠመረ ሆኖ ተቆጥሯል ። በጠቅላላው ከምእመናን በኩል በተሳትፎም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ ያገኘው ተቀባይነት ሌሎች ሁነቶች ሲሆኑ እንደምናየው በጅምር የሚቀር ሳይሆን እንደ ባህል የመተከል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን ያመላክታል ። እንዲያውም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ብቻ ሳይወሰን ወደ ሌሎች ቦታዎችም እንዲሰፋ የሕዝብ ጥያቄ እና በአዘጋጆቹም በኩል እቅድ መኖሩ ይታወቃል ። ስለዚህ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ልክ እንደ ጥምቀት ሁሉ በሁሉም ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ (የአዘጋጆቹ አቅም በፈቀደው ልክ) የአእላፋት ዝማሬ የልደት በዓል መለያ ሆኖ እንዲካሔድ መጠበቅ እንችላለን ። ይህ ነገር በብዙዎች ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጥቅም የሚሰጥ ሆኖ ይታያል ። በእነርሱ ዐይን ይህ ሁነት ቤተ ክርስቲያን በብዙዎች ዘንድ እንድትታወቅ ያደርጋል ። ብዙዎች በዓሉን አስመልክተው ከሚሔዱባቸው የማይገቡ ዓውዶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ ከማድረጉ ባሻገር ፥ በቤተ ክርስቲያን ሱታፌ ያላቸውንም በሚስብ እና በሚገባቸው መልኩ ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ እንዲያውቋት ያስችላቸዋል ። ስለዚህም የሌሉትን በመጥራት ፥ ያሉትንም በማጽናት ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን እንድትዋጅ የሚያስችላት መሣሪያ ነው ፤ ከእርሷ ዘንድ ወደ ክሕደት እና ወደ ኑፋቄ የፈለሰውን ፥ ወይም በስም ክርስቲያን ሆኖ እና ማዕተብ አስሮ ሳለ በምድራዊ ተድላ ባሕር የሰጠመውን ወጣት ወደ ራሷ የምትስብበት መረብ ነው ። ነገር ግን ከኖረው የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና አስተምህሮ አንጻር ከመረመርነው ፥ ይህ ሁነት

Read More »
Emmaus Posts
ኤልያስ ገብረ ሥላሴ

መከራ ፣ እከይ እና ክርስትና

መከራ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ድንገተኛ የሆነ ክስተት አይደለም ። ፍቅር በሆነው እግዚአብሔር ለጥቅማችን የሚፈቀድ የእርምት መንገድ ነው እንጂ ። በየዘመኑ ቤተክርስቲያን በወቅታዊ ሁነቶች እንድትወጠር እና መሠረታዊ ነገሮች ትኩረት እንዳያገኙ የሚቀርብ ፈተና አለ ። ሰበር ዜናዎች ፣ ወቅታዊ አጀንዳዎች ፣ አከራካሪ ጉዳዮች ወዘተ ከመነኩሴ መቁጠሪያ በላይ በሚሽከረከሩበት ዘመን ላይ ነው የምንገኘው ። እነዚህ ሁነቶች ትኩረታችንን ይወስዱትና ሳይታወቀን መሠረታዊ ከሆኑትና ዘለዓለማዊነታችንን ከሚበይኑት ጉዳዮች ወጥተን ምድራዊና እዚሁ ቀሪ በሆኑ ጉዳዮች ተወጥረን እንገኛለን ። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁኔታ በቤተክርስቲያንን መምህራን እና “ተጽዕኖ ፈጣሪዎች” ላይ እጅግ በርትቶ የሚታይ መሆኑ እና በቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እና መድረኮች ሳይቀር ሰፊውን ሰዓት መያዙ ነው ። የቤተክርስቲያን ተልእኮ ስለ ክርስቶስ ምስክር መሆን ነው ። መሠረታዊ ካልሆኑት ሁነቶች ወጥተን ወደዚህ ዋነኛ ተልእኮአችን እንድንመለስ ተዋሥኦ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ። ይህ በምእመናን ፥ በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲን አገልጋዮች ፥ ዘንድ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ። የሁነቶችን መሠረት መመርመርና ትክክለኛ ባሕርያቸውን መረዳት ያሻል ። ሁነቶቹ ችግሮች የሆኑ እንደሆነ ሥር ነቀል መፍትሔ ማሰብ የሚቻለው ፥ መልካም አጋጣሚዎችም ከሆኑ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ልናውላቸው የምንችለው የሁነቶቹን መሠረት በጥልቀት መረዳት ከቻልን ነው ። በመቀጠልም ተከትለው ሊደረጉ ስለሚገቡ ነገሮች መወያየት ከተቻለ ብቻ ነው ። ካልሆነ አሁን እየሆነ እንዳለው የወቅታዊ አጀንዳዎች አሳዳጅ ብቻ ሆነን ነው የምንቀረው ። በተለይ ዘመናችን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ስለሆነ በዚህ

Read More »
Emmaus Posts
መሐሪ ዘመልአክ

ከእውነት አልባነት ጋር የሚካሔድ ሙግት

(‘ሐሳቦች መዘዝ አላቸው’ በሚል ርእስ በኤማሁስ መጽሔት ቅጽ 1 ፣ ቁጥር 1 በወጣው ጽሑፍ ላይ የተጻፈ አስተያየት) በመሐሪ ዘመልአክ (PhD) ከዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት የእጓለ ገብረ ዮሐንስ ‘የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ’ ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበብኹ በኋላ ጸሐፊውን ከዚያ በፊት አለማወቄ ገርሞኝ እንደነበር አስታውሳለኹ ። ማን ናቸው ? እንዴት እስከዛሬ ድረስ ስለእርሳቸው ሳልሰማ ቀረኹ ? ለምን ? ይኼ በ1956 ዓ.ም. የታተመ የሬድዮ ንግግር ከኾነ መጽሐፍ ለመጻፍ ብለው ተነሥተው ቢጽፉ ኖሮ ምን ሊጽፉ ነበረ ? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎች ጭንቅላቴ ውስጥ ተመላልሰዋል ።[1] በኋላ ፈላስፋው ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተማሪና መምህር እንደነበሩ ስሰማ በመጽሐፉ ውስጥ ያየሁት የሐሳብ ጥልቀት በዘመኑ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልሒቃን ዘንድ የነበረው ተዋሥኦ ሊደርስ ይንጠራራበት የነበረውን ልክ የጠቆመኝ መሰለኝ ። ከዚያ በኋላ ያ የተዋሥኦ ልሕቀት የት ገባ ? እንዴት ድርቅና የተጫነው ተዋሥኦ ዋጠው ? እንዴት ኦርቶዶክሳዊነትን ከአመክንዮ የተፋታ እና አመክንዮን የሚፈራ ጭፍን እምነት የሚያስመስሉ የፎክሎር ሰባኪዎች ተፈለፈሉብን ?  የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህን ለመኾን የሚጠየቀው መስፈርት ስለምን ድፍረት የለበሰ አላዋቂነት መሰለ ? በሚዲያ ላይ ሲናገሩ በአላዋቂነታቸው አንገታችንን የማያስደፉን ካህናት ስለምን ቁጥራቸው አልበረክት አለን ? ኦርቶዶክሳዊነት ችግርን እና ጭንቀትን ለማረሳሳት የተጠመቀ ዕፀ-ዝንጋዔ (‘opium of the masses’) እስኪመስል ድረስ በኦርቶዶክሳዊነት ስም የገነነው ተዋሥኦ ለምን አላዋቂነት ተጫነው ? ቤተ ክርስቲያን ሲባል ከስሜታዊ ሙጥኝታ (sentimental attachment) ባለፈ ለሰው ልጅ ህልውናዊ ጥያቄ የተሰጠ ከሞት ፍርኃት

Read More »
Emmaus Posts
ኤማሁስ

የኤማሁስ መንገድ

መጽሔቷን ለማግኘት ይህን ይጫኑ . . . የዘመናችን ተዋሥኦ በይዘቱም ሆነ በመንገዶቹ በግልብነት በእጅጉ የተጠቃ ነው ። ‘በይዘቱ እንዴት ?’ቢባል ሁነቶች ላይ ያተኮረ እና ወቅታዊነትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ። አንድም አቋም ከመያዝና ጎራ ከፍሎ ከመናቆር ባለፈ የእውነት የመማር እና የማሰላሰል ጉጉት የማይታይበት በመሆኑ ። በዚህ ተዋሥኦ ውስጥ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሣት እና ከሁነቶቹ የሚሻገር እና ሐሳባዊ የሆነ ትንተና ለማካሔድ መሞከር ትኩረት ያስነሣል ፤ ሲብስም አጉል እንደመራቀቅ ይታያል ። የሚካሄድበት ከባቢ እና ዘመን ደግሞ ሌላ ግልብነት ደርቦለታል ። በእኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሀገራት ፣ ከዘመናዊነትና ከቴክኖሎጂ መራቀቅ ጋር ተያይዞ ሕዝባዊ ተዋሥኦ በጠቅላላው ስለቱን እና ርቀቱን እንዲያጣ ሆኗል ። የሚነበብም ሆነ የሚታይ ወይም የሚደመጥ ነገር አጭር መሆን አለበት ። ነገር ግን ጠቃሚና ወሳኝ ርእሶች እንዲህ ባለ መንገድ ሊስተናገዱ አይችሉም ። የሚያጠግብ ፍሬ ከሌለበት የተመልካቹ እና የአንባቢው ብዛት ምን ጥቅም ይኖረዋል ? እንዲህ ባለው ከባቢ ውስጥ ሁነቶችን ከሁነትነታቸው እና ከሚያመጡት ወቅታዊ ውጤት በተሻገረ መልኩ ለመመልከት እንቸገራለን ። ቀድሞውኑም (እይታችን ከመጥበቡ የተነሣ) ጠባብ አድርገን የቀረጽነውን አጀንዳ በምንገልጽበት መንገድ የበለጠ እናጠብበዋለን ። ነገር ግን ሁነቶችን እና ሒደቶችን ከመሠረታቸው መመርመራችን እና የምናቀርባቸው መፍትሔዎችም እንዲሁ የማይናወጥ መሠረት ያላቸው መሆናቸው አስፈላጊ ከሆነ ተዋሥኦውም እንዲሁ የጠለቀ እና የረቀቀ መሆን አለበት ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ጊዜ ወስዶ ማሰብ ፣ ማንበብ ፣ ማጠናቀር ፣ መወያየት ፣ መሟገት እና እንዲህ ካለው ሒደት

Read More »
Emmaus Posts
በርናባስ ሽፈራው

ክፍል ፭ ፡ ወደ ርስታችን ያልተመለስንበት ኢዮቤልዩ

ሩሲያዊው ደራሲ ፌዮዶር ዶስቶየቭስኪ በ1860ዎቹ አውሮፓን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጎበኝ የታዘበውን በዘገበበት ማስታወሻው የለንደን ድሆች ቅዳሜ ማታን እንዴት ባለ መንገድ እንደሚያሳልፉ ይነግረናል ። በቅድሚያ ሌሊቱን በሙሉ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ጭምር ደስታ ፈጽሞ በተለየው ፣ ድብርት በተጫነው መንፈስ አኳዃን ሲበሉ እና ሲጠጡ ፣ ከሕይወታቸው መራራነት ለማምለጥ ፣ ራሳቸውን ፍጹም ለማደንዘዝ በሙሉ ጥምብዝ እስኪሉ እንደሚሰክሩ መስማቱን ይዘግባል ። ሳምንቱን ሙሉ ሠርተው የቋጠሯትን ገንዘብ ቅዳሜ ሌሊት እንዲህ ይበትኗታል ። አስከትሎም እንዲህ ባለው አንድ ምሽት እሱ ራሱ በመንደራቸው ውስጥ ሲያልፍ የታዘበውን እና የተሰማውን እንደሚከተለው ይመሰክራል ። “One such night – it was getting on for two o’clock in the morning – I lost my way and for a long time trudged the streets in the midst of a vast crowd of gloomy people, asking my way almost by gestures, because I do not know a word of English. I found my way, but the impression of what I had seen tormented me for three days afterwards. The populace is much the same anywhere, but there all was so vast, so vivid that you almost physically felt things which up till then you had only imagined. In London, you no longer see the populace. Instead, you see a loss of sensibility, systematic, resigned and

Read More »